ባልንጀሮቻችሁን ባያችሁ ቁጥር ራሳችሁን ተመልከቱ " አሉ ጃፓናዊው መምህር ። " ግን እንደሱ ማድረጉ ራስ ወዳድነት አይሆንም ? "- አንደኛው ተማሪ ያቸው ጠየቀ ። - " ምክንያቱም ሁልጊዜ የምናተኩረው በራሳችን ላይ ከሆነ ፥ ሌሎች ሰዎች የያዙአቸውን መልካም እሴቶች ለማስተዋል እድል እናጣለን ። " " አንተ እንዳልከው ሌሎች ሰዎች የያዙአቸውን መልካም እሴቶች መመልከት የምንችል ቢሆን እንዴት ደግ ነበር ! " መለሱ መምህር ። - ቀጠሉና " እውነታው ግን አንተ ካልከው በተቃራኒው ነው ። .. ሌሎች ሰዎችን ባየን ቁጥር የምንመርጠው እንከኖቻቸውን ነው ። የሌላኛውን ሰው ክፋ ገፅታ ለማግኘት የቻልነውን ያህል የምንባትለው ከእኛ የባሰ እንዲሆን ስለምንፈልግ ነው ። ስሜታችንን ሲጎዳን ይቅርታ ልናደርግለት የሚከብደንም የራሳችን ጥፋት ይቅር ያስብላል ብለን ስለማናምን ነው ።የምናውቃቸውን ጦረኛ ቃላት እያፈናጠርን እናቆስለዋለን ። ይህን የምናደርገው እውነታውን ከራሳችን ለመደበቅ ስለምንፈልግ ነው ። ...ማንም ሰው ምን ያህል ተሰባሪ ፥ ምን ያህል ስንጥቅጥቃችን የበዛ ፥ ሽንቁራችን የጎደጎደ መሆኑን እንዳያይብን ስንል ጠቃሚ እንደሆንን አድርገን እናስመስላለን ። ለዚያም ነው ወዳጅህን በፈረድክ ፥ ሌላውን ሰው በበየንክ ቁጥር በትክክል ፍርድ ላይ ያለኸው ራስህ መሆንህንም ማወቅ የሚጠቅምህ ። ውብ አሁን @TIBEBnegni @TIBEBnegni @TIBEBnegni 272 views18:53