Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-ስፖርት ተመራጭ

የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvah_sport123 — TIKVAH-ስፖርት ተመራጭ T
የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvah_sport123 — TIKVAH-ስፖርት ተመራጭ
የሰርጥ አድራሻ: @tikvah_sport123
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.66K
የሰርጥ መግለጫ

ለሀገራችን እድገት እንተጋለን
@TIKVAH_Sport123
ከፈለጉ 👇
@keld_be_amargna
ከእሁድ እስከ እሁድ ፈጣን የመረጃ ምንጭ!
════════════
➮የሃገር ቤት ትኩስ ትኩስ መረጃዎች
➮የአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች ሙሉ መረጃ
➮ቁጥራዊ መረጃዎች እና ዳሰሳዎች
➮ጨዋታዎችን በቀጥታ ከየስታዲየሙ
➮የተለያዩ ስፖርታዊ ታሪኮች
ስፖርት እወዳለው በጣምምም
2012 ሰኔ 12

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-06-23 11:58:03
ሞሀመድ ሳለህ ላደገበት መንደር !

ግብፃዊው ኮከብ የፊት መስመር ተጫዋች ለትውልድ መንደሩ የተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል ።

ሳላህ ተወልዶ ላደገበት ናግሪግ መንደር ሆስፒታል ፣ ትምህርት ቤት እና የወጣቶች ማዕከል አስገንብቶ አስረክቧል ።

ሳላህ በችግር ላይ ለሚገኙ ቤተሰቦቹ በየወሩ 3,500 ዶላር ድጎማ እንደሚያደርግ ተዘግቧል ።

ሳላህ የኮቪድ ወረርሽኝ በተከሰተበት ወቅት በሺዎች የሚቆጠር የምግብ አቅርቦት ከ 500ሺህ ዶላር በላይ መለገሱ ተነግሮለታል ።

ሳለህ በተለይም በ 2019 በግብፅ ለካንሰር ታማሚዎች የሚውል 2.5 ሚልዮን ዶላር እርዳታ ማድረጉ ተገልጿል ።

@TIKVAH_Sport123
488 views08:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 11:57:09
|| ሊድስ አርሰናልን ይጠብቃል !

ሊድስ ዩናይትድ ባርሳ ላይ ያለው ትዕግስት አልቋል ። ከረጅም ጊዜ በፊት ከተጫዋቹ ጋር ስምምነት ቢኖረውም እስካሁን ግን ምንም ነገር ማቅረብ አልቻለም ። አሁን የባርሳን ሁኔታ መጠበቅ ሰልችቷቸዋል ።

ራፊንሃ ቅድሚያ የሚሰጠው ባርሳ ቢሆንም ሊድስ ከዝርዝሩ አስወጡቷቸዋል ። አርሰናል በአሁን ሰአት የተሻለ ቦታ ላይ ይገኛል እና ድርድሩ በጥሩ መልኩ እየተካሄደ ነው ። [ ሙንዶ ዲፖርቲቮ ]

@TIKVAH_Sport123
417 views08:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 11:56:18
የኦስማን ዴምቤሌ ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጫዋች ኦስማን ዴምቤሌ በያዝነው ወር መጨረሻ ከካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ጋር ያለው ኮንትራት የሚጠናቀቅ ይሆናል ።

ኦስማን ዴምቤሌ ስሙ ከቼልሲ ጋር ቢያያዝም በወርሀ ታህሳስ በባርሴሎና ቀርቦለት የነበረውን የውል ማራዘሚያ ኮንትራት ከዣቪ ጋር ከተነጋገረ በኋላ ለመቀበል መዘጋጀቱ ተዘግቧል ።

ባርሴሎና ኮንትራቱን ሚያድስ ከሆነ አርሰናል ራፊናን ለማስፈረም አሪፍ ይሆንለታል።

@TIKVAH_Sport123
408 views08:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 21:07:32
ዋልያው ፈርዖኑን ረቷል !

በኮትዲቫር አዘጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ በምድብ አራት ላይ በቢንጉ ብሄራዊ ስታዲየም በተካሄደ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከ ግብፅ ጋር ያደረገውን ጨዋታ ከጨዋታ ብልጫ ጋር 2 - 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል ።

የዋልያዎቹን የማሸነፊያ ግቦች ዳዋ ሁቴሳ እና አምበሉ ሽመልስ በቀለ አስቆጥረዋል ።

ዋልያዎቹ ከ እ.ኤ.አ 1989 በኋላ በኋላ የግብፅ ብሄራዊ ቡድንን ማሸነፍ ችሏል ።

የዛሬው ውጤት ተከትሎ ሀገራችን በሶስት ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች ።

@TIKVAH_Sport123
719 views18:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 21:05:56
የምድብ የደረጃ ሰንጠረዝ
@TIKVAH_Sport123
578 views18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 17:13:21
አርሰናል ቡካዮ ሳካ በዚህ ክረምት የኮንትራት ማራዘሚያውን እንደሚፈርም ተስፋ አላቸው።

@TIKVAHSport123
587 views14:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 17:11:37
በኳታር አዘጋጅነት ከሚካሄደው የአለም ዋንጫ አስቀድሞ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ህዳር 4 የሚቋረጥ ሲሆን የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በውድድሩ ላይ ህዳር 12 የሚያከናወኑ ይሆናል ።

የእንግሊዝ እግር ኳስ ፌድሬሽን ህዳር 3 እና 4 በሚደረጉ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች በተለምዶ " ቢግ 6 " የሚባሉ ክለቦች ለእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድኑ ጥቅም ሲባል እርስ በእርስ እንዳይገናኙ ይፋዊ ጥያቄ ማቅረቡ ተዘግቧል ።

@TIKVAH_Sport123
540 views14:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-06 21:51:34
መሐመድ ሳላህ ሀገሩ ከኢትዮጵያ ጋር በምታደርገው ጨዋታ እንደማይሰለፍ ተገለጸ

በአሠልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንም ትናንትና በማላዊ ባደረገው ጨዋታ ሁለት ለአንድ ተሸንፏል፡፡ የማላዊ ብሔራዊ ቡድንም ሆነ የኢትዮጵያ አቻው ያስቆጠሯቸው ግቦች በፍጹም ቅጣት ምት የተገኙ ናቸው፡፡
TIKVAH_Sport123
519 views18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-06 21:50:28
" ለሪያል ማድሪድ ኩራት ፈጥሯል "

የሪያል ማድሪዱ ፕሬዝዳንት ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግን ለማሸነፍ ሪያል ማድሪድ የተጓዘበት መንገድ ለሎስ ብላንኮዎቹ ኩራት እንደፈጠረ ገልፀዋል ።

ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ ሲናገሩ " ሪያል ማድሪድ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግን ለማሸነፍ የተጓዘበት መንገድ ለሪያል ማድሪድ ኩራት ከመፍጠርም አልፎ ጥሩ ጨዋታ የሚወዱ ሁሉም ደጋፊዎች በፍቅር እንዲወድቁ ያደረገ ነው " ሲሉ ተደምጧል ።

@TIKVAH_Sport123
489 views18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 11:04:32
" የዘረኝነት ጥቃት ሲደርስብኝ እርምጃ አይወስዱም "

የቦርሲያ ዶርትሙንዱ እንግሊዛዊ አማካይ ጁድ ቤሊንግሀም በጀርመን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የዘረኝነት ጥቃት ሲደርስበት የጀርመን እግር ኳስ ፌድሬሽን እርምጃ እንደማይወስድ ገልጿል ።

ጁድ ቤሊንግሀም ሲናገር " የጀርመን እግር ኳስ ፌድሬሽን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የዘረኝነት ጥቃት ሲደርስብኝ እርምጃ አይወስዱም ነገር ግን ዳኞችን ከተቸው በፍጥነት እርምጃ ይወሰድብኛል " ሲል ተደምጧል ።

@TIKVAH_Sport123
572 views08:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ