Get Mystery Box with random crypto!

ሰው መሆን...

የቴሌግራም ቻናል አርማ tibebnegni — ሰው መሆን...
የቴሌግራም ቻናል አርማ tibebnegni — ሰው መሆን...
የሰርጥ አድራሻ: @tibebnegni
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 553
የሰርጥ መግለጫ

ሰው ከመሆን በላይ ምን አለ ?
መልካም እንሁን ፡፡
ሟች መሆናችንን እያሰብን እንኑር
0923983389
@sam2127

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-05-04 20:20:46 5. VIP 4
* ይህ ደረጃ አባሉ 10,000 ብር ከፍሎ የሚሰጠው ደረጃ ነው።
* በቀን ክሊክ የሚያደርጋቸው 17 ስራዎችን ነው።
* ለአንዱ ስራ 18 ብር ይከፈለዋል።
* በቀን 306 ብር, በወር 9,180 ብር ያገኛል።
* ከአንድ ጊዜ በላይ ብር ማውጣት ይችላል።

6. VIP 5
* ይህ ደረጃ አባሉ 30,000 ብር ከፍሎ የሚሰጠው ደረጃ ነው።
* በቀን ክሊክ የሚያደርጋቸው 38 ስራዎችን ነው።
* ለአንዱ ስራ 25 ብር ይከፈለዋል።
* በቀን 905 ብር, በወር 28,500 ብር ያገኛል።
* ከአንድ ጊዜ በላይ ብር ማውጣት ይችላል።

ከዚህ በተጨማሪ ሁሉም ፖኬጆች የ ሪፈራል (Invitation ) አዋርድ አላቸው ይሄም እስከ ሶስት ደረጃ ይሄዳል።

ባሁኑ ሰአት ቢዝነሱ ገና ሀገር ውስጥ በመታወቅ ላይ ያለ በመሆኑ ብዙዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ህይወታቸውን የሚቀይር ገቢ እያገኙበት ይገኛሉ

ከታች ባለው ሊንክ ገብተው መጀመር ይችላሉ
https://fias777.com/#/pages/register?invite_code=JY4jgVUR&t=1651659645281

➲ ስልክቁጥር ሲያስገቡ ከ 9 ይጀምሩ
➲ Verification Code ሚለው ላይከጉን ቦክሱ ውስጥ ያለውን ፅሁፍ ያስገቡ


በነዚህ የፈለጉትን መረጃ ማግኘት ይችላሉ

Remember
➲ ያለምንም ክፍያ መጀመር ይቻላል
➲ paid marketer ለመሆን በ 1000 ብር መጀመር ይቻላል
➲ በአሁኑ ሰአት 2 ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በመቶ ሺዎች እያገኙ ያሉ ሰዎች አሉ

Dont miss the opportunity !
በነዚህ የፈለጉትን መረጃ ማግኘት ይችላሉ

➲ 0975361399
➲ fias.worldbusiness.work
➲ https://t.me/fiaseth - join
193 views17:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 20:20:46
ብዙዎች ባሁኑ ሰአት በስልካቸው ብቻ በሺዎች ብሎም መቶሺዎችን እያገኙበት ያለ ስራ

FIAS

በሀገራችን በቅርቡ የገባ እና በኮሚሽን የሚሰራ የማስታወቂያ ድርጅት ነው።
* ከተለያዩ የሶሻል ሚዲያ ኔትዎርኮች ጋር ይሰራል።

በቀን ውስጥ የተለያዩ ስራዎችን ለተመዘገቡ አባላቶቹ ይሰጣል። ስራዎቹ እጅግ በጣም ቀላል ናቸው። ክሊክ ማድረግ ብቻ ነው። በዛ ቢባል 5 ዲቂቃ ቢወስዱ ነው። አንድ አባል የሚሰጠው የስራ ብዛትና የሚያገኘው ብር እንደ ደረጃው ይለያያል። ደረጃዎቹ VIP-0, VIP-1, VIP-2, VIP-3, VIP-4, & VIP-5 ናቸው።

1. VIP 0
* አንድ አባል ገና እንደተመዘገበ የሚሰጠው ደረጃ ነው።
* በቀን ክሊክ የሚያደርጋቸው 3 ስራዎችን ብቻ ነው።
* ለአንዱ ስራ 5 ብር ይከፈለዋል።
* በቀን 15.00, በወር 450.00, ይሰራል
* ብር ለማውጣት አፕግሬድ ያደርጋል።


2. VIP 1
* ይህ ደረጃ አባሉ 1,000 ብር ከፍሎ የሚሰጠው ደረጃ ነው።
* በቀን ክሊክ የሚያደርጋቸው 4 ስራዎችን ነው።
* ለአንዱ ስራ 6 ብር ይከፈለዋል።
* በቀን 24 ብር, በወር 724.00 ብር ያገኛል።
* ከአንድ ጊዜ በላይ ብር ማውጣት ይችላል።

3. VIP 2
* ይህ ደረጃ አባሉ 3,000 ብር ከፍሎ የሚሰጠው ደረጃ ነው።
* በቀን ክሊክ የሚያደርጋቸው 6 ስራዎችን ነው።
* ለአንዱ ስራ 16 ብር ይከፈለዋል።
* በቀን 84 ብር, በወር 2,520 ብር ያገኛል።
* ከአንድ ጊዜ በላይ ብር ማውጣት ይችላል።

4. VIP 3
* ይህ ደረጃ አባሉ 6,000 ብር ከፍሎ የሚሰጠው ደረጃ ነው።
* በቀን ክሊክ የሚያደርጋቸው 11 ስራዎችን ነው።
* ለአንዱ ስራ 16 ብር ይከፈለዋል።
* በቀን 176 ብር, በወር 5,280 ብር ያገኛል።
* ከአንድ ጊዜ በላይ ብር ማውጣት ይችላል።
170 views17:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-30 15:36:21 *ምን አለበት**** (ሳሙኤል አዳነ)
     አሁን ምን አለበት ...
 ሰው እንዳሻው ቢኖር
    በራሱ ዳር ድንበር ፣
በልበ ጥፉዎች
       ልብ ባይሰበር ።

እውነት ምን አለበት ...
    ሜዳውን ፈልጎ ዳገቱን ለወጣ፣
ሌላ መሰናክል
      ሌላ እክል ባልመጣ ።
ምን አለበት
      ሰው ከገንዘብ በላይ
ለፍቅር ቢታደል፣
   በምንዝር አለቃ ፍትህ ባይጓደል ።
ቢቻል ለፈጣሪ ባይሆን ለህሊና፣
     ምናል  ይሄ ትውልድ  ለክፋት ባይቀና።

እውነት ምን አለበት ...
        በውዥንብር አለም
ግራ ባይገባ፣
ቁማር ባይጫወት
       ሰው ከግዜሩ ጀርባ ።

ምን አለበት...
       ላዳም የተሰጠው
የማፍቀር  ልቦና ።
        ዛሬም በዚህ ጊዜ ቀጥሎ ቢፀና።

 እውነት ምናለበት ...
   ሰውን በ ሰውነት
              ሁሉ ባከበረ ፣
    ግን በሚል አንድምታ
               ተቃርኖ ባልኖረ  ።
.....
ይገርመኛል ....
    ሰው በትምህርት አለም
              ጎልቶ እየዘመነ ፣
     በጭላንጭል እውቀት
                በራሱ መስተዋል
                  እየተማመነ ፣
     ከጥቁር ሀሳብ ጋር
                አብሮ እየዳመነ ፣
    ትናንትን ተወና
               የባቶችን ፀጋ
                የበረከቷን ቀን ፣
      በጦር አውድማ ላይ
        ተጨንቆ  እየዋለ
         ያድራል በሰቀቀን ..

እና ምን አለበት
      ሰው መነሻውን ቢያቅ
                  ትናንትን በይረሳ ፣
       በአምላክ ፍጡር ላይ
                   እጁን ባያነሳ ፣
    አውነት ምን አለበት
             በአባቶች ልቦና ፤
             በአባቶች እግር ፤
             መራመድ ቢበጀው ፣
ይሄን ጭንቅ ጊዜ
             በጥበብ ቸሻግሮ
              በፍቅር ቢዋጀው።

ምን አለበት ??????????......
 
07/09/2011
 ከምሽቱ 2:45
አ.አ
@TIBEBnegni
@sam2127




            



             

          
              
  
               



 
194 views12:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-13 02:01:39 ” ማንም ሰው ሌላውን ሰው በዘሩ እና በቆዳው ቀለም ወይም በሃይማኖቱ እንዲጠላ ሆኖ አልተወለደም
ሰዎች መጥላትን ተምረውት ነው ።
የሰው ልጅ ጥላቻን ከተማረ ፍቅርንም መማር ይችላል ።
እንደውም ፍቅር ለሰው ልጅ ተፈጥሮ ከጥላቻ ይልቅ ቅርብ ነው ።

@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
302 views23:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-13 02:00:38 *የልብ ቋንቋ*

የህይወት ጣዕሙ የጠፋባቸው ሰዎች አሉ፤በየዕለቱ ተመሳሳይ ህይወት የሚኖሩና በህይወታቸው ውስጥ አዲስ ክስተት አጥተው ስልቹ የሆኑ ሰዎች ።

ዘወትር ተመሳሳይህይወት መግባትና መዉጣት ፣መብላትና መጠጣት ..ብቻ አዲስ ህይወት የሌለበት ስልቹ አለም።

እነዚህ ሰዎች ህይወትን በማሰብ (አእምሮ) ብቻ የሚኖሯት ሰዎች ናቸው።

ምክንያቱን የሰው ልጅ የልብ ቋንቋ ካልገባው በአእምሮ ብቻ ከኖረ ህይወት ትርጉም የሌለባት ባዶ ስለምትሆን ህይወትን በአእምሮ ሳይሆን በልብ ኑሯት ፤ ህይወታችሁን በልብ ቋንቋ ስትመሯ አእምሯችሁ ታላቅ ተፈጥሮን ያሳያችኧል ።
በአእምሯችሁ ስትኖሩ ፓለቲከኛ፣ዘረኛ፣ አክራሪ.......ወ.ዘ.ተ ትሆናላችሁ ፤ በልባችሁ ስትኖሩ ግን መንፈሳዊ ትሆናላችሁ።

በልባችሁ ስትኖሩ የህይወት ጣእሙ ይገባችኧል፤ የፍቅር ሙቀቱ ይሰማችኧል።

ተልእኳችሁን ስታውቁና በተሰጥኦዋችሁ ስትኖሩ የህይወታችሁ ገዢ ሀይል ከልባችሁ ይመነጫል።
አእምሯችሁም የልባችሁ ታዛዥ ይሆናል።
ተሰጥኦዋችሁን ፈልጉ ራሳችሁን ፈልጉ አግኙትም።
የዚያን ጊዜ ህይወታችሁ ከአሰልቺነት ወጥቶ በደስታ ይሆናል። "
283 views23:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-24 21:55:58 ኑሮ እና ዋና

መዋኘት የሚችል ሰው በውሃ ላይ የመንሳፈፍ ጥበቡን በደንብ ያውቀዋል። ውሃ ላይ ለመንሳፈፍ ጠንካራ መሆንን አይጠይቅም። ይልቅ ውሃ ደግ ሆኖ ከመስመጥ የሚታደገን ፈታ ብለን ስንጫወትለት ብቻ ነው። ውሃ ግትር ሰው አይወድም፤ እጅ እና እግሩን ከማያፍታታ ግትር ጋር ውሃ ልጫወት አይልም። በጉልበት እንሳፈፋለው ለሚል ሰውም ውሃ እርህራሄ የለውም።እኔ በግሌ ውሃ ላይ እምብዛም ድፍረት አለነበረኝም። ዋናን ከልጅነቴ ስላልተማርኩት፤ ካደግኩኝ በኋላ መማሩ አስፈርቶኝ፤ ለረጅም ጊዜ አቆይቼው ነበር። ከጊዜ በኋላ ግን ፍራቻዬን ወደዳር አድርጌ ከወሃ ጋር በጥቂቱም ቢሆን ለመስማማት ችያለው። እናም ወሃ ሳይ ሁሌም ትዝ የሚለኝን አባባል ላካፍላችሁ ወደድኩኝ…..

አለን ዋትስ የተባለ አንድ ምሁር በአንድ ወቅት እንዲህ ሲል ሰምቸው ነበር ” እምነት ልክ እንደዋና ነው። ዋናተኛ ከውሃው ላይ ለመንሳፈፍ ከፈለገ፤ እጁን ዘርጋ አድርጎ በነጻነት በውሃው ላይ ይወራጫል እንጂ፤ ላለመስመጥ ሲል ዉሃውን ልጨብጥ አይልም። ውሃውን ልጨብጥ ብሎ ግትር የሚል ሰው እጣ ፋንታው መስመጥ ብቻ ነው፤ በውሃ ላይ ለመንሳፈፍ ምንም ነገር መጨበጥ የለብንም ፤ ዋና መዋኘት እና ህይወትን መኖር በጣም ተመሳሳይነት አላቸው”

“To have faith is to trust yourself to the water. When you swim you don’t grab hold of the water, because if you do you will sink and drown. Instead you relax, and float”.-Alan Watts

እናም ሁል ግዜ ውሃ ሳይ ትዝ የሚለኝ ይህ አባባል ሆነ። ብዙዏቻችን በህይወት ባህር ውስጥ የምንሰምጠው፤ ከኑሮ ጋር በቀላሉ መንሳፈፍን ስላለመድን ነው። እርግጥም ኑሮ እንደዋና ፈታ ብለው የሚኖሩት ባህር ነው። ግትር መሆን ውሃውን ለመጨበጥ እንደመሞከር ይሆናል። በህይወታችን ወስጥ በእኛ ቁጥጥር ስር የሆኑ ነገሮች አሉ፤ ሌሎች ከእኛ ቁጥጥር ውጪ የሆኑ ደግሞ እጅግ ብዙ ነገሮች ይኖራሉ። በኑሮ ውስጥ መስመጥ የሚከሰተው ታዲያ፤ ከእኛ ቁጥጥር ወጪ የሆኑ ነገሮች ላይ ግትርነታችንን ለማሳየት ስንሞክር ነው። መለወጥ የማንችለውን ነገር በጉልበት ለመለወጥ ስንሞክር፤ የመዋኘት ጥበቡ ጠፍቶናል ማለት ነው።

አንድ ዋናተኛ ከሆዱ እየተሳበ እጅ እና እግሩን እያወራጨ ወደፊት ካልሄደም የመስመጥ እድሉ ሰፊ ነው። ኑሮም ላይ እንደዛው ትላንት ከቆምንበት ቦታ ካልተንቀሳቀስን፤ ውሃ ላይ እንደመቆም ይከብደናል። የሚገርመው የህይወት ሚስጢር በየተፈጥሮ ገንባር ላይ ተጽፎ መገኘቱ ነው፤ እርግጥ ነው ሶስተኛ አይን ኖሮት ላስተዋለው ሰው ብቻ የሚገለጥ ሚስጢር ነው።

ሌላው ብዙዏቻችን የሚያሰምጠን ዋነኛው ምክንያት ለለውጥ ያለን አመለካከት ነው። አሁንም ከግትረነት ጋር የተያያዘ ነው። ለውጥ ምንም አይነት ይሁን ማስፈራቱ አይቀርም። ከማላውቀው መላዕክ የማላውቀው ሰይጣን ይሻላል አይነት ነገር ነው። ህይወት ወደድንም ጠላንም ባልታሰቡ ስጦታዎች የተሞላች ነች። እንደ ዋናተኛው በእምነት ፈታ ብለን ካልተንሳፈፍን በፍጹም ከለውጥ ጋር ተግባብተን ለመኖር አይቻለንም። #relax #beflexible እምነታችንን አስቀድመን ፤ ከጭንቀት ተላቀን፤ ከጠባብ አስተሳሰብ ወጥተን፤ ከጊዜው ጋር መለዋወጡን ልምድ አድርገን መኖር ከቻለን በቀላሉ ለመንሳፈፍ ይቻለናል።
አቤል ብርሀኑ


@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
343 views18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-24 21:53:08 ባልንጀሮቻችሁን ባያችሁ ቁጥር ራሳችሁን ተመልከቱ " አሉ ጃፓናዊው መምህር ።

" ግን እንደሱ ማድረጉ ራስ ወዳድነት አይሆንም ? "- አንደኛው ተማሪ ያቸው ጠየቀ ። - " ምክንያቱም ሁልጊዜ የምናተኩረው በራሳችን ላይ ከሆነ ፥ ሌሎች ሰዎች የያዙአቸውን መልካም እሴቶች ለማስተዋል እድል እናጣለን ። "

" አንተ እንዳልከው ሌሎች ሰዎች የያዙአቸውን መልካም እሴቶች መመልከት የምንችል ቢሆን እንዴት ደግ ነበር ! " መለሱ መምህር ። - ቀጠሉና " እውነታው ግን አንተ ካልከው በተቃራኒው ነው ።

.. ሌሎች ሰዎችን ባየን ቁጥር የምንመርጠው እንከኖቻቸውን ነው ። የሌላኛውን ሰው ክፋ ገፅታ ለማግኘት የቻልነውን ያህል የምንባትለው ከእኛ የባሰ እንዲሆን ስለምንፈልግ ነው ። ስሜታችንን ሲጎዳን ይቅርታ ልናደርግለት የሚከብደንም የራሳችን ጥፋት ይቅር ያስብላል ብለን ስለማናምን ነው ።የምናውቃቸውን ጦረኛ ቃላት እያፈናጠርን እናቆስለዋለን ።

ይህን የምናደርገው እውነታውን ከራሳችን ለመደበቅ ስለምንፈልግ ነው ። ...ማንም ሰው ምን ያህል ተሰባሪ ፥ ምን ያህል ስንጥቅጥቃችን የበዛ ፥ ሽንቁራችን የጎደጎደ መሆኑን እንዳያይብን ስንል ጠቃሚ እንደሆንን አድርገን እናስመስላለን ።

ለዚያም ነው ወዳጅህን በፈረድክ ፥ ሌላውን ሰው በበየንክ ቁጥር በትክክል ፍርድ ላይ ያለኸው ራስህ መሆንህንም ማወቅ የሚጠቅምህ ።

ውብ አሁን

@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
272 views18:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-04 18:43:21 “As A Man Thinketh” -By James Allen

ክፍል

የአስተሳሰባችን ተጽዕኖ”
(Effect of Thought on Circumstances.)

ጭንቀት እና መከራ ትክክለኛ ያልሆነ አስተሳሰብ ውጤቶች ናቸው። ሰው ከውስጣዊ ማንነቱ ጋር አብሮ መሄድ ሲያቅተው፤ በሰብዓዊ ህግ ስር ተገዝቶ መኖር ሲሳነው የመከራን ቀንበር ይሸከማል። የጭንቀት ማብቂያው ነፍስን ማጽዳት ነው፤ አይምሮን የሚያጎድፉ ነገሮችን ሁሉ ማስወገድ። መንፈሱ ንጹህ የሆነ ሰው ጭንቀት አያደፍረውም። ወርቅ ንጹህ ወርቅ እስኪሆን ድረስ በእሳት ይፈተናል እንጂ፤ ንጹህ ወርቅ ከሆነ ባኋላ በእሳት ብናቀልጠው ዋጋ የለውም። ልክ እንደ ንጹህ ወርቅም፤ በመንፈሱ ንጹህ የሆነ ሰው በመከራ እና ጭንቀት ከልክ በላይ አይፈተንም።

ሰው ከአይምሮው ጋር ሰላም ሲኖረው መልካም ሁኔታዎችን በዙሪያው ይፈጥራል፤ ከራሱ ጋር ሰላም መፈጠር ሲሳነው ግን ለመጥፎ አጋጣሚዎች እራሱን ያጋልጣል። የትክክለኛ አስተሳሰብ መገለጫ ሰላማዊ መሆን ሲሆን ደስተኛ ያልሆነ ወይም ዝብርቅርቅ ያለ ኑሮ ደግሞ ትክክለኛ ያልሆነ አስተሳሰብ መለያ ነው። ሰው የተባረከ፤ ነገር ግን ድሃ ሊሆን ይችላል፤ ወይም ደግሞ የተረገመ ግን ደግሞ ሃብታም ሊሆንም ይችላል። ሰላማዊ ኑሮ እና ባለጸግነት አብረው የሚሄዱት፤ ሃብትን በአግባቡ እና በትክክለኛው መንገድ መጠቀም ሲቻል ብቻ ነው።

ከልክ ያለፈ ድህነት እና ከልክ ያለፈ ቅንጦት እርካታ የሌለው ህይወት ተቃራኒ ጥጎች ናቸው። ሁለቱም ለአይምሮ ህመም ይዳርጋሉ። አንድ ሰው ትክክለኛ ሁኔታ ላይ ነው ያለው የሚባለው፤ ሃብቱ፤ ጤናው እና ደስታው ተጣጥመው መሄድ ሲችሉ ነው። ሃብት፤ ጤና እና ብልጽግና፤ የውጫዊ እና ውስጣዊ ማንነቶች የስምምነት ውጤቶች ናቸው።

ሰው እንደ ሰው ኖረ የሚባለው፤ ነገሮችን ማማረር ፤ሌሎችን መውቀስ ሲያቆም እና ህይወቱ የሚመራበትን ድብቅ ፍትህ መመርመር ሲጅምር ብቻ ነው። ወደራሱ መመልከትን ልምድ ሲያደርግ፤ ላለበት ሁኔታ ሌሎችን መውቀሱን ይተዋል። ውስጡን ያጠነክራል፤ አይምሮውን በጠንካራ አስተሳሰቦች ይገነባል። ከሁኔታዎች ጋር በጭፍን መጋፋጡን ትቶ፤ እራሱን ለመለወጥ እና በውስጡ ያለውን ድብቅ ሃይል እና ጉልበት ለመፈለግ እንደምክንያት ይጠቀመባቸዋል።

አለም በበላይነት በህግ እንጂ ግራ በመጋባት አትመራም፤ የህይወት መሰረትም ፍትህ ነው፤ አለምን በመንፈሳዊ መንገድ የሚያስሄዳት ትልቁ ሃይልም በህሊና ላይ የተመሰረተ ትክክለኛ ድርጊት ነው። ስለዚህ ሰው አለም ትክክለኛ መሆኗን እና አለመሆኗን ለመገንዘብ በመጀመሪያ እራሱ ትክክለኛ መሆን ይጠበቅበታል። ይህንን ለማውቅ በሚያደርገው ጥረትም፤ እራሱን በትክክለኛ መንገድ ሲያስሄድ ፤ የእሱ መለወጥ በሰዎች እና በሁኔታዎች ላይ እንዴት ተጽዕኖ እንደሚያደርግ ያስተውላል። የዚህ እውነታ ማረጋገጫም በእያንዳንዱ ሰው ውስጥ አለ። እራስን በመፈተሽ ማረጋገጥም ይቻለል። ለምስሌ አንድ ሰው አስተሳሰቡን ሙሉ በሙሉ ቢለውጥ፤ በህይወቱ ውስጥ የሚከሰተው ፈጣን ለውጥ ያስገርመዋል። ሰዎች አስተሳስብ ተደብቆ የሚቀር ይመስላልቸዋል፤ነገር ግን በአይምሮ ውስጥ ያለ ሃሳብ ተደብቆ ሊቀር አይቻለውም፤ ወደ ልምድ (ባህሪ) ይለወጣል እንጂ። ልምድ ደግሞ ሁኔታዎችን እና አጋጣሚዎችን ይፈጥራል።

ሰው እንደሰው ማሰብ ሲሳነው ደካማ አስተሳሰቡ ወደ መጠጥ ሱሰኛነት፤ ሴሰኛነት የመሳሰሉ የህይወት ልምዶች ውስጥ ይከቱታል። እኒህ ልምዶች ደግሞ  ለበሽታ እና ድህነት የሚያጋልጡ ሁኔታዎችን ይፈጥሩለታል። የተበከሉ አስተሳሰቦች በሙሉ ግራ በሚያጋባ አኗኗር ይገለጻሉ። በፍርሃት፤ በጥርጣሬ እና በመዋዠቅ ላይ የተመሰረቱ አስተሳሰቦች ፤ ደከማ እና ለውሳኔ የሚከብዱ ባህሪ እና ልምዶችን ሲያስከትሉ፤ እኒህ ባህሪ እና ልምዶች ደግሞ ውድቀትን፤ ድህነትን እና ጥገኝነትን ይፈጥራሉ። የስንፍና አስተሳሰቦች ሰው ንጽህናውን እንዳይጠብቅ እና ታማኝ እንዳይሆን ያደርጉታል፤ ሲቀጥልም ለልመና እና ለጥፋት ያደርሳሉ።የጥላቻ አስተሳሰቦች ለእረብሻ  እና ለጦርነት ይዳርጋሉ፤ እረብሻ እና ጦርነት ደግሞ ሰዎች የሚጎዱባቸውን ሁኔታዎች ይፈጥራሉ። የእራስ ወዳድነት አስተሳሰቦች አነሰም በዛም  ለጭንቀት ይገፋፋሉ።

በአንጻሩ መልካም አስተሳሰቦች በመልካም ሁኔታዎች እና አጋጣሚዎች ይገለጻሉ። ከክፉ ነገር የጸዳ አስተሳስበ፤ እረጋ ያለ ባህሪ እንዲኖር ሲያደርግ፤ እረጋ ያለ ባህሪ ደግሞ ሰላምን ይሰጣል። በራስ መተማመን እና ወኔ ላይ የተገነቡ አስተሳሰቦች ደግሞ ለስኬት የሚያደርሱ ባህሪዎች እንዲፈጠሩ ያደርጋሉ። ነጻ የሆኑ እና ጉልበት ያላቸው አስተሳሰቦች ይቅር ባይ፤ ቀና እና ጠንካራ ማንነትን ያጎናጽፋሉ። በፍቅር እና ሌላውን ባማከለ መልኩ የሚጸነሱ አስተሳሰቦች ከራስ ወዳድነት የጸዳ ባህሪን ያላብሳሉ። ከራስ ወዳድነት የጸዳ ባህሪ ደግሞ እውነተኛ ሃብት እና ብልጽግናን የሚሰጡ ሁኔታዎችን ያመቻቻሉ።

ሰዎች ሁኔታዎችን እና የህይወት አጋጣሚዎቻቸውን በቀጥታ መምረጥ አይችሉም፤ ነገር ግን አስተሳሰባቸውን መምረጥ ይችላሉ። አስተሳሰባቸውን ሲመርጡ በተዘዋዋሪ ሁኔታዎችን እና የህይወት መንገዳቸውን መረጡ ማለት ነው ።

ይቀጥላል ......


@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
544 views15:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-29 16:49:36 “As A Man Thinketh” -By James Allen

ክፍል ሶስት

የአስተሳሰባችን ተጽዕኖ”
(Effect of Thought on Circumstances.)

ሰው በውስጡ ብዙ ሃሳቦች፤ ምኞቶች እና ተስፋዎች አሉት። ከእነዚህ መካከል ገዝፈው ህይወቱን  የሚመራባቸው አስተሳሰቦች እና ምኞቶች እንዲሁም ተስፋዎች በስተመጨረሻ ፍሬ ማፍራታቸው አይቀርም። ግራ ቢያጋባም ሰው ለእሱ መልካም ካልሆነ ስፍራ (ጸሃፊው እስር ቤትን እና ድህነትን ይጠቅሳል) በእድል ወይም በአጋጣሚ አይገኝም። ይልቁንም በኑሮ ጉዞ ላይ ይመሩት በነበሩት አስተሳሰቦች እና ጥልቅ ፍላጎቶች ምክንያት ቀስ እያለ ተገፍቶ የደረሰበት ስፍራ ነው። በሌላ በኩል መልካም አስተሳሰብ የነበረው ሰው ድንገት ስህተት ቢሰራ እና ወንጀል ቢፈጽም፤ ውጫዊ በሆነ ነገር ተገፋፍቶ አልያም በአጋጣሚ ተገዶ ነው ልንል አንችልም። በአንጻሩ ያ የወንጀለኛ አስተሳሰብ ከመልካም ስብዕናው ስር ተደብቆ ለዘመናት የኖረ እና ሰዓቱ ሲደረስ የፈነዳ ነው።

አጋጣሚዎች ሰዎችን አይለውጡም፤ ሰውን ከድብቅ ማንነቱ ጋር ያስተዋውቁታል እንጂ። ሰውን ድንገት ከኑሮ ጎትቶ ወደ መጥፎ አለም የሚከት አጋጣሚ የለም፤ ወደ መጥፎ የሚመሩ አስተሳሰቦችን በውስጣችን ካልያዝን በቀር። በሌላ በኩል ወደ ደስታ ድንገት የሚወስድ አቋራጭ መንገድ ወይም አጋጣሚም የለም፤ ያ የደስታ ሃሳብ እና ምኞት ለረጅም ጊዜ በሰው ልብ ውስጥ የኖረ መሆን አለበት። ለዚህ ነው ሰው የኑሮው ጌታ፤ የአስተሳሰቡ ባለቤት እንዲሁም የህይወቱ ጠራቢ ነው የምንለው።

ወደዚህ ምድር ከመጣን ጀምሮ፤ በምድር ጉዞዋችን እያንጠለጠልን የምናልፋቸው የህይወት አጋጣሚዎች እና ልምዶች፤ የነፍሳችን ነጸብራቆች ናቸው። እንደ ነፍሳችን ንጽህና እና ግድፈት የሚከፈሉን ዋጋዎች።ሰው ወደራሱ የሚስበው የሚፈልገውን ነገር ሳይሆን፤ እራሱ የሆነውን ነገር ነው። አንዳንዴ የምንወስናቸው ውሳኔዎች እና ምኞቶቻችን እውን ከመሆን ሲገደቡ እናያለን።እንዲህ  የሚሆነው በውስጣችን ተደብቀው ያሉ አስተሳሰቦች እና ምኞቶች በምትኩ እውን ስለሚሆኑ ነው (Innermost desires and thoughts)። ድርጊታችን እና አስተሳሰባችን የእጣ ፋንታችን ወሳኞች ናቸው፤ የኑሮ እስር ውስጥ የሚከረችሙ ብረቶች ወይም እንደ ወፍ በነጻነት የሚያበሩ መልዕክቶች።

ሰው ስለተመኘ እና ስለጸለየ ብቻ የሚፈልገውን ያገኛል ማለት አይቻልም። ምኞቱ እና ጸሎቱ እውን የሚሆኑት ከተግባሩ እና ከአስተሳሰቡ ጋር መዋሃድ ሲችሉ ብቻ ነው። ታዲያ ሰው ካለበት ሁኔታ ጋር ሳይስማማ ሲቀር እና ከሁኔታዎች ጋር ሲጋፈጥ በውጤቶች ላይ እያመጸ ነው ማለት ነው። ችግሩ ከውጤቱ ጋር መጋፈጡ እና ለመለወጥ መነሳቱ ሳይሆን በጊዜው ሁሉ የውጤቱን መንስዔ ሲያዳብር መኖሩ ነው ። መንስዔውን ያዳብራል ሲባል በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ሊሆን ይችላል።

ብዙ ሰዎች ኑሮዋችውን ለማሻሻል ይፈልጉና እራሳቸውን ለማሻሻል ግን ፈቃድኛ አይሆኑም፤ ስለዚህም የራሳቸው እስረኛ ሆነው ይቀራሉ። እራሱን በወቀሳ እና በማሳነስ የማያሸማቅቅ ሰው፤ ልቡ የመረጠውን ማሳካት አይሳነውም። ሌላው ይቅር ገንዘብን ለማከማቸት ብቻ የሚደክም ሰው እራሱ በቅድሚያ ብዙ ማንነቱን የሚነኩ መስዋቶችን ለመክፈል ይገደዳል(ከገንዘብ የላቀ ህልም ያለው ሰው ደግሞ እራሱን በእጅጉ ለመለወጥ ዝግጁ መሆን አለበት)።ጠንካራ የሆነ ህይወትን ለመምራት፤ ጠንካራ የሆነ ማንነትን ይጠይቃልና።

ይቀጥላል ......


@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
400 views13:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-22 21:22:38 “As A Man Thinketh” -By James Allen

ክፍል ሶስት

የአስተሳሰባችን ተጽዕኖ”
(Effect of Thought on Circumstances.)

ሰው በውስጡ ብዙ ሃሳቦች፤ ምኞቶች እና ተስፋዎች አሉት። ከእነዚህ መካከል ገዝፈው ህይወቱን  የሚመራባቸው አስተሳሰቦች እና ምኞቶች እንዲሁም ተስፋዎች በስተመጨረሻ ፍሬ ማፍራታቸው አይቀርም። ግራ ቢያጋባም ሰው ለእሱ መልካም ካልሆነ ስፍራ (ጸሃፊው እስር ቤትን እና ድህነትን ይጠቅሳል) በእድል ወይም በአጋጣሚ አይገኝም። ይልቁንም በኑሮ ጉዞ ላይ ይመሩት በነበሩት አስተሳሰቦች እና ጥልቅ ፍላጎቶች ምክንያት ቀስ እያለ ተገፍቶ የደረሰበት ስፍራ ነው። በሌላ በኩል መልካም አስተሳሰብ የነበረው ሰው ድንገት ስህተት ቢሰራ እና ወንጀል ቢፈጽም፤ ውጫዊ በሆነ ነገር ተገፋፍቶ አልያም በአጋጣሚ ተገዶ ነው ልንል አንችልም። በአንጻሩ ያ የወንጀለኛ አስተሳሰብ ከመልካም ስብዕናው ስር ተደብቆ ለዘመናት የኖረ እና ሰዓቱ ሲደረስ የፈነዳ ነው።

አጋጣሚዎች ሰዎችን አይለውጡም፤ ሰውን ከድብቅ ማንነቱ ጋር ያስተዋውቁታል እንጂ። ሰውን ድንገት ከኑሮ ጎትቶ ወደ መጥፎ አለም የሚከት አጋጣሚ የለም፤ ወደ መጥፎ የሚመሩ አስተሳሰቦችን በውስጣችን ካልያዝን በቀር። በሌላ በኩል ወደ ደስታ ድንገት የሚወስድ አቋራጭ መንገድ ወይም አጋጣሚም የለም፤ ያ የደስታ ሃሳብ እና ምኞት ለረጅም ጊዜ በሰው ልብ ውስጥ የኖረ መሆን አለበት። ለዚህ ነው ሰው የኑሮው ጌታ፤ የአስተሳሰቡ ባለቤት እንዲሁም የህይወቱ ጠራቢ ነው የምንለው።

ወደዚህ ምድር ከመጣን ጀምሮ፤ በምድር ጉዞዋችን እያንጠለጠልን የምናልፋቸው የህይወት አጋጣሚዎች እና ልምዶች፤ የነፍሳችን ነጸብራቆች ናቸው። እንደ ነፍሳችን ንጽህና እና ግድፈት የሚከፈሉን ዋጋዎች።ሰው ወደራሱ የሚስበው የሚፈልገውን ነገር ሳይሆን፤ እራሱ የሆነውን ነገር ነው። አንዳንዴ የምንወስናቸው ውሳኔዎች እና ምኞቶቻችን እውን ከመሆን ሲገደቡ እናያለን።እንዲህ  የሚሆነው በውስጣችን ተደብቀው ያሉ አስተሳሰቦች እና ምኞቶች በምትኩ እውን ስለሚሆኑ ነው (Innermost desires and thoughts)። ድርጊታችን እና አስተሳሰባችን የእጣ ፋንታችን ወሳኞች ናቸው፤ የኑሮ እስር ውስጥ የሚከረችሙ ብረቶች ወይም እንደ ወፍ በነጻነት የሚያበሩ መልዕክቶች።

ሰው ስለተመኘ እና ስለጸለየ ብቻ የሚፈልገውን ያገኛል ማለት አይቻልም። ምኞቱ እና ጸሎቱ እውን የሚሆኑት ከተግባሩ እና ከአስተሳሰቡ ጋር መዋሃድ ሲችሉ ብቻ ነው። ታዲያ ሰው ካለበት ሁኔታ ጋር ሳይስማማ ሲቀር እና ከሁኔታዎች ጋር ሲጋፈጥ በውጤቶች ላይ እያመጸ ነው ማለት ነው። ችግሩ ከውጤቱ ጋር መጋፈጡ እና ለመለወጥ መነሳቱ ሳይሆን በጊዜው ሁሉ የውጤቱን መንስዔ ሲያዳብር መኖሩ ነው ። መንስዔውን ያዳብራል ሲባል በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ሊሆን ይችላል።

ብዙ ሰዎች ኑሮዋችውን ለማሻሻል ይፈልጉና እራሳቸውን ለማሻሻል ግን ፈቃድኛ አይሆኑም፤ ስለዚህም የራሳቸው እስረኛ ሆነው ይቀራሉ። እራሱን በወቀሳ እና በማሳነስ የማያሸማቅቅ ሰው፤ ልቡ የመረጠውን ማሳካት አይሳነውም። ሌላው ይቅር ገንዘብን ለማከማቸት ብቻ የሚደክም ሰው እራሱ በቅድሚያ ብዙ ማንነቱን የሚነኩ መስዋቶችን ለመክፈል ይገደዳል(ከገንዘብ የላቀ ህልም ያለው ሰው ደግሞ እራሱን በእጅጉ ለመለወጥ ዝግጁ መሆን አለበት)።ጠንካራ የሆነ ህይወትን ለመምራት፤ ጠንካራ የሆነ ማንነትን ይጠይቃልና።

ይቀጥላል ......


@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
352 views18:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ