Get Mystery Box with random crypto!

*የልብ ቋንቋ* የህይወት ጣዕሙ የጠፋባቸው ሰዎች አሉ፤በየዕለቱ ተመሳሳይ ህይወት የሚኖሩና | ሰው መሆን...

*የልብ ቋንቋ*

የህይወት ጣዕሙ የጠፋባቸው ሰዎች አሉ፤በየዕለቱ ተመሳሳይ ህይወት የሚኖሩና በህይወታቸው ውስጥ አዲስ ክስተት አጥተው ስልቹ የሆኑ ሰዎች ።

ዘወትር ተመሳሳይህይወት መግባትና መዉጣት ፣መብላትና መጠጣት ..ብቻ አዲስ ህይወት የሌለበት ስልቹ አለም።

እነዚህ ሰዎች ህይወትን በማሰብ (አእምሮ) ብቻ የሚኖሯት ሰዎች ናቸው።

ምክንያቱን የሰው ልጅ የልብ ቋንቋ ካልገባው በአእምሮ ብቻ ከኖረ ህይወት ትርጉም የሌለባት ባዶ ስለምትሆን ህይወትን በአእምሮ ሳይሆን በልብ ኑሯት ፤ ህይወታችሁን በልብ ቋንቋ ስትመሯ አእምሯችሁ ታላቅ ተፈጥሮን ያሳያችኧል ።
በአእምሯችሁ ስትኖሩ ፓለቲከኛ፣ዘረኛ፣ አክራሪ.......ወ.ዘ.ተ ትሆናላችሁ ፤ በልባችሁ ስትኖሩ ግን መንፈሳዊ ትሆናላችሁ።

በልባችሁ ስትኖሩ የህይወት ጣእሙ ይገባችኧል፤ የፍቅር ሙቀቱ ይሰማችኧል።

ተልእኳችሁን ስታውቁና በተሰጥኦዋችሁ ስትኖሩ የህይወታችሁ ገዢ ሀይል ከልባችሁ ይመነጫል።
አእምሯችሁም የልባችሁ ታዛዥ ይሆናል።
ተሰጥኦዋችሁን ፈልጉ ራሳችሁን ፈልጉ አግኙትም።
የዚያን ጊዜ ህይወታችሁ ከአሰልቺነት ወጥቶ በደስታ ይሆናል። "