Get Mystery Box with random crypto!

የተዋህዶ አርበኞች-Ye Tewahedo Arbegnoch

የቴሌግራም ቻናል አርማ yetewahedoarbegnoch — የተዋህዶ አርበኞች-Ye Tewahedo Arbegnoch
የቴሌግራም ቻናል አርማ yetewahedoarbegnoch — የተዋህዶ አርበኞች-Ye Tewahedo Arbegnoch
የሰርጥ አድራሻ: @yetewahedoarbegnoch
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.53K
የሰርጥ መግለጫ

#ኢትዮጵያ_የዓለም_ብርሃን
ክንድህን ኃይልህንም ጽድቅህንም እስክነግር ድረስ አቤቱ አትተወኝ
#መዝሙር_ዳዊት 70 ( 71 ) 15 – 18

"የመለከቱን ድምፅ የሚሰማ ሰዉ ባይጠነቀቅ፥ ሰይፍ መጥቶ ቢወስደዉ፥ ደሙ በራሱ ላይ ይሆናል።
"የመለከቱን ድምፅ ሰምቶ ስላልተጠነቀቀ ደሙ በራሱ ላይ ይሆናል፤ ቢጠነቀቅስ ኖሮ ነፍሱን ባዳነ ነበር።"
#ትንቢተ_ህዝቅኤል 33፡4-5

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-29 11:27:25
የቤሩቱ ኮከብ የልዳው አንበሳ የኢትዮጵያ ገበዝ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ፡፡
#ሀይል_ኮከብ_ክብር።
806 views08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 09:44:17
#የተስፋ_ቃል!!!
...ምድራችን እዉነትን በማያዉቁ አመጸኞችና ወንጀለኞች የዲያብሎስ ልጆች ስለተሞላች በግድ መጽዳት አለባት። ለቅዱሳንም የተመቸችች የበረከት ምድር ልትሆን ይገባል! ስለሆነም ይኸዉ የፈጣሪ ፈቃድ ይፈጸማል።

በኢትዮጵያ የሚደርሰው የሚፈጸመው ሁሉ እነሆ ይመጣል! እግዚአብሔር የቀባቸው በምድሪቱ ላይ ሲነግሱ ያኔ ብቻ የእረፍት ጅማሮ ይሆናል። ይህ እስኪሆን ግን ዓለም አይታ የማታውቀውን ጥፋትና ውድመት
ታስተናግዳለች በዚህን ጊዜ ሁሉም የሚጮኸው የፈጣሪ ቁጣ እንዲቆምለት ብቻ ነው። ያ ደግሞ የሚሆነው የታዘዘው ሁሉ ሲፈጸም የእግዚአብሔርም ሕዝቦች ነጻ ሲወጡ ብቻ ነው።

የታመኑ የፈጣሪ ልጆች በዓለም ሁሉ ፊት የሚያበራውን ከጌታ የተሰጣቸውን ስልጣን ሲያፀኑ! ሁሉም ሲንበረከክና ለፈጣሪና ላከበራቸው ሲገዛ ብቻ ነው! ሰላም፣ በረከት፣ ቸርነት፣ የሚሆነው ይኸው ሲሆን ብቻ ነው። ይህ ደግሞ ከብዙ ጉዳት በህዋላ የሚፈጸም ነው።

ምክንያቱም የሰው ልጅ ትእቢቱንና አውቃለሁ ባይነቱን ቶሎ አይጥልምና!! ዓለም ሁሉ በታላቅ እንባና ጩኸት ይሞላል። ከቁጣው ብርታት የተነሳ ዓለም ያለፈች እስኪመስል ድረስ፤ አሁንም ደግሜ እለዋለሁ! በኢትዮጵያና በዙሪያዋ ባሉ ተራሮች (ሀገሮች) ሁሉ የብርሃን ዙፋኑን የሚዘረጋው ጌታ ልጆቹን ከዙፋኑ ላይ ሲያስቀምጥ ብቻ ነው ቁጣው መስከን የሚጀምረው ከዚህ ውጪ የሚመጣ አንዳችም ነገር የለም።
ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልእክት 2
#ኢትዮጵያ_የሥላሴ_የክብራቸው_መገለጫና_መመስገኛ_ምድር
#ኢትዮጵያ_ርስተ_ድንግል_ማርያም
#ኢትዮጵያ_የዓለም_ብርሃን
#ኢትዮጵያ_የዓለሙ_ገዥ
992 views06:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 09:33:28 #ኢትዮጵያ_የዓለም_ብርሃን_እምነት_ተስፋ_ፍቅር_ትምህርት
❖ የእውነት ሰው፣ የእምነት ሰው፣ የእግዚአብሔር ሰው ጽኑና የማይፈራ፣ የማይነቃነቅ መሰረቱ የጠበቀ አለት ማለት ነው።
አለቱ ክርስቶስ አይደል እሱ ላይ የተመሰረተ ስለሆነ አለት ነው።
የእግዚአብሔርን ፈቃድ አድርጋችሁ ❖ የተሰጣችሁን የተስፋ ቃል እንድታገኙ መጽናት ያስፈልጋችኋልና ይለናል ቃሉ።
#ልብ_በሉ.....
❖ አምናችሁ አይደል በእምነት ውስጥ አይደል ያላችሁት ካመናችሁ በኋላ የእግዚአብሔር ድምጽ ወደ እናንተ ይመጣል። በቃሉ ይናገራችኋል፣ በራዕይ ይናገራችኋል፣ በሕልም ይናገራችኋል።
ማን? #እግዚአብሔር_የአብርሃሙ_ሥላሴ!!!
❖ ዛሬም ምድሪቱን የሚያጽናናው ከሦስቱ አካል አንዱ የሆነው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ዘውትር ስለ እውነት ይናገራችኋል፣ መንገዱን ያሳያችኋል፣ ያጸናችኋል። ምንም ጨለማ ቢሆን ምንም ማዕበል ቢፈስ፣ ቢጠርግ ልትነቃነቁ አይገባም፣ ልትጨነቁ አይገባም።
የተሰጣችሁን የተስፋ ቃል እንድታገኙ መጽናት ያስፈልጋችኋል።
❖ የተስፋውን ቃል የጠበቀ ከእምነት ተነስቶ ተስፋ ያደረገ የጸና ነው ባለድል የሚሆነው።
#ልብ_በሉ

''....ገና በጣም ጥቂት ጊዜ ነው ሊመጣ ያለው ይመጣል፣አይዘገይም፤ ጻዲቅ ግን በእምነት ይኖራል''።
#ኢትዮጵያ_የዓለም_ብርሃን...#እምነት_ተስፋ_ፍቅር ክፍል ሁለት ትምህርት 'ሠ' ከ 00: 10: 16 - 00: 12: 02 ደቂቃ ላይ የተወሰደ።
ከመልካሙ እረኞ ንጉሰ ነገስት ሣልሳዊ ቴዎድሮስ
702 views06:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 16:07:40
እንቁ የኢትዮጵያ ዓለም ብርሃን ቤተሰቦች!
798 views13:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 14:18:05
የኢትዮጵያ ሕዝበ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያንህን ከወደቀችበት አንሳ።

ሃይማኖት ካለ ሁሉን ማድረግ እንደሚቻል የተረጋገጠ ነው። እኔ ገንዘብ የለኝም ካለኝ ልስጥህ " በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሥ " የሚለውን ያን ሃይማኖታዊ ድምፅ ምን በላው? መጽሐፍ ቅዱስ አንጋቢዎች ብዙ ናቸው። ኃይሉ ግን የላቸውም ችግሩ ይህ ነው። ለኢትዮጵያ ሕይወት ሆና የኖረችውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ተቃዋሚዎችም መሪዎችም ተባብረው ስለገደሏት ፣ ስለቀበሩዋት የኢትዮጵያ ሕዝብ በልዩ ልዩ ችግር ላይ ወድቆ ይታያል። አሁንም ከእርስዋ በቀር ሕይወት መድኃኒት የሚገኝበት ሃይማኖት የለምና የኢትዮጵያ ሕዝበ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያንህን ከወደቀችበት አንሳ።ያን ጊዜ መልካም ነገር ሁሉ የአንተ ነው።በእግዚአብሔር አትጠራጠር የነበረህን ሃይማኖት፣ ሥርዓት ፣ ባህል አጽና።የቅልውጡን ተወው አያገለግልህም።

ክቡር አለቃ አያሌው ታምሩ
902 views11:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 18:56:29
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እቴ ሙሽራዬ ሆይ:- የተቆለፈ ገነት ነሽ ; የተዘጋ አትክልትና የታተመ ምንጭም:: በምሥራቅ በኩልም የተዘጋ አዳራሽ አሳየኝ : ይህ ቤት የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር አልፎበታልና ለዘለዓለም የተዘጋ ሆኖ ይኖራል አይከፈትም አለኝ:: " ብለው ከተናገሩ ነቢያት ከሰሎሞን ከሕዝቅኤል ጋር ሆና እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የዘለዓለም ድንግል መሆኗን ታምናለች ትመሰክራለች::

ወላዲተ አምላክ በኢትዮጵያ
ሊቀ ሊቃውንት አያሌው ታምሩ
376 views15:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 18:55:57
ከሔዋን ጀምሮ በተሰጠው ሥነ ተፈጥሮና ፍርድ፣ ሴቶች በሐልዮ፣ በነቢብ፣ በገቢር በፍትወት ይጠመዳሉ። ኋላም በጋብቻ ለአንድ ወንድ ይኾናሉ። ድንግልናን ያጣሉ። በሕማም ይፀንሳሉ ፣ በሕማም ይወልዳሉ፣ ከ ፲፭ ዓመት በኋላ ተፈትሖ ማሕፀን አለባቸው። ቢወልዱም ባይወልዱም በየወሩ የወር ግዳጅ ከነሕመሙ አለባቸው። በድሮ ቋንቋ አደፍ ያያሉ ይባላል። በዛሬው ግን አበባ ተብሎአል። እንግዲኽ ይኽ ሁሉ በእመቤታችን የለም። እግዚአብሔር ከዚህ ሁሉ ጠብቋታል አድኗታል። ከመርገመ ሥጋ ከመርገመ ነፍስ ጠብቋታል። እላይ የዘረዘርነው ኹሉ በአምላክ ፍርድ የጸና ስለኾነ በሴቶች ላይ የማይለወጥ ያልተለወጠ ግዳጅ ነው። በእመቤታችን ግን ይኽ ሁሉ የለም። ለምን? ቢሉ ምክንያቱ መልአኩ " ቡርክት አንቲ እምአንስት" ብሎ እንደመሰከረ ከሴቶች ተለይታ የተባረከች ናትና ፣ እንከን ለሌለው ደስታ የተፈጠረች ናትና፣ ጸጋን ኹሉ የተሞላች ናትና ፣ እግዚአብሔር ከእርሷ ጋር ነውና፣ እናቱ ልትሆን፣ ማደሪያው ልትሆን ፣ መቅደሱ ዙፋኑ ልትኾን ቅድስተ ቅዱሳን አድርጎ ፈጥሮአታልና። ለምን? የሚል ጥያቄ የሚገባበት አይደለም። ሥልጣኑ ፣ ሥራው ገንዘቡ ነው። እግዚአብሔር ቅዱስ ነው ፣ ዙፋኑም ቅዱስ ነው።
" እግዚአብሔርሰ ይነብር ዲበ መንበሩ ቅዱስ።" "እግዚአብሔር በቅዱስ ዙፋኑ ላይ ይኖራል" ተብሎ ተጽፎአል። ( መዝ.፵፮:፰) እሱ ቅዱስ ነው እናቱም ቅድስት ናት።

ሊቀ ሊቃውንት አያሌው ታምሩ።
398 views15:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 13:59:42
ለሰዉ ሁሉ ከመገዛት የሚያወጣ የነፃነት መፅሀፍ የተፃፈባት ማህፀን ምንኛ ድንቅ ናት፤ እግዚአብሄር ከባህርዮ ሳይለወጥ፣እንደ መልከ ፄዴቅ ያለ ክህነትን ገንዘብ ያደረገ ካህን ሆኖ ያገለገለባት(ሰዉ የሆነባት) መቅደስ ምንኛ ድንቅ ናት...።
#ቅዱስ_ፕሮክልዮስ
#ዛሬ በተለያዮ ገዳማት፣ በየ በርሃው ያሉ አባቶቻችን እና እናቶቻችን ሱባኤ ጨርሰዉ የሚሰባሰቡበት ቀን ነዉ።
#ቸር_ያሰማን!
591 viewsedited  10:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 10:12:05 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
እምነት ተስፋ ፍቅር
ትምህርት ክፍል 2
533 views07:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 10:12:05 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
እምነት ተስፋ ፍቅር
ትምህርት ክፍል 2
512 views07:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ