Get Mystery Box with random crypto!

ክፍል ሁለት በተስፋ እና በታማኝነት ውስጥ ያለህ ደስታ # አንድ ሰው፣ የሚረብሽ ነገር ቢያጋጥመውም | ዩአንገሊዎን

ክፍል ሁለት
በተስፋ እና በታማኝነት ውስጥ ያለህ ደስታ
# አንድ ሰው፣ የሚረብሽ ነገር ቢያጋጥመውም እንኳ ልቡ በደስታ ሊሞላ ይችላል። ደግሞም ይሞላል ለምሳሌ ያህል፣ ሐዋርያቱ ስለ ክርስቶስ በመናገራቸው ምክንያት ተገርፈው ነበር። ሆኖም ከሳንሄድሪን ሸንጎ ሲወጡ “ስለ ስሙ ውርደት ለመቀበል ብቁ ሆነው በመቆጠራቸው ደስ እያላቸው” ነበር። (ሥራ 5:41) ሐዋርያቱ ደስ ያላቸው ስለተገረፉ እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ይሁንና የእግዚአብሔር አምላክ አገልጋዮች እንደመሆናቸው መጠን ለእርሱ ያላቸውን ታማኝነት በመጠበቃቸው እውነተኛ ደስታ አግኝተዋል።
#እንዲህ ያለው ደስታ ስንወለድ ጀምሮ የሚኖረን አሊያም ያለምንም ጥረት የምናገኘው ነገር አይደለም። ለምን? ምክንያቱም እውነተኛ ደስታ ከመንፈስ ፍሬ ገጽታዎች አንዱ ነው። በእግዚአብሔር አምላክ በቅዱስ መንፈስ እርዳታ “አዲሱን ስብዕና” በተሟላ ሁኔታ መልበስ የምንችል ሲሆን ይህም ደስታን በሙሉነት ያካትታል። ደግሞም በእውነተኛው ደስታ እንሞላለን ። “ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ።”ኤፌሶን 4፥24 . “የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።” ገላትያ 5፥22 #በአጠቃላይ ደስታ ሲኖረን ደግሞ የሕይወትን ውጣ ውረዶች በተሻለ ሁኔታ በታማኝነት መቋቋም እንችላለን። አሜን
ለመሆኑ ደስታን እንዴት አድርገን ነው የምናስባት? ማንን ነው የምትመስለው? ፈንጠዚያ ደስታ ናት? ያለማቋረጥ በሳቅ መንከትከት ደስተኝነት ነው? በምቾት መንገላታትስ? ምንድናት ደስታ? እንዴት ነው የደስታን ጅራቷን መያዝ የሚቻለው?
እኛ ነገሮች እንደጠበቅነው በማይሆኑበት ጊዜ ከልክ በላይ ባለመጨነቅ በታማኝነት ይሖዋን መምሰል እንችላለን። ደስታችንን ከማጣት ይልቅ አሁን ባሉን ጥሩ ነገሮች ላይ ማተኮርና ወደፊት የምናገኛቸውን የተሻሉ ነገሮች በትዕግሥት መጠበቅ ተስፋችን በታማኝነት ከደስታ ጋር መያዝ እንችላለን።
ፈታኝ ሁኔታዎች ቢያጋጥሟቸውም ደስታቸውን ሳያጡ በታማኝነት የተሰጣቸውን ተስፋ አጽንተው በመያዝ መኖር የቻሉ በርካታ ምሳሌዎችን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እናገኛለን። አብርሃም የደረሱበትን ለሕይወት አስጊ የሆኑ ሁኔታዎችና ችግሮች በጽናት እና በታማኝነት ተቋቁሟል። (ዘፍ. 12:10-20፤ 14:8-16፤ 16:4, 5፤ 20:1-18፤ 21:8, 9) አብርሃም፣ ሌሎች ሰዎች እንደዚህ ያሉ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ቢፈጥሩበትም ደስታውን ጠብቆ መኖር ችሏል። ይህን ማድረግ የቻለው እንዴት ነው? በመሲሑ አገዛዝ ሥር በአዲሱ ዓለም ውስጥ የመኖር ተስፋው በአእምሮው ውስጥ ብሩህ ሆኖ ይታየው ስለነበረ ነው። (ዘፍ. 22:15-18፤ ዕብ. 11:10) ኢየሱስ “አባታችሁ አብርሃም ቀኔን እንደሚያይ ተስፋ በማድረግ እጅግ ተደሰተ” በማለት ተናግሮ ነበር። (ዮሐ. 8:56) እኛም ወደፊት በምናገኘው ደስታ ላይ በማሰላሰል አብርሃምን ልንመስለው እንችላለን።—“ተስፋውም ፍጥረት ራሱ ደግሞ ከጥፋት ባርነት ነፃነት ወጥቶ ለእግዚአብሔር ልጆች ወደሚሆን ክብር ነፃነት እንዲደርስ ነው።”ሮሜ 8፥21
እንደ አብርሃም ሁሉ ሐዋርያው ጳውሎስና ጓደኛው ሲላስም አምላክ በሰጣቸው ተስፋዎች ላይ ያሰላስሉ ነበር። ጠንካራ እምነት የነበራቸው ሲሆን አስቸጋሪ ሁኔታዎች ቢያጋጥሟቸውም እንኳ የተጠሩበትን የሕይወት ዓላማ በታማኝነት በመያዝ ደስታቸውን ሳያጡ መኖር ችለዋል። ለምሳሌ ያህል፣ በአሰቃቂ ሁኔታ ተደብድበው ወደ ወህኒ ከተጣሉ በኋላ “እኩለ ሌሊት ገደማ . . . እየጸለዩና አምላክን በመዝሙር እያወደሱ” እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። (ሥራ 16:23-25) ጳውሎስና ሲላስ ብርታት እንዲያገኙ የረዳቸው አንዱ ነገር ተስፋቸው ነው፤ ከዚህም በተጨማሪ መከራ የደረሰባቸው በክርስቶስ ስም የተነሳ መሆኑ ደስተኞች እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። እኛም አምላክን በታማኝነት ማገልገል ደስታን እንድሆን የሚያስገኘውን መልካም ውጤት ማስታወሳችን የጳውሎስንና የሲላስን ምሳሌ ለመከተል ያስችለናል።—ፊልጵ. 1:12-14 https://t.me/Yoangeliwon