Get Mystery Box with random crypto!

የተዋህዶ አርበኞች-Ye Tewahedo Arbegnoch

የቴሌግራም ቻናል አርማ yetewahedoarbegnoch — የተዋህዶ አርበኞች-Ye Tewahedo Arbegnoch
የቴሌግራም ቻናል አርማ yetewahedoarbegnoch — የተዋህዶ አርበኞች-Ye Tewahedo Arbegnoch
የሰርጥ አድራሻ: @yetewahedoarbegnoch
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.53K
የሰርጥ መግለጫ

#ኢትዮጵያ_የዓለም_ብርሃን
ክንድህን ኃይልህንም ጽድቅህንም እስክነግር ድረስ አቤቱ አትተወኝ
#መዝሙር_ዳዊት 70 ( 71 ) 15 – 18

"የመለከቱን ድምፅ የሚሰማ ሰዉ ባይጠነቀቅ፥ ሰይፍ መጥቶ ቢወስደዉ፥ ደሙ በራሱ ላይ ይሆናል።
"የመለከቱን ድምፅ ሰምቶ ስላልተጠነቀቀ ደሙ በራሱ ላይ ይሆናል፤ ቢጠነቀቅስ ኖሮ ነፍሱን ባዳነ ነበር።"
#ትንቢተ_ህዝቅኤል 33፡4-5

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-08-24 18:45:11 #ሦስቱ_ዋንኛ_ቀሪ_ትንቢቶች!!
(በወንድማችን ተክለኪዳን)
ከእንግዲህ ለዓለም ፍጻሜ የሚቀሯችሁ ሦስት ዋንኛ ትንቢቶች የሚከተሉት ናቸዉ፡፡
1. ዓለም ብትመከር፣ ብትገሰጽ፣ እጇን እንድትሰጥ ብትጠየቅ፣ አሻፈረኝ ዲያብሎስ ይበልጥብኛል ብላለች፡፡ እናንተ የአዳምና የሔዋን ዘሮች ወደ እኔ በንሰሐ አለመለስም ብላችኋል፤ ከእኔ የሆነዉን እዉነት አልቀበልም ብላችኋል፤ እያንዳንዱ አገር የዘራዉን ያጭዳል፤ የዓመፃዉን ፍዳ ይቀበላል፡፡ ይህም የመጨረሻ ፍርዴ ሩቅ አይምሰላችሁ፤ በደጃችሁ ቆሟል፡፡ እኔን ከመፍራትና ከማወቅ ስለራቃችሁ ማስተዋሉን አላገኛችሁም እንጂ ደጃፋችሁን አልፌ ከቤታችሁ ነኝ፡፡

2. ስራና የዓመፃ ልጆችን ከዚህች ምድር ካጸዳዉ በኋላ በእኔ የተመረጠዉ የእናቴ የአደራ እናታችሁ የእመቤታችሁ ምርጥ ባለሟል ለሆነዉ ለኢትዮጵያዊዉ ሰዉ ይህችን የተቀደሰች አገርና ዓለምን በእጁ አሳልፌ እሰጠዋለሁ፡፡ ፈቃዴን ይፈጽማል፤ ያስፈጽማል፡፡ ፈቃዴ ሲፈጸም ይህችን አገርና ዓለምን በምሕረት እጎበኛለሁ፤ መልካም ዘመንን አመጣለሁ፡፡

3. ዘመን መጨረሻ አንድ ቀን አሁን የሚደረገዉን ማጥሪያና ማበጠሪያ ኃይሌን እንዲሁም መልካሙን ዘመን የሚዘነጋ ትዉልድ በዓለም ይወለዳል፡፡ በዚያን ጊዜ ዋናዉ የዓመፃ ልጅ (ሐሰተኛዉ መሲህ) (ሐሰተኛዉ ክርስቶስ) (ሐሰተኛዉ አምላክ) ይነሳል፤ በኃይልና በድንቃድንቅ ተአምራት ለዓለም ይገለጣል፡፡ ለሦስት ዓመት ተኩል (ለአርባ ሁለት ወራት) ብቻ ባለ ጊዜ ሆኖ በእኔ የሚያምኑትን ይፈታተናል፣ ያጠቃል፣ ያሰናክላል፡፡ ትዕቢት የተባሉት የፈርኦን ወንድምና እህቶች፣ ክፋት የተባሉት የይሁዳ ወንድምና እህቶች፣ ዓመፃ የተባሉት የአርዮስ ወንድምና እህቶች የክፉ ትንቢት ፈጻሚዎች በዋናነት ተከታዮቹና አጫፋሪዎቹ ይሆናሉ፡፡ ቁጣዉን በመፍራት አእምሮ ሕፃናትና አእምሮ ቀላሎች ይከተሉታል፡፡ አእምሮ አዋቂዎች ይሰናከሉበታል፡፡ ቁጣዉንና ድንቃድንቅ ተአምራቱን በመመልከት አእምሮ ጽኑአን ይፈተኑበታል፡፡

በሦስት ዓመት ተኩል ዉስጥ በእምነቱ የጸና እርሱ ለሰማያዊ መንግሥት የተመረጠ ነዉ፡፡ የዋናዉ የዓመፃና የዓመፃ ልጆች ባለጊዜነት ስሽር ዓለም እንዳልነበረች ትሆናለች፡፡ የዓመፃ ልጆች በመቅሰፍትና በስቃይ ሞት፣ የተመረጡት ሰዎች ደግሞ በምሕረት ሞት ወደ ማረፊያ ቦታ ይጠራሉ፡፡ በዚህች ምድር ዉስጥ ሆነ በዓለም ዉስጥ በዓይን የሚታዩት፣ የማይታዩት ከመኖር ወደ አለመኖር ያልፋሉ፡፡ የዓለም ፍጻሜ በዚህ መልክ ይጠናቀቃል፡፡” ይላል አልፋና ዖሜጋ እግዚአብሔር፤ የቅዱስ ሚካኤል፣ ገብርኤል፣ ሩፋኤል፣ ዑራኤል፣ ፋኑኤል፣ ራጉኤል አምላክ“ ይላል፡፡

ምንጭ "የኢትዮጵያና የዓለም የመጨረሻ ፍርድ አፈጻጸም ዉሳኔ" በመስከረም 2003 ዓ.ም የተጻፈዉና ለሁለተኛ ጊዜ ከታተመዉ ክፍል 2 ምእራፍ 4 ገጽ 55. በተክለ ኪዳን
850 views15:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 08:57:52
#ኢትዮጵያን የሷ ከሆነዉ ጋራ ይዘን ከሌላ ጋር የምንጎዳኝበት የምንተባበርበት፣ የምንዛመድበት መንገድ ካለ ያንን በመልኩ እንያዘዉ የሚል ጠባይ ነዉ ያለኝ።

በስጋዊም በኩል ቢሆን አስተዳደር የሚባለዉ ዛሬ ይሄዉ ተሞከረ ቢያፈልሱት፣ ቢነቅሉት፣ ቢተክሉት አንድ የሚበቅል ነገር አልታየም! አልተገኘም...
#ክቡር_አለቃ_አያሌዉ_ታምሩ
888 views05:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 08:57:31 ...እንኳን ሁለት አይን አንድ አይን ማጣት ይጎዳል፡፡ አሁን ሀገራችን ሁለት አይን አልባናት በሥጋዊውም አይን የላትም በመንፈሳዊም አይን የላትም ወዴት እንደምትሄድ ፣ ምን አንደምታደርግ አታውቅም...፡፡
ክቡር አለቃ አያሌው ታምሩ፡፡
846 views05:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 08:57:11
«እውነትን ጨብጣችሁ ፤ እግዚአብሔርን ጠይቃችሁ መልስም አግኝታችሁ የተረጋገጠ ተስፋን ጨብጣችሁ ያላችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ባለድል ናችሁ ፡፡ እውር አይናማውን ቢተቸው እኔ ልምራህ ቢለው ምንኛ ፌዝ እንደሚሆን ትረዳላችሁ ፡፡ ስለዚህ ማንም ተነስቶ በሚደረድረው ከንቱ ቃል ልባችሁን አታስቱ ! በቅርቡ ሁሉንም እነደቃሉ ሲፈፀም ታያላችሁ ፡፡ ለመሆኑ በኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን የተገለፁ የልኡል የፍርድ ቃሎች መልእክቶች ሲፈፀሙ አላያችሁም የቀሩትስ ለመፈፀማቸው ምልክታቸውን እየሰጡ የሰውን ልጅ በእግዚአብሔር የፍርድ ሚዛን ተለክተው ሲካተቱ እንደምታዩት አልተረዳችሁምን የጥርጥር ችግር ካለባችሁ ልኡልን ጠይቁ ከሰው ይልቅ ከሱ የሚሰጣችሁ ማረጋገጫ ይበልጣልና መጠየቅ መብታችሁ ስለሆነ ጠይቁ ተረዱ ተዘጋጁ በቃ ! ስላበቃ ሁሉም የምታዩት የሚያስቷችሁ የአውሬው የዘንዶው የሃሰተኛው ነብይ ደቀ መዝሙሮች ቅጥረኞች ሆድ አደሮች በሙሉ በቅርብ በክፉ መከራና ስቃይ ሲወገዱ ታዩአቹዋላችሁ፡፡»

➲ ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት 9ኛ መልዕክት ገጽ 18—19 * ተጻፈ ታኅሣሥ 21/2013 ዓ.ም !
917 views05:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 15:49:49



#12_ሰዓት_ላይ_ይለቀቃል!
ሁሉም ሰው ሊያዳምጠው የሚገባ የወንድማችን ተክለኪዳን መልእክት።
1.6K views12:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ