Get Mystery Box with random crypto!

Yeka Abado Full Gospel Belivers'church

የቴሌግራም ቻናል አርማ yafgbchurch — Yeka Abado Full Gospel Belivers'church Y
የቴሌግራም ቻናል አርማ yafgbchurch — Yeka Abado Full Gospel Belivers'church
የሰርጥ አድራሻ: @yafgbchurch
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 208
የሰርጥ መግለጫ

Channal

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-22 04:26:05 ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች

መግቢያ


የዚህ መጽሐፍ ዓላማ:

ይህ መጽሐፍ ጳውሎስ ከእስር ቤት ሆኖ ከጻፋቸው አራቱ መልእክቶች ውስጥ አንዱ ነው:: (ሌሎቹ መጽሐፍት ኤፌሶን፤ ቆላስያስ እና ፊልሞና ናቸው)

ይህ ቤተክርስቲያን በአውሮፓ የመጀመሪያው ቤተክርስቲያን ነው::

በሐዋርያት 15:40-19:22 በጳውሎስ ሁለተኛው የወንጌል ጉዞ ላይ በህልሙ (በሐዋ 16:9) ወደ መቄዶንያ መተህ እርዳን የሚለውን ራዕይ ካየ በኃላ ነው የመጣው::

ፊልጲስዮስ በመቄዶንያ ግዛት ውስጥ የምትገኝ ወይም በአሁንዋ ሰሜናዊ ግሪክ ውስጥ ያለች ግዛት ናት::

የመጽሐፉ ጸሐፊ እራሱ ጳውሎስ ነው::
በዚህ መልዕክቱ:-

1. ስለሰጡት ስጦታ ሊያመሰግናቸው (ከነሱ ከተለየ በኃላ ስጦታ በተደጋጋሚ የላኩለት ከዚህ ቤተክርስቲያን ብቻ ነው (2ቆሮ 11:9 እና ፊል 4:10-20)

2. ሊያበረታታቸው

3. ሁልጊዜ በጌታ ደስ እንዲላቸው (ምንም እንኳን ከእስር ቤት የጻፈው መልዕክት ቢሆንም 16 ጊዜ ስለደስታ ጽፏል)
141 views01:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 07:10:46 የተወደዳችሁ

በቴሌግራም ቻናላችን በየቀኑ ከመጽሐፍ ቅዱስ 1ኛ እና 2ኛ ተሰሎንቄን ከ1ኛ ዬሐንስ መልዕክት በተለያዪ ርዕሰ ጉዳይ ቃል በቃል (verse by verse) ስናጠና
ቆይተናል ከነገ ሰኞ ጀምረን ደግሞ የሐዋርያው የጳውሎስ መልዕክትን ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎችን እናጠናል!!!

ተባረኩ!
154 views04:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 07:08:24 Watch "Mix - ዝናህ የገነነው Zinah Yegenew በአንተ ደስ ይለኛል Bante Des Yilegnal" on YouTube
https://youtube.com/playlist?list=RDPiq3Qfw-r1s&playnext=1
126 views04:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 15:35:06 Dr Siyum
238 viewsedited  12:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 08:46:40 የተወደዳችሁ ሰላማችሁ የበዛ ይሁን !

በዚህ ነሃሴ ወር 2014 ዓ.ም ከቤተእምነታችን በተላለፈልን መልዕክት መሰረት በግልም ይሁን በህብረት በምንጸልይበት ጊዜ

1ኛ) ስለ ቤተክርስቲያን መሪዎች፤ስለ አገር መሪዎች ፤ስለ ህዝባችን በደል በንስሃ እና በምልጃ

2ኛ) የእግዚአብሔርን ምህረት በመለመን

3ኛ) ስለ መንፈስ አንድነት

4ኛ) ቀጣዩ ዓመት የሰላምና የእረፍት ጊዜ እንዲሆንልን ወደ እግዚአብሔር አብዝተን የምንቀርብበት እንዲሆንልን
ከላይ ያሉትን ታሳቢ በማድረግ መጸለይና መኖር እንዲሆንልን ቤተክርስቲያንም ታሳስባለች፡፡

እግዚአብሔር ምድራችንን ይባርክ!
267 views05:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 07:40:10 ኢየሱስ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው

1ኛ ዮሐንስ 5: 18-21

18፤ ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን እንዳያደርግ፥ ነገር ግን ከእግዚአብሔር የተወለደው ራሱን እንዲጠብቅ ክፉውም እንዳይነካው እናውቃለን።

19 ከእግዚአብሔር እንደ ሆንን ዓለምም በሞላው በክፉው እንደ ተያዘ እናውቃለን።

20 የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።

21 ልጆች ሆይ፥ ከጣዖታት ራሳችሁን ጠብቁ።

ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ

1. ኃጢአትን እንዳያደርግ:- ለምን ሐጥያትን አያደርግም? ምክንያቱም ዘሩ በእርሱ ይኖራልና፤ ከእግዚአብሔርም ተወልዶአልና ኃጢአትን ሊያደርግ አይችልም።

2. ራሱን እንዲጠብቅ:- ሰው እራሱን እንዴት ይጠብቃል? በአእምሯችን መታደስ እንለወጥ እንጂ ይህንን ዓለም አንምሰል ነው ቃሉ የሚለን::

አእምሯችንም የሚታደሰው በቃሉና በመንፈስ ቅዱስ ስለሆነ ለቃሉ ጊዜ እንስጥ እናመንዥገው አእምሯችን ስራ አይፍታ በቃሉ እንሙላው::

3. ክፉውም እንዳይነካው እናውቃለን:- ልጅ ነንና እግዚአብሔር ስለሚጠብቀን ክፉ አይነካንም እኛ ለእርሱ ተቀድሰናልና በእኛ እርሱ ይታያል::

የክርስትና እምነታችን በአጭሩ ወይም በአንድ ጥቅስ:-

1. የእግዚአብሔር ልጅ እንደ መጣ፥

2. እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤

3. እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥

4. እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

5. እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።

የእግዚአብሔር ልጅ እንደመጣ ያወቀ የሚያውቅበትን ልብ የተቀበለው ከጌታ ነው የሚኖረውም እውነት በሆነው በልጁ ውስጥ ነው ዓለም በሞላው በክፉ ቢያዝም እኛ ግን እውነት በሆነው በእየሱስ ውስጥ እየኖርን ነው::

በዚህ 1ዮሐንስ ጥናታችንን ጨርሰናል::

የጌታ ጸጋ ይብዛልን!
246 viewsedited  04:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 08:34:35 ስለሌላው እንማልድ

1ኛ ዮሐንስ 5: 16-17

16፤ ማንም ወንድሙን ሞት የማይገባውን ኃጢአት ሲያደርግ ቢያየው ይለምን፥ ሞትም የማይገባውን ኃጢአት ላደረጉት ሕይወት ይሰጥለታል። ሞት የሚገባው ኃጢአት አለ፤ ስለዚያ እንዲጠይቅ አልልም።

17፤ ዓመፃ ሁሉ ኃጢአት ነው፥ ሞትም የማይገባው ኃጢአት አለ።

ማንም ወንድሙን ሞት የማይገባውን ኃጢአት ሲያደርግ ቢያየው፤ ምን ሲሆን? ኃጢአት ሲያደርግ ቢያየው እዚህ ላይ ነው እንግዲህ እስከአሁን ድረስ የተነገረን ቃል አገልግሎት ላይ የሚውለው:: እርስ በእርስ ተዋደዱ የሚለው:: እንዴት ብትሉኝ? ኃጢአት ሲያደርግ ወንድማችን ስናይ ለሌላ ሰው ነግረን በእንጸልይለት ሽፋን ሀሜት ውስጥ መግባት የለብንም::

የተባልነው እኛው እንድንጸልይ ነው ካየነው እንጸልይእንጂ አንንቀፍ ጌታ አምኖ የሰውን ጉድለት ሲያሳየን እንሸከም:: ዓመፃ ሁሉ ኃጢአት ነው፥ እርሱ እንዳለ ሆኖ እርስ በእርሳችን እንድንማልድ ጌታ ሊያስተምረን ፈልጎ ነው ከመማለድ ባለፈ ሰውየው ተመልሶ ከጌታው ጋር አስተካክሎ ሳለ እኛ የማንመለስበት አጋጣሚ ብዙ ነው ጌታ ግን የቱን ኃጥያት ብሎ ከንስሀ በኃላ ረስቶለታል ስለዚህ የጌታን ልብ እንያዝ ጎበዝ! እናም በተግባር የሆነ መዋደድ እንዋደድና እንሸከም ደግሞም ይቅር እንበል የወንድማችንን ገበናን ሸፍነን እንሸከም:: ይህ ወተት ከመጋት ወጥቶ አጥንት መቆርጠም ነው! ጌታም ይህንን ጸሎት ይሰማና ሞት የማይገባውን ኃጢአት ላደረጉት ሕይወት ይሰጥለታል! የሚገርመው ይሰጠዋል ሳይሆን ይሰጥለታል ስለ ጸላዩ ብሎ:: ስንቱን መርዳት እንችል ነበር?!

ሞት የሚገባው ኃጢአት አለ፤ ስለዚያ እንዲጠይቅ አልልም። ይህ ሞት የሚገባው ኃጥያት ምንድነው? መንፈስ ቅዱስን መሳደብ ነው ጌታም ነግሮናልና:: ለመንፈስ ቅዱስ እንጠንቀቅ!!

የጌታ ጸጋ ይብዛልን!
195 views05:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ