Get Mystery Box with random crypto!

“As A Man Thinketh” -By James Allen ክፍል | ሰው መሆን...

“As A Man Thinketh” -By James Allen

ክፍል

የአስተሳሰባችን ተጽዕኖ”
(Effect of Thought on Circumstances.)

ጭንቀት እና መከራ ትክክለኛ ያልሆነ አስተሳሰብ ውጤቶች ናቸው። ሰው ከውስጣዊ ማንነቱ ጋር አብሮ መሄድ ሲያቅተው፤ በሰብዓዊ ህግ ስር ተገዝቶ መኖር ሲሳነው የመከራን ቀንበር ይሸከማል። የጭንቀት ማብቂያው ነፍስን ማጽዳት ነው፤ አይምሮን የሚያጎድፉ ነገሮችን ሁሉ ማስወገድ። መንፈሱ ንጹህ የሆነ ሰው ጭንቀት አያደፍረውም። ወርቅ ንጹህ ወርቅ እስኪሆን ድረስ በእሳት ይፈተናል እንጂ፤ ንጹህ ወርቅ ከሆነ ባኋላ በእሳት ብናቀልጠው ዋጋ የለውም። ልክ እንደ ንጹህ ወርቅም፤ በመንፈሱ ንጹህ የሆነ ሰው በመከራ እና ጭንቀት ከልክ በላይ አይፈተንም።

ሰው ከአይምሮው ጋር ሰላም ሲኖረው መልካም ሁኔታዎችን በዙሪያው ይፈጥራል፤ ከራሱ ጋር ሰላም መፈጠር ሲሳነው ግን ለመጥፎ አጋጣሚዎች እራሱን ያጋልጣል። የትክክለኛ አስተሳሰብ መገለጫ ሰላማዊ መሆን ሲሆን ደስተኛ ያልሆነ ወይም ዝብርቅርቅ ያለ ኑሮ ደግሞ ትክክለኛ ያልሆነ አስተሳሰብ መለያ ነው። ሰው የተባረከ፤ ነገር ግን ድሃ ሊሆን ይችላል፤ ወይም ደግሞ የተረገመ ግን ደግሞ ሃብታም ሊሆንም ይችላል። ሰላማዊ ኑሮ እና ባለጸግነት አብረው የሚሄዱት፤ ሃብትን በአግባቡ እና በትክክለኛው መንገድ መጠቀም ሲቻል ብቻ ነው።

ከልክ ያለፈ ድህነት እና ከልክ ያለፈ ቅንጦት እርካታ የሌለው ህይወት ተቃራኒ ጥጎች ናቸው። ሁለቱም ለአይምሮ ህመም ይዳርጋሉ። አንድ ሰው ትክክለኛ ሁኔታ ላይ ነው ያለው የሚባለው፤ ሃብቱ፤ ጤናው እና ደስታው ተጣጥመው መሄድ ሲችሉ ነው። ሃብት፤ ጤና እና ብልጽግና፤ የውጫዊ እና ውስጣዊ ማንነቶች የስምምነት ውጤቶች ናቸው።

ሰው እንደ ሰው ኖረ የሚባለው፤ ነገሮችን ማማረር ፤ሌሎችን መውቀስ ሲያቆም እና ህይወቱ የሚመራበትን ድብቅ ፍትህ መመርመር ሲጅምር ብቻ ነው። ወደራሱ መመልከትን ልምድ ሲያደርግ፤ ላለበት ሁኔታ ሌሎችን መውቀሱን ይተዋል። ውስጡን ያጠነክራል፤ አይምሮውን በጠንካራ አስተሳሰቦች ይገነባል። ከሁኔታዎች ጋር በጭፍን መጋፋጡን ትቶ፤ እራሱን ለመለወጥ እና በውስጡ ያለውን ድብቅ ሃይል እና ጉልበት ለመፈለግ እንደምክንያት ይጠቀመባቸዋል።

አለም በበላይነት በህግ እንጂ ግራ በመጋባት አትመራም፤ የህይወት መሰረትም ፍትህ ነው፤ አለምን በመንፈሳዊ መንገድ የሚያስሄዳት ትልቁ ሃይልም በህሊና ላይ የተመሰረተ ትክክለኛ ድርጊት ነው። ስለዚህ ሰው አለም ትክክለኛ መሆኗን እና አለመሆኗን ለመገንዘብ በመጀመሪያ እራሱ ትክክለኛ መሆን ይጠበቅበታል። ይህንን ለማውቅ በሚያደርገው ጥረትም፤ እራሱን በትክክለኛ መንገድ ሲያስሄድ ፤ የእሱ መለወጥ በሰዎች እና በሁኔታዎች ላይ እንዴት ተጽዕኖ እንደሚያደርግ ያስተውላል። የዚህ እውነታ ማረጋገጫም በእያንዳንዱ ሰው ውስጥ አለ። እራስን በመፈተሽ ማረጋገጥም ይቻለል። ለምስሌ አንድ ሰው አስተሳሰቡን ሙሉ በሙሉ ቢለውጥ፤ በህይወቱ ውስጥ የሚከሰተው ፈጣን ለውጥ ያስገርመዋል። ሰዎች አስተሳስብ ተደብቆ የሚቀር ይመስላልቸዋል፤ነገር ግን በአይምሮ ውስጥ ያለ ሃሳብ ተደብቆ ሊቀር አይቻለውም፤ ወደ ልምድ (ባህሪ) ይለወጣል እንጂ። ልምድ ደግሞ ሁኔታዎችን እና አጋጣሚዎችን ይፈጥራል።

ሰው እንደሰው ማሰብ ሲሳነው ደካማ አስተሳሰቡ ወደ መጠጥ ሱሰኛነት፤ ሴሰኛነት የመሳሰሉ የህይወት ልምዶች ውስጥ ይከቱታል። እኒህ ልምዶች ደግሞ  ለበሽታ እና ድህነት የሚያጋልጡ ሁኔታዎችን ይፈጥሩለታል። የተበከሉ አስተሳሰቦች በሙሉ ግራ በሚያጋባ አኗኗር ይገለጻሉ። በፍርሃት፤ በጥርጣሬ እና በመዋዠቅ ላይ የተመሰረቱ አስተሳሰቦች ፤ ደከማ እና ለውሳኔ የሚከብዱ ባህሪ እና ልምዶችን ሲያስከትሉ፤ እኒህ ባህሪ እና ልምዶች ደግሞ ውድቀትን፤ ድህነትን እና ጥገኝነትን ይፈጥራሉ። የስንፍና አስተሳሰቦች ሰው ንጽህናውን እንዳይጠብቅ እና ታማኝ እንዳይሆን ያደርጉታል፤ ሲቀጥልም ለልመና እና ለጥፋት ያደርሳሉ።የጥላቻ አስተሳሰቦች ለእረብሻ  እና ለጦርነት ይዳርጋሉ፤ እረብሻ እና ጦርነት ደግሞ ሰዎች የሚጎዱባቸውን ሁኔታዎች ይፈጥራሉ። የእራስ ወዳድነት አስተሳሰቦች አነሰም በዛም  ለጭንቀት ይገፋፋሉ።

በአንጻሩ መልካም አስተሳሰቦች በመልካም ሁኔታዎች እና አጋጣሚዎች ይገለጻሉ። ከክፉ ነገር የጸዳ አስተሳስበ፤ እረጋ ያለ ባህሪ እንዲኖር ሲያደርግ፤ እረጋ ያለ ባህሪ ደግሞ ሰላምን ይሰጣል። በራስ መተማመን እና ወኔ ላይ የተገነቡ አስተሳሰቦች ደግሞ ለስኬት የሚያደርሱ ባህሪዎች እንዲፈጠሩ ያደርጋሉ። ነጻ የሆኑ እና ጉልበት ያላቸው አስተሳሰቦች ይቅር ባይ፤ ቀና እና ጠንካራ ማንነትን ያጎናጽፋሉ። በፍቅር እና ሌላውን ባማከለ መልኩ የሚጸነሱ አስተሳሰቦች ከራስ ወዳድነት የጸዳ ባህሪን ያላብሳሉ። ከራስ ወዳድነት የጸዳ ባህሪ ደግሞ እውነተኛ ሃብት እና ብልጽግናን የሚሰጡ ሁኔታዎችን ያመቻቻሉ።

ሰዎች ሁኔታዎችን እና የህይወት አጋጣሚዎቻቸውን በቀጥታ መምረጥ አይችሉም፤ ነገር ግን አስተሳሰባቸውን መምረጥ ይችላሉ። አስተሳሰባቸውን ሲመርጡ በተዘዋዋሪ ሁኔታዎችን እና የህይወት መንገዳቸውን መረጡ ማለት ነው ።

ይቀጥላል ......


@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni