Get Mystery Box with random crypto!

ኢየሱስ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው 1ኛ ዮሐንስ 5: 18-21 18፤ ከእግዚአብሔር | Yeka Abado Full Gospel Belivers'church

ኢየሱስ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው

1ኛ ዮሐንስ 5: 18-21

18፤ ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን እንዳያደርግ፥ ነገር ግን ከእግዚአብሔር የተወለደው ራሱን እንዲጠብቅ ክፉውም እንዳይነካው እናውቃለን።

19 ከእግዚአብሔር እንደ ሆንን ዓለምም በሞላው በክፉው እንደ ተያዘ እናውቃለን።

20 የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።

21 ልጆች ሆይ፥ ከጣዖታት ራሳችሁን ጠብቁ።

ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ

1. ኃጢአትን እንዳያደርግ:- ለምን ሐጥያትን አያደርግም? ምክንያቱም ዘሩ በእርሱ ይኖራልና፤ ከእግዚአብሔርም ተወልዶአልና ኃጢአትን ሊያደርግ አይችልም።

2. ራሱን እንዲጠብቅ:- ሰው እራሱን እንዴት ይጠብቃል? በአእምሯችን መታደስ እንለወጥ እንጂ ይህንን ዓለም አንምሰል ነው ቃሉ የሚለን::

አእምሯችንም የሚታደሰው በቃሉና በመንፈስ ቅዱስ ስለሆነ ለቃሉ ጊዜ እንስጥ እናመንዥገው አእምሯችን ስራ አይፍታ በቃሉ እንሙላው::

3. ክፉውም እንዳይነካው እናውቃለን:- ልጅ ነንና እግዚአብሔር ስለሚጠብቀን ክፉ አይነካንም እኛ ለእርሱ ተቀድሰናልና በእኛ እርሱ ይታያል::

የክርስትና እምነታችን በአጭሩ ወይም በአንድ ጥቅስ:-

1. የእግዚአብሔር ልጅ እንደ መጣ፥

2. እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤

3. እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥

4. እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

5. እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።

የእግዚአብሔር ልጅ እንደመጣ ያወቀ የሚያውቅበትን ልብ የተቀበለው ከጌታ ነው የሚኖረውም እውነት በሆነው በልጁ ውስጥ ነው ዓለም በሞላው በክፉ ቢያዝም እኛ ግን እውነት በሆነው በእየሱስ ውስጥ እየኖርን ነው::

በዚህ 1ዮሐንስ ጥናታችንን ጨርሰናል::

የጌታ ጸጋ ይብዛልን!