Get Mystery Box with random crypto!

#የተስፋ_ቃል!!! ...ምድራችን እዉነትን በማያዉቁ አመጸኞችና ወንጀለኞች የዲያብሎስ ልጆች ስለተ | የተዋህዶ አርበኞች-Ye Tewahedo Arbegnoch

#የተስፋ_ቃል!!!
...ምድራችን እዉነትን በማያዉቁ አመጸኞችና ወንጀለኞች የዲያብሎስ ልጆች ስለተሞላች በግድ መጽዳት አለባት። ለቅዱሳንም የተመቸችች የበረከት ምድር ልትሆን ይገባል! ስለሆነም ይኸዉ የፈጣሪ ፈቃድ ይፈጸማል።

በኢትዮጵያ የሚደርሰው የሚፈጸመው ሁሉ እነሆ ይመጣል! እግዚአብሔር የቀባቸው በምድሪቱ ላይ ሲነግሱ ያኔ ብቻ የእረፍት ጅማሮ ይሆናል። ይህ እስኪሆን ግን ዓለም አይታ የማታውቀውን ጥፋትና ውድመት
ታስተናግዳለች በዚህን ጊዜ ሁሉም የሚጮኸው የፈጣሪ ቁጣ እንዲቆምለት ብቻ ነው። ያ ደግሞ የሚሆነው የታዘዘው ሁሉ ሲፈጸም የእግዚአብሔርም ሕዝቦች ነጻ ሲወጡ ብቻ ነው።

የታመኑ የፈጣሪ ልጆች በዓለም ሁሉ ፊት የሚያበራውን ከጌታ የተሰጣቸውን ስልጣን ሲያፀኑ! ሁሉም ሲንበረከክና ለፈጣሪና ላከበራቸው ሲገዛ ብቻ ነው! ሰላም፣ በረከት፣ ቸርነት፣ የሚሆነው ይኸው ሲሆን ብቻ ነው። ይህ ደግሞ ከብዙ ጉዳት በህዋላ የሚፈጸም ነው።

ምክንያቱም የሰው ልጅ ትእቢቱንና አውቃለሁ ባይነቱን ቶሎ አይጥልምና!! ዓለም ሁሉ በታላቅ እንባና ጩኸት ይሞላል። ከቁጣው ብርታት የተነሳ ዓለም ያለፈች እስኪመስል ድረስ፤ አሁንም ደግሜ እለዋለሁ! በኢትዮጵያና በዙሪያዋ ባሉ ተራሮች (ሀገሮች) ሁሉ የብርሃን ዙፋኑን የሚዘረጋው ጌታ ልጆቹን ከዙፋኑ ላይ ሲያስቀምጥ ብቻ ነው ቁጣው መስከን የሚጀምረው ከዚህ ውጪ የሚመጣ አንዳችም ነገር የለም።
ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልእክት 2
#ኢትዮጵያ_የሥላሴ_የክብራቸው_መገለጫና_መመስገኛ_ምድር
#ኢትዮጵያ_ርስተ_ድንግል_ማርያም
#ኢትዮጵያ_የዓለም_ብርሃን
#ኢትዮጵያ_የዓለሙ_ገዥ