Get Mystery Box with random crypto!

በፋሲካ ............. በፋሲካው እኛን ከእርሱ እኛን በእርሱ እኛን ለእርሱ ለክብሩ ምስጋና | ዩአንገሊዎን

በፋሲካ .............
በፋሲካው እኛን ከእርሱ እኛን በእርሱ እኛን ለእርሱ ለክብሩ ምስጋና እንሆን ዘንድ ከአብ ጋር አስታርቆ የጥልን ግርግዳ በሥጋው አፍርሶ የድነታችን ቤዛነት በመስቀል ላይ በመሞት ፈፅሞ ዘላለማችንን አሳመረው ወደ አብ መሄጃ (መድረሻ) እውነተኛ መንገድ ሆኖ ኢየሱስ ተነስቶል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለዓመፀኞች ማልዶ።

ወዳጆቼ በየአመቱ የምንሰቅለው ኢየሱስ የለንም ትንሳኤውን ስናስብ እግዚአብሔር አብ ለእኛ ያሳየን ፍቅር እግዚአብሔር ወልድ የታገሰለን የትግስትን ጥግ መረዳት እድንችል እመኛለሁ ለዚህም ነው ቃሉ እንዲህ የሚለን “ጌታም ወደ እግዚአብሔር ፍቅር ወደ ክርስቶስም ትዕግሥት ልባችንን ያቅናው።” የሚለን 2ኛ ተሰሎንቄ 3፥5

ስለዚህ ወዳጆቼ መልካም የትንሳኤ መታሰብያ ቀን እንዲሆንላችሁ በእዚህም ቀን ይህን እንድታስብ “የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን። “እንግዲህ ያለ እርሾ እንዳላችሁ አዲሱን ሊጥ ትሆኑ ዘንድ አሮጌውን እርሾ አስወግዱ። ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና፤” የእግዚአብሔርን አብ ፍቅር እና የእግዚአብሔርን ወልድን (የክርስቶስን) መስዋዕትነት እንድታስብ ብርቱ ምኞቴ ነው። 1ኛ ቆሮንቶስ 5፥7 1ኛ ዮሐንስ 3፥1
መልካም የትንሳኤ መታሰቢያ ቀን ይሁንላችሁ

አገልጋይ አቤነዘር ዳዊት
ቀን 16/8/2814 ዓ/ም


https://t.me/Yoangeliwon