*ምን አለበት**** (ሳሙኤል አዳነ) አሁን ምን አለበት ... ሰው እንዳሻው ቢኖር በራሱ ዳር ድንበር ፣ በልበ ጥፉዎች ልብ ባይሰበር ። እውነት ምን አለበት ... ሜዳውን ፈልጎ ዳገቱን ለወጣ፣ ሌላ መሰናክል ሌላ እክል ባልመጣ ። ምን አለበት ሰው ከገንዘብ በላይ ለፍቅር ቢታደል፣ በምንዝር አለቃ ፍትህ ባይጓደል ። ቢቻል ለፈጣሪ ባይሆን ለህሊና፣ ምናል ይሄ ትውልድ ለክፋት ባይቀና። እውነት ምን አለበት ... በውዥንብር አለም ግራ ባይገባ፣ ቁማር ባይጫወት ሰው ከግዜሩ ጀርባ ። ምን አለበት... ላዳም የተሰጠው የማፍቀር ልቦና ። ዛሬም በዚህ ጊዜ ቀጥሎ ቢፀና። እውነት ምናለበት ... ሰውን በ ሰውነት ሁሉ ባከበረ ፣ ግን በሚል አንድምታ ተቃርኖ ባልኖረ ። ..... ይገርመኛል .... ሰው በትምህርት አለም ጎልቶ እየዘመነ ፣ በጭላንጭል እውቀት በራሱ መስተዋል እየተማመነ ፣ ከጥቁር ሀሳብ ጋር አብሮ እየዳመነ ፣ ትናንትን ተወና የባቶችን ፀጋ የበረከቷን ቀን ፣ በጦር አውድማ ላይ ተጨንቆ እየዋለ ያድራል በሰቀቀን .. እና ምን አለበት ሰው መነሻውን ቢያቅ ትናንትን በይረሳ ፣ በአምላክ ፍጡር ላይ እጁን ባያነሳ ፣ አውነት ምን አለበት በአባቶች ልቦና ፤ በአባቶች እግር ፤ መራመድ ቢበጀው ፣ ይሄን ጭንቅ ጊዜ በጥበብ ቸሻግሮ በፍቅር ቢዋጀው። ምን አለበት ??????????...... 07/09/2011 ከምሽቱ 2:45 አ.አ @TIBEBnegni @sam2127 194 views12:36