Get Mystery Box with random crypto!

ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች መግቢያ የዚህ መጽሐፍ ዓላማ: ይህ መጽሐፍ ጳውሎስ ከእስር ቤት ሆኖ ከ | Yeka Abado Full Gospel Belivers'church

ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች

መግቢያ


የዚህ መጽሐፍ ዓላማ:

ይህ መጽሐፍ ጳውሎስ ከእስር ቤት ሆኖ ከጻፋቸው አራቱ መልእክቶች ውስጥ አንዱ ነው:: (ሌሎቹ መጽሐፍት ኤፌሶን፤ ቆላስያስ እና ፊልሞና ናቸው)

ይህ ቤተክርስቲያን በአውሮፓ የመጀመሪያው ቤተክርስቲያን ነው::

በሐዋርያት 15:40-19:22 በጳውሎስ ሁለተኛው የወንጌል ጉዞ ላይ በህልሙ (በሐዋ 16:9) ወደ መቄዶንያ መተህ እርዳን የሚለውን ራዕይ ካየ በኃላ ነው የመጣው::

ፊልጲስዮስ በመቄዶንያ ግዛት ውስጥ የምትገኝ ወይም በአሁንዋ ሰሜናዊ ግሪክ ውስጥ ያለች ግዛት ናት::

የመጽሐፉ ጸሐፊ እራሱ ጳውሎስ ነው::
በዚህ መልዕክቱ:-

1. ስለሰጡት ስጦታ ሊያመሰግናቸው (ከነሱ ከተለየ በኃላ ስጦታ በተደጋጋሚ የላኩለት ከዚህ ቤተክርስቲያን ብቻ ነው (2ቆሮ 11:9 እና ፊል 4:10-20)

2. ሊያበረታታቸው

3. ሁልጊዜ በጌታ ደስ እንዲላቸው (ምንም እንኳን ከእስር ቤት የጻፈው መልዕክት ቢሆንም 16 ጊዜ ስለደስታ ጽፏል)