Get Mystery Box with random crypto!

YeneTube

የሰርጥ አድራሻ: @yenetube
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 125.42K
የሰርጥ መግለጫ

መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 16

2024-03-01 13:28:09
ዛሬ አንዲት አህያ መንታ ልጅ ወለደች እኮ ሰምታችኃል ?

የዛሬው FBC ዘገባ ነው ይሄ እንግዲህ

መጠየቅ ለምትፈልጉ :- ቦታው ሀረርጌ ዞን ብርቅ አከባቢ ናት።
14.1K viewsedited  10:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-01 11:32:15 ተፈረደበት

* 1 ዓመት ና
* 2 ሺህ ብር

ኮሜዲያን ያሬድ ዘላለም (ልጅ ያሬድ) በ 1 ዓመት ቀላል እስራትና በ2 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ተወሰነ

የቅጣት ውሳኔውን የወሰነው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ህገመንግስታዊና በህገመንግስት ስርዓቱ ላይ የሚፈጸሙ የወንጀል ጉዳዮችን የሚመለከተው ችሎት ተከሳሹ ያቀረበውን አምስት የቅጣት ማቅለያ አስተያየቶችን ይዟል።

የፍትህ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በኮሜዲያን ያሬድ ዘላለም ላይ ሶስት ክሶችን አቅርቦበት ነበር።

ከቀረቡበት ክሶች መካከል በኮምፒዩተር የሚፈጸም ወንጀል ድንጋጌን መተላለፍ፣ የቤተክርስቲያንና የሰዎችን ክብርና መልካም ስም ማጉደፍ እንዲሁም የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት የሚሉ ተደራራቢ ክሶች ይገኙበታል።

ኮሜዲያን ያሬድ ዘላለም የቀረበበት ክስ እንዲሻሻል የክስ መቃወሚያውን በጽሁፍ ያቀረበ ቢሆንም በዐቃቤ ሕግ በኩል ክሱ ሊሻሻል የሚችልበት የህግ አግባብ እንደሌለ ተጠቅሶ መልስ ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን መርምሮ ተከሳሹ ያቀረበው የክስ መቃወሚያ ጥያቄ የህግ አግባብነት የለውም በማለት ውድቅ አድርጎታል።

ከዚህም በኋላ ተከሳሹ በክሱ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት አለመፈጸሙን በመጥቀስ የዕምነት ክህደት ቃሉን በመስጠቱ ዐቃቤ ሕግ የሰውና የሰነድ ማምረጃውን አቅርቧል።

የቀረበውን ማስረጃ የመረመረው ችሎቱ ተከሳሹ የቀረቡበት ሶስት ክሶች ተጠቃለው በአዋጅ ቁጥር 1185/2012 አንቀጽ 4 እና 7 መሰረት እንዲከላከል ብይን ሰጥቷል።

ሶስቱም ክስ በአንድ እንዲጠቃለል የታዘዘው የወንጀል ድርጊቱ በሀሳብ፣ በጊዜና በቦታ ተመሳሳይ መሆኑን በምክንያትነት ተጠቅሶ ነበር።

ተከሳሹ የመከላከያ ማስረጃ አለኝ ማለቱን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ ያቀረባቸውን የሰው መከላከያ ማስረጃዎችን ቃል አዳምጧል።

ተከሳሹ የሰው የመከላከያ ማስረጃ ያቀረበ ቢሆንም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን በተገቢው መከላከል ባለመቻሉ እና በክስ ዝርዝሩ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት መፈጸሙ በፍርድ ቤቱ በመረጋገጡ በዛሬው ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ ተሰጥቶበታል።

ዐቃቤ ሕግ ድርጊቱ ታስቦ የተፈጸመ መሆኑን ጠቅሶ ቅጣቱ ከብዶ እንዲጣል ጠይቋል።

ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ ለአካባቢ ጥበቃ ያበረከተውን አስተዋጾኦ፣ የቤተሰብ አስተዳዳሪና የቀደመ የወንጀል ሪከርድ እንደሌለው ገልጾ ያቀረበውን የቅጣት ማቅለያ ይዞለታል።

ፍርድ ቤቱ በድርጊቱ የእርስ በእርስ ግጭት አለመፈጠሩንና ጉዳት አለመድረሱን ከግምት ውስጥ በማስገባት በዕርከን 6 መሰረት በአንድ ዓመት ቀላል እስራትና በሁለት ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ወስኗል።

የአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት ተከሳሹ እጁ ከተያዘበት ከነሃሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ያለውን ጊዜ ታሳቢ እንዲያደርግ ታዟል።

Via:- ታሪክ አዱኛ
@Yenetube @Fikerassefa
13.7K views08:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-01 11:30:56 የተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች!!

128ኛው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ክብረ በዓል በአዲስ አበባ ይከበራል፡፡

በዓሉ ፒያሳ አካባቢ በሚገኘው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም እንደሚከበር ተገልጿል፡፡ ለበዓሉ መከበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል፡፡

የካቲት 23 ቀን 2016 ዓ.ም የሚከበረው 128ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል በስኬት እንዲከበር ለማስቻል ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ተግባር መግባቱን ማስታወቁ ይታወቃል፡፡

ክብረ በዓሉ በሚከበር ዕለት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥም እና አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑም የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት፡-
• ከአፍንጮ በር ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን
• ከሰሜን ሆቴል ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን
• ከዮሃንስ ቤተ ክርስቲያን ወደ አቡነ ጴጥሮስ
• ከአራት መንታ ወደ ጅንአድ
• ከይርጋ ሃይሌ የገበያ ማዕከል ወደ አቡነ ጴጥሮስ
• ከሃብተ ጊዮርጊስ ድልድይ ወደ ሱማሌ ተራ
• ከሱማሌ ተራ ወደ ኤሊያና ሆቴል(ባንኮዲሮማ) መስቀለኛ
• ከተክለ ሃይማኖት አደባባይ ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ
• ከአገር አስተዳደር መብራት( ኢሚግሬሽን) ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ
• ከንግድ ማተሚያ ቤት ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ
• ከአሮጌው ቄራ ወደ ባንኮ ዲሮማ መብራት
• ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ደጎል አደባባይ
• ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን
• ከመቅደላ ሆቴል ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን
• ከቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ወደ ቴሌ እና ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ፊት ለፊት ወደሚገኘው አደባባይ የሚወስዱት መንገዶች የካቲት 23 ቀን 2016 ዓ/ም ከንጋቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች ይህንን ተገንዝበው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ እና የትራፊክ ፖሊሶች የሚጠቁሟቸውን አማራጭ አቅጣጫዎችን በመጠቀም አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ክብረ በዓሉ በሚከበርበት ዙሪያ ከዋዜማው ከየካቲት 22 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ በዓሉ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከላይ በተጠቀሱት መንገዶች እና ፕሮግሙ በሚካሄድበት በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ዙሪያ ተሽከርካሪን ማሳደርም ሆነ ለአጭርም ሆነ ለረጀም ሰዓት አቁሞ መሄድ ፈፅሞ የተከለከለ መሆኑንም ፖሊስ አሳስቧል፡፡
@Yenetube @Fikerassefa
12.9K viewsedited  08:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-29 22:13:01
በ19ኛው ክፍለ ዘመን በብሪታኒያ ወታደሮች ከኢትዮጵያ የተወሰደውን ጋሻ የሀገሪቷ መንግስት ጫና ተከትሎ ዛሬ የሚደረገዉ የጨረታው ሽያጭ እንዲሰረዝ ተደርጓል!

እንግሊዝ በ 1968 ከመቅደላ የዘረፈችዉ "የጦር ጋሻ" ዛሬ ሐሙስ ለአለም አቀፍ ጨረታ መቅረብን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት ጨረታዉ ተሰርዞ ወደ ትዉልድ ሀገሩ እንዲመለስ ደብዳቤ ፅፏል።እ.ኤ.አ በ 1868 በመቅደላ ጦርነት ወቅት የተዘረፈው የኢትዮጵያ ጋሻ ሐሙስ በኒዉካስል ታይን ላይ ለአለም አቀፍ ለጨረታ ክፍት እንደሚደረግ ካፒታል ዘግቦ ነበር።

ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዛሬ በሰጠዉ በመግለጫው የጨረታ ቤቱን እና የጋሻው ባለቤት ሽያጩን ለመሰረዝ እና "ወደ አገሩ ለመመለስ ድርድር ለመጀመር የወሰዱትን ጥበብ የተሞላበት ውሳኔ" በደስታ እንደሚቀበለዉ ገልጿል።

በቱሪዝም ሚኒስቴር ስር የሚንቀሳቀሰው ባለስልጣኑ ይህ ውድ ሀብት ወደ ትውልድ አገሩና ወደ ህጋዊ ባለቤቶቹ፣ የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት የሚመለስበትን ውጤት ለማስገኘት ጥረቴን እቀጥላለሁ ብሏል።

በኒውካስል ታይን የሚገኘው አንደርሰን እና ጋርላንድ የጨረታ ቤት ጋሻው ዛሬ የካቲት 21፤2016 ይካሄድ በነበረው “ጨርታ ዝርዝር ዉስጥ የጦር ጋሻዉን አካቷል” ለዚህም ለጋሻዉ ግምታዊ ዋጋዉ ከ1,000 እስከ 1,500 ዶላር አካባቢ መቀመጡ ታዉቋል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAseffa
13.2K views19:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-29 21:47:09
በሞተር ብስክሌት ላይ እስከ ሰኞ ገደብ ተጣለ

በአዲስ አበባ ከነገ አርብ የካቲት 22/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ እስከ ሰኞ የካቲት 25/2016 ዓ.ም እስከ ጠዋት 12:00 ሰአት ድረስ ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ፍጹም  የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አሳውቋል።

ቢሮው ክልከላው ለምን እንደተጣለ በግልፅ ያሳወቀው ነገር የለም።

ክልከላው የፀጥታ እና የትራፊክ ቁጥጥር የሚሰሩ አካላትን አያካትትም ተብሏል።

የሞተር ብስክሌት ባለንብረቶች ሆኑ አሽከርካሪዎች እስከ ተጠቀሰው ቀን ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ ቢሮው አሳስቦ ይህን መልእክት በሚተላለፉ አካላት ላይ እርምጃ ይወሰዳል ሲል አስጠንቅቋል።

ባለፈው ከአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ ጋር በተያያዘ ለቀናት የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሎባቸው እንደነበር ይታወሳል።

@Yenetube @Fikerassefa
13.3K viewsedited  18:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-29 14:00:12
ትሪፕ ኤክስ በአዳዲስ OFFER / አቅርቦት በአይነቱ ልዩ የሆነ እድል ይዞልዎት መጥቷል::

6% ክፍያ በመክፈል ወደ ሮማንያ ለስራ እንዲሁም፣

ከ3-6% ክፍያ በመክፈል ለጉብኝት ወደ:
ካናዳ
ጣልያን
አሜሪካ
ጀርመን
ፖላንድ
ስፔን እና
ወደ ተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት በመመዝገብ የጉዞ ህልምዎን በትሪፕ ኤክስ እውን ያድርጉ!

በተጨማሪም የተለያዩ ቢዝነስ ኢቬንቶች ላይ መታደም ለሚፈልጉ የማማከር እና የማዘጋጀት አገልግሎት እንሰጣለን፡፡

ትሪፕ ኤክስ ፍላጎትዎን ለማሳካት እነሆ አለው ይላል!

ይምጡና ይጎብኙን! Trust us to get you there!

አድራሻ፡ ሃያ ሁለት-ከጎላጉል አጠገብ ኖህ ህንጻ -5ኛ ፎቅ


ስልክ፡
0926389973
14.5K viewsedited  11:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-29 10:55:10 ጋና የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን በተመለከተ ጠንካራ ሕግ አጸደቀች!

የጋና ፓርላማ ከተመሳሳይ ፆታ ግንኙነቶች እና በዚህ ዙሪያ ከሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ጋር በተያያዘ በሚከሰሱ ሰዎች ላይ ጠንከር ባለ እስር የሚቀጣ ሕግ አጸደቀ።አዲሱ ሕግ በተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት ውስጥ መሆናቸውን የሚገልጹ እንዲሁም ሆነው የተገኙ ሰዎችን እስከ ሦስት ዓመት በሚደርስ እስር፣ ቡድኖችን የሚያቋቁሙ እና በገንዘብ የሚደግፉ እስከ አምስት ዓመት እስር እንዲቀጡ ያደርጋል።

የአገሪቱ ሕግ አውጪዎች የእስር ቅጣቱ ወደ ማኅበረሰብ አገልግሎት እና የምክር ድጋፍ እንዲቀየር የተደረገውን ጥረት ተቃውመው ውድቅ አድርገውታል።በአገሪቱ ሁለት ዋነኛ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተደገፈው እና ፓርላማው ያጸደቀው ይህ ሕግ ተግባራዊ የሚሆነው የጋናው ፕሬዝዳንት ናና አኩፎ-አዶ በፊርማቸው ሲያጸድቁት ነው።ፕሬዝዳንቱ ቀደም ሲል አብዛኛው የአገሪቱ ዜጎች የሚፈልጉት ከሆነ ሕጉን እንደሚያጸድቁት ተናግረው ነበር።

የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት በጋና ውስጥ ቀደም ብሎም ሕገወጥ ሆኖ በሦስት ዓመት እስር የሚያስቀጣ ነው።ሕጉ “በሰዎች መሠረታዊ መብት እና ነጻነት ላይ ከባድ አደጋን የሚደቅን ነው” ሲል ባለፈው ወር አምነስቲ ኢንተርናሽናል ተቃውሞውን አሰምቶ ነበር።የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት መብት ተቆርቋሪዎች አሁን የወጣው ሕግ ሰዎችን እና በዚህ ዙሪያ የሚሠሩ ማኅበራትን ለማሳደድ ስለሚውል አንዳንዶች ለመደበቅ ይገደዳሉ ብለዋል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
14.6K views07:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-28 16:50:54
የኮንስራክሽን ተረፈ ምርት ተንዶ የ20 አመት ወጣት ህይወቱ አለፈ

ዛሬ የካቲት 20 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 5:09 ሰዓት ላይ በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 13 አያት ሪል እስቴት በሚያስገነባዉ የቤት ግንባታ ላይ የኮንስትራክሽን ተረፈ ምርት ተንዶ ዕድሜዉ ሀያ ዓመት የሆነ የድርጅቱ ሰራተኛ ወዲያዉ ህይወቱ ማለፉ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት ባለሞያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለፋስት መረጃ ገለፁ።

የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የወጣቱን አስከሬን ከፍርስራሽ ዉስጥ አዉጥተዉ ለፖሊስ አስረክበዋል። በአዲስ አበባ በኮንስትራክሽን የስራ ላይ አደጋ በአንድ ወር ዉስጥ የዛሬዉን ጨምሮ የስድስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ስድስት ሰዎች ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
13.8K views13:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-28 13:59:38 በስድስት ወራት ውስጥ ብቻ በተከሰቱ የትራፊክ አደጋዎች 1 ሺህ 358 ሰዎች ህይወታቸው ተቀጥፏል ተባለ!

በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት 1 ሺህ 358 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን አጥተዋል ሲሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ ተናግረዋል፡፡

ሰሞኑን የተከሰተውን አደጋ ሳይጨምር በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት ብቻ የተመዘገበው ሞት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በቁጥር ደረጃ በ 514 የቀነሰ ቢሆንም የጉዳቱ ልክ አሁንም እጅግ አሳሳቢ መሆኑን መገንዘብ ይገባል ብለዋል፡፡2 ሺህ 672 ሰዎች ደግሞ በመኪና አደጋ ሳቢያ ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው እና ከ1 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ ውድመት መድረሱን ገልፀዋል፡፡

በሀገሪቱ የትራፊክ አደጋ መንስኤዎች ተብለው ከተጠኑ ዝርዝር ምክንያቶችም ከ60 በመቶ በላይ የሚሆኑ የትራፊክ አደጋዎች የሚደርሱት በአሽከርካሪዎች ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ከ20 በመቶ የማያንሱት ደግሞ ከተሸከርካሪዎች ብቃት ማነስ ምክንያት የሚደርሱ መሆናቸውን ገልጸው፤ እነዚህ ሁለት ምክንያቶች ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አመልክተዋል።

Via Bisrat FM
@YeneTube @FikerAssefa
13.8K views10:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-28 12:40:19
ፈረንሳዊው ጋዜጠኛ አንቷን ጋሊንዶ በቁጥጥር ሥራ የዋለው ከተሰጠው የዘገባ ፈቃድ ውጪ በሀገር ውስጥ ጉዳይ ዘገባ ለመስራት ሲንቀሳቀስ በመገኘቱ ነው ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ!

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ በሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።በመግለጫቸውም ጋዜጠኛ አንቷን ጋሊንዶ ለ37ኛው አፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ የዘገባ ሽፋን ለመስጠት ፈቃድ አግኝቶ ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱን አስታውሰዋል፡፡

ይሁን እንጂ ግለሰቡ የጋዜጠኝነት ሙያን ሽፋን በማድረግ አዲስ አበባ ከገባበት ቀን ጀምሮ ከመጣበት ዓላማ ፍጹም ተቃራኒ የሆኑ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን የሚሳዩ መረጃዎች መገኘታቸውን አንስተዋል፡፡ይህም ከመጣበት አላማ ውጪ በተለይም የኢትዮጵያን ውስጣዊ የፖለቲካ ጉዳዮችን የተመለከቱ መረጃዎችን ለመሰብሰብ ሲሞከር እንደነበር አብራርተዋል፡፡

በዚህም የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች እና አባላትን እንዲሁም የፖለቲካ ተሳትፎ አላቸው ያላቸውን ማህበራዊ አንቂዎችን ሲያነጋግር እንደነበር ገልጸዋል፡፡ግለሰቡ ወደ ኢትዮጵያ ከመጣበት ዋነኛ ዓላማ ውጪ በሀገሪቱ ውስጣዊ ጉዳይ ላይ ትኩረት በማድረግ መረጃዎችን ለመሰብሰብ ባደረገው ጥረት ተጠርጥሮ የካቲት 14 ቀን በቁጥጥር ስር ውሎ ጉዳዩ በፍርድ ቤት እየታየ መሆኑን አስገነዝበዋል፡፡

ግለሰቡ በ24 ሰዓታት ውስጥ ፍርድ ቤት መቅረቡንም ነው ሚኒስትር ዴዔታዋ ያስረዱት፡፡ለአፍሪካ ህብረት ዘገባ ፈቃድ የሚሰጠው ማንኛውም ጋዜጠኛ ከመጣበት ዓላማ ውጪ መስራት ህገ ወጥ እንደሆነ ጠቁመው÷ ይህም በየትኛውም ዓለም ያለ ሕግ መሆኑን አንስተዋል፡፡የግለሰቡን ጉዳይ በተለያየ መልኩ ከሙያው እና ከዜግነቱ ጋር በማገናኘት የሚሰራጩ መረጃዎች ትክክል አለመሆናቸውንም አረጋግጠዋል፡:


[FBC]
@YeneTube
13.5K views09:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ