Get Mystery Box with random crypto!

ስለሌላው እንማልድ 1ኛ ዮሐንስ 5: 16-17 16፤ ማንም ወንድሙን ሞት የማይገባውን ኃጢአት ሲ | Yeka Abado Full Gospel Belivers'church

ስለሌላው እንማልድ

1ኛ ዮሐንስ 5: 16-17

16፤ ማንም ወንድሙን ሞት የማይገባውን ኃጢአት ሲያደርግ ቢያየው ይለምን፥ ሞትም የማይገባውን ኃጢአት ላደረጉት ሕይወት ይሰጥለታል። ሞት የሚገባው ኃጢአት አለ፤ ስለዚያ እንዲጠይቅ አልልም።

17፤ ዓመፃ ሁሉ ኃጢአት ነው፥ ሞትም የማይገባው ኃጢአት አለ።

ማንም ወንድሙን ሞት የማይገባውን ኃጢአት ሲያደርግ ቢያየው፤ ምን ሲሆን? ኃጢአት ሲያደርግ ቢያየው እዚህ ላይ ነው እንግዲህ እስከአሁን ድረስ የተነገረን ቃል አገልግሎት ላይ የሚውለው:: እርስ በእርስ ተዋደዱ የሚለው:: እንዴት ብትሉኝ? ኃጢአት ሲያደርግ ወንድማችን ስናይ ለሌላ ሰው ነግረን በእንጸልይለት ሽፋን ሀሜት ውስጥ መግባት የለብንም::

የተባልነው እኛው እንድንጸልይ ነው ካየነው እንጸልይእንጂ አንንቀፍ ጌታ አምኖ የሰውን ጉድለት ሲያሳየን እንሸከም:: ዓመፃ ሁሉ ኃጢአት ነው፥ እርሱ እንዳለ ሆኖ እርስ በእርሳችን እንድንማልድ ጌታ ሊያስተምረን ፈልጎ ነው ከመማለድ ባለፈ ሰውየው ተመልሶ ከጌታው ጋር አስተካክሎ ሳለ እኛ የማንመለስበት አጋጣሚ ብዙ ነው ጌታ ግን የቱን ኃጥያት ብሎ ከንስሀ በኃላ ረስቶለታል ስለዚህ የጌታን ልብ እንያዝ ጎበዝ! እናም በተግባር የሆነ መዋደድ እንዋደድና እንሸከም ደግሞም ይቅር እንበል የወንድማችንን ገበናን ሸፍነን እንሸከም:: ይህ ወተት ከመጋት ወጥቶ አጥንት መቆርጠም ነው! ጌታም ይህንን ጸሎት ይሰማና ሞት የማይገባውን ኃጢአት ላደረጉት ሕይወት ይሰጥለታል! የሚገርመው ይሰጠዋል ሳይሆን ይሰጥለታል ስለ ጸላዩ ብሎ:: ስንቱን መርዳት እንችል ነበር?!

ሞት የሚገባው ኃጢአት አለ፤ ስለዚያ እንዲጠይቅ አልልም። ይህ ሞት የሚገባው ኃጥያት ምንድነው? መንፈስ ቅዱስን መሳደብ ነው ጌታም ነግሮናልና:: ለመንፈስ ቅዱስ እንጠንቀቅ!!

የጌታ ጸጋ ይብዛልን!