Get Mystery Box with random crypto!

«እውነትን ጨብጣችሁ ፤ እግዚአብሔርን ጠይቃችሁ መልስም አግኝታችሁ የተረጋገጠ ተስፋን ጨብጣችሁ ያላ | የተዋህዶ አርበኞች-Ye Tewahedo Arbegnoch

«እውነትን ጨብጣችሁ ፤ እግዚአብሔርን ጠይቃችሁ መልስም አግኝታችሁ የተረጋገጠ ተስፋን ጨብጣችሁ ያላችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ባለድል ናችሁ ፡፡ እውር አይናማውን ቢተቸው እኔ ልምራህ ቢለው ምንኛ ፌዝ እንደሚሆን ትረዳላችሁ ፡፡ ስለዚህ ማንም ተነስቶ በሚደረድረው ከንቱ ቃል ልባችሁን አታስቱ ! በቅርቡ ሁሉንም እነደቃሉ ሲፈፀም ታያላችሁ ፡፡ ለመሆኑ በኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን የተገለፁ የልኡል የፍርድ ቃሎች መልእክቶች ሲፈፀሙ አላያችሁም የቀሩትስ ለመፈፀማቸው ምልክታቸውን እየሰጡ የሰውን ልጅ በእግዚአብሔር የፍርድ ሚዛን ተለክተው ሲካተቱ እንደምታዩት አልተረዳችሁምን የጥርጥር ችግር ካለባችሁ ልኡልን ጠይቁ ከሰው ይልቅ ከሱ የሚሰጣችሁ ማረጋገጫ ይበልጣልና መጠየቅ መብታችሁ ስለሆነ ጠይቁ ተረዱ ተዘጋጁ በቃ ! ስላበቃ ሁሉም የምታዩት የሚያስቷችሁ የአውሬው የዘንዶው የሃሰተኛው ነብይ ደቀ መዝሙሮች ቅጥረኞች ሆድ አደሮች በሙሉ በቅርብ በክፉ መከራና ስቃይ ሲወገዱ ታዩአቹዋላችሁ፡፡»

➲ ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት 9ኛ መልዕክት ገጽ 18—19 * ተጻፈ ታኅሣሥ 21/2013 ዓ.ም !