Get Mystery Box with random crypto!

ስለ ጤና የቴሌግራም ቻናል 🔍💊💉

የቴሌግራም ቻናል አርማ seltena — ስለ ጤና የቴሌግራም ቻናል 🔍💊💉
የቴሌግራም ቻናል አርማ seltena — ስለ ጤና የቴሌግራም ቻናል 🔍💊💉
የሰርጥ አድራሻ: @seltena
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.68K
የሰርጥ መግለጫ

እንኳን ደህና መጣችሁ! ይህ ስለ ጤና ጉዳዮች የምናስተምርበት ቻናል ነው። አብረን እንቆይ !
በዚህ ቻናል- ስለ
👉አካላዊ ና ሰነ-ልቦናዊ የጤና እክሎች እና መፍትሄዎቻቸው በዝርዝር በጤና ባለሞያዎች ይዳሰሳል። ️
👉አዳዲስ የጤና ሳይንስ መረጃዎች ይቀርባሉ::
👉እንዲሁም በቀረቡ መረጃዎች ላይ ተጨማሪ ጥያቄ ካለ በጤና ጥያቄ ና መልስ ግሩፕ ላይ እወያያለን! ይምጡ ይቀላቀሉን ይወዱታል!

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-01-04 14:34:21 #የድድ #መድማት
#ከወደዱት #ያጋሩት

የድድ መድማት በጣም ከተለመዱ የድድ በሽታ ምልክቶች ውስጥ አንዱ ነው። አልፎ አልፎ የሚከሰት የድድ መድማት ጥርስዎን በሀይል በመቦረሽ ወይም በትክክል የማይገጥሙ አርቴፊሻል ጥርስ ሲያስገቡ ሊከሰት ይችላል። በተደጋጋሚ የሚከሰት የድድ መድማት ችግር ካለዎ ከፍ ያለ የጤና ችግር ምልክት ሊሆን ይችላል፤ ከነዚህም ዉስጥ፦

የጥርስ ዙሪያ ያለዉ አካባቢ ህመም( ፔሪኦዴንታይቲስ)-- በጣም ከፍ ያለ የድድ በሽታ
የቫይታሚን እጥረት
ደም እንዲረጋልዎ የሚያደርግ ሴሎች ( ፕላትሌት) እጥረት ወይም ማነስ
የደም ካንሰር( ሊኮሚያ)ና የመሳሰሉት ናቸዉ።

የድድ መድማት የሚያመጡ የጥርስ ችግሮች

የጥርስ ችግሮች የድድ መድማት ችግር ሊያመጡ ከሚችሉ ነገሮች ዋነኛ ሲሆኑ የድድ መቆጣትና የጥርስ ዙሪያ ችግሮች መኖር ድድዎ በቀላሉ ለመድማት የተጋለጠ እንዲሆን ያድርጋሉ።
የድድ በሽታ
በጥርሶችዎና በድድዎ መስመሮች ላይ ቆሻሻዎችና ባክቴሪያዎች ለረጅም ጊዜ ተጣብቀዉ ሲቆዩ ብዙ ሰዎች የድድ በሽታ ይይዛቸዋል። ጥርስዎን በአግባቡ የማያፀዱና የተጣበቁ ቆሻሻዎች ካልተወገዱ ቆሻሻዉ በጣም ጠንካራ ግግር በጥርስዎና ድድዎ ላይ ስለሚፈጠር መድማቱን ያባብሰዋል። የቆሻሻ ግግሩ በጥርስዎ ላይ ሲጋገር ወደ ድድዎ የተጠጋ ከሆነ የድድ ህመም እንዲከሰት ያደርጋል።

የድድ ህመም ምልክቶች

የድድ ማበጥ
በአፍዎና በድድዎ ላይ ህመምና ቁስል መከሰት
የድድ መድማት ናቸዉ።

የጥርስ ዙሪያ መቆጣት( ፔሪኦዴንታይቲስ)

የድድ ህመም እየጨመረ ወይም እየባሰ ከመጣ የጥርስ ዙሪያ ህመም እንዲከሰት ያደርጋል። የጥርስ ዙሪያ ህመም የድድ፣ የመንጋጋ አጥንትና ጥርስን ከድድ ጋር የሚያጣብቁ ክፍሎች እንፌክሽን ምክንያት የሚከሰት ነዉ። ይህ ችግር ለጥርስዎ መነቃነቅና መነቃቀል መንስኤ ሊሆን ይችላል።
የቫይታሚን እጥረት
የቫይታሚን ሲና ቫይታሚን ኬ እጥረት የድድ በቀላሉ መድማት ችግር ሊያመጣ ይችላል። የድድ መድማት ችግር ካለዎና መንስኤዉ የጥርስ እንክብካቤ ችግር ምክንያት ካልሆነ የቫይታሚን ሲና ኬን መጠን ከህክምና ባለሙያዎ ጋር በመነጋገር ያድርጉ። በተጨማሪም የቫይታሚን ሲና ኬ ምንጭ የሆኑ ምግቦችን ይመገቡ።

ሌሎች ለድድ መድማት ችግር ሊዳርጉ የሚችሉ ነገሮች

አርቴፊሻል ጥርስ የሚጠቀሙ ሰዎች፥ በተለይ በትክክል የማይገጥም ከሆነ
እርግዝና፦ በእርግዝና ወቅት የሚከሰቱ የሆርሞን ለውጦች ድድ ይበልጥ በቀላሉ ለመድማት እንዲጋለጥ ያደርጋሉ።
የደም መፍሰስ ችግር የሚያመጡ አንደ ሄሞፊሊያና የደም ካንሰር ያሉ ችግሮች
የደም ማቅጠኛ መድሃኒቶችን የሚወስዱ ሰዎች፦ እንደ ዋርፋሪን፣ ሄፓሪንና አስፕሪን ያሉ መድሃኒቶች

አድራሻችን፦ ቦሌ ሩዋንዳ ከሩዋንዳ ኤምባሲ ጎን ሲሆን በተጨማሪም እኛን ለማግኘት ከፈለጉ የሚከተሉትን ይጠቀሙ
https://www.sturaelclinic.com/
https://www.facebook.com/sturaelclinic/
9424
+251-940464646 /0940565656 /0913349301 +251-116662556
/0116663741
Rwanda St Just Beside Rwanda Embassy Addis Ababa Ethiopia.
https://sturaelclinic@gmail.com
1.3K views11:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-26 13:56:59 #ኦሚክሮን
#ከወደዱት #ያጋሩት

ኦሚክሮን አዲሱ የኮቪድ 19 ዝሪያ ሲሆን ከመጀመሪያው ኮቪድ ቫይረስ በበለጠ በቀላሉ ሊሰራጭ ይችላል፤ ነገር ግን ኦሚክሮን ከዴልታ የኮቪድ ዝሪያ ጋር ሲወዳደር ምን ያህል በቀላሉ እንደሚሰራጭ አይታወቅም። እንደ ሲዲሲ መረጃ ከሆነ ማንኛውም የኦሚክሮን ኢንፌክሽን ያለበት ሰው ምንም እንኳን ክትባት ቢወስድም ወይም የበሽታ ምልክት ባይኖረውም ቫይረሱን ወደሌሎች ሊያስተላልፍ ይችላሉ።

በተለይም ሙሉ በሙሉ በተከተቡ ሰዎች ላይ በኦሚክሮን ቫይረስ የሚከሰቱ ኢንፌክሽኖችና አዲስም ይሁን በድጋሚ ኢንፌክሽን ከተከሰት በኋላ ከሌሎች የኮሮና ቫይረሶች አንፃር የበለጠ ከባድ ህመም ወይም ሞት እንደሚያደርስና እንደማያደርስ ለማወቅ የበለጠ መረጃ ስለሚያስፈልግ ብጥናት ላይ ነዉ ያለዉ።
አሁን እየተሰጠ ያሉት ክትባቶች ከከባድ ሕመም፣ በኮቪድ ምክንያት ሆስፒታል ከመተኛትና በኦሚክሮን ምክንያት ከሚከሰተዉ ሞት ይከላከላሉ ተብሎ ይጠበቃል። ነገር ግን ክትባት ሙሉ በሙሉ በተከተቡ ሰዎች ላይ ድንገተኛ ኢንፌክሽኖች ሊከሰቱ ይችላሉ። እንደ ዴልታ የኮቪድ ዝርያዎች ክትባቶችን መዉሰድ ለኦሚክሮን ዝርያም ከባድ ሕመምን፣ ሆስፒታል መተኛትንና ሞትን ለመከላከል ውጤታማ ሆነው ቀጥለዋል።

ህክምናን በሚመለከት ጥናቶች የቀጠሉ ቢሆንም ለሌሎች የኮቪድ ዝርያዎች የሚሰጠዉ ህክምና ለኦሚክሮን የኮቪድ ዝርያ የሚሰራ መሆኑን ነዉ።

ኦማይክሮንን ለመከላከል

ክትባት፦ ክትባት ሰዎችን ከኮቪድ-19 ለመጠበቅ፣ የኮቪድን ስርጭት ለማዘግየ ወይም ለመቀነስና አዳዲስ የኮቪድ ዝሪያዎች የመፈጠር እድልን ለመቀነስ የሚረዳ ምርጡ የህብረተሰብ ጤና መለኪያ ዋነኛ እርምጃ ነዉ።
ማስክ ማድረግ፦ ማስክ ከሁሉም አይነት የኮቪድ ዝሪያዎች ለመከላከል ይረዳል። አንድ ሰዉ የኮቪድ ክትባት ሙሉዉን ቢወስድም ማስክ ማድረግ ይጠበቅበታል።
የኮቪድ ምርመራ ማድረግ
በአሁኑ ወቅት ኮቪድ በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋና የስርጭት አድማሱ እየጨመረ የመጣ በመሆኑ እራስዎንና ቤተሰብዎን ከኮቪድ ወረርሽኝ ይጠብቁ። ስለሆነም

ርቀትዎን ይጠብቁ
ማስክ በአግባቡ ያድርጉ
እጅዎን በአግባቡ ያፅዱ!

አድራሻችን፦ ቦሌ ሩዋንዳ ከሩዋንዳ ኤምባሲ ጎን ሲሆን በተጨማሪም እኛን ለማግኘት ከፈለጉ የሚከተሉትን ይጠቀሙ

https://www.sturaelclinic.com/
https://www.facebook.com/sturaelclinic/
9424
+251-940464646 /0940565656 /0913349301 +251-116662556
/0116663741
Rwanda St Just Beside Rwanda Embassy Addis Ababa Ethiopia.
https://sturaelclinic@gmail.com
936 views10:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-10 14:43:07 #ፅንስ ማስወረድ እና አደጋዎቹ

#ፅንስ ማስወረድ ምንድን ነው?
ሴቶች ሳያስቡት ወይም ሳይወጥኑት ፅንስ ቢያስወርዳቸው የፅንስ መጨንገፍ ወይም ውርጃ ይባላል።
# ነገር ግን በፍላጎት ሆነ በእቅድ ፅንስን ለማስወገድ የሚደረግ ክንዋኔ ፅንስ ማስወረድ ይባላል።
ፅንስ ማስወረድ በተመለከተ የጤና ባለሙያዎች እና የሲቪል ማህበራት ያላቸው አስተያየት በሁለት ጎራ ይከፍላቸዋል።
የመጀመሪያው ፅንስ ማቋረጥ የሴቷ መብት ነው። በመሆኑም ይህ መብት በህግም ሆነ በአገልግሎት አለማቅረብ ሳቢያ መገደብ የለበትም የሚል ሲሆን
በሌላ በኩል ደግሞ
2ኛው ፅንሱ ህይወት ያለው ፍጡር በመሆኑ ፅንስ ማስወረድ አውቆ እና ሆን ብሎ ህይወት እንደማጥፋት ይቆጠራል የሚሉ ወገኖች አሉ።

በአገራችን ያሉ ትላልቅ ሃይማኖቶችም ቢሆኑ ፅንስ ማስወረድን ይቃወማሉ።

በፅንስ ማስወረድ ሕጋዊ መሆን አለመሆን ያለው ውዝግብ በአገራችን ብቻ ሳይሆን በሁሉም አገሮች ውስጥ የሚካሄድ ነው። የዚህ ፅሁፍ አላማ ከአንደኛው ወይም ከሌላኛው ጋር መወገን ሳይሆን በፅንስ ማስወረድ ዙሪያ ያሉትን እውነታዎችና አደጋዎች ለማያውቁ ማሳወቅ ነው።

#ሴቶች ፅንስ የሚያስወርዱት ለምንድን ነው?
ሴቶች ፅንስ የሚያስወርዱት አስገዳጅ ሁኔታዎች በሚያጋጥማቸው ጊዜ ነው። ሴቶች ፅንስ ለማቋረጥ የሚገደዱበት የተለያዩ ምክንያቶች አሉ
● በቂ ልጆች ስላሏቸው ተጨማሪ ልጅ ለማሳደግ ስልማይችሉ
● ባለማግባታቸው ምክኒያት ልጅ ብቻቸውን ማሳደግ ስለማይፈልጉ
● ከባለቤታቸው ጋር በሚፈጠሩ ችግሮች ምክኒያት
● በጽንሱ ላይ የሆነ የአፈጣጠር ችግር እንዳለ ከታወቀ
● እርግዝናው ለጤናቸውም ሆነ ለሂወታቸው አደገኛ ከሆነ
● እርግዝናው የመጣው በአስገድዶ መደፈር ከሆነ

#ፅንስ የሚቋረጠው እንዴት ነው?

ፅንስ ለማስወረድ ሁለት ዋና ዋና መንገዶች አሉ
● በመድኃኒት ፅንስ ማስወረድ
እርግዝናዎን ለማቆም ክኒን ይወስዳሉ። ይሄ እስከ 10 ሳምንታት ድረስ ላለ እርግዝና ይሆናል። የመድሃኒት ውርጃ የመረጡ ሴቶች 2 የተለያዩ መድሃኒቶች መውሰድ አለባቸው።
● በሕክምና መሳሪያ የተደገፈ (MVA) ፅንስ ማስወረድ
ሐኪም እርግዝናን ለማስቆም የቀዶ ጥገና መሣሪያዎችን ይጠቀማል። ይህ በመጀመሪያው ወይም በሁለተኛ ወር ውስጥ ላለ እርግዝና ለማስወረድ ሊከናወን ይችላል። ሂደቱ (ፕሮሲጀሩ) ከ 15 እስከ 30 ደቂቃዎች ይወስዳል ነገር ግን አብዛኛዎቹ ሴቶች ክሊኒኩ ውስጥ ለጥቂት ሰዓታት ለክትትል ይቆያሉ።

በመድሃኒት ውርጃ ከተፈጸመ በኋላ የሕመም ምልክቶች ይታዩኛል?
አዎ ሁለተኛውን መድሃኒት ከወሰዱ በኋላ
● የታችኛው የሆድ ህመም እና ቁርጠት ይኖራል። እነዚህ ህመሞች እስከ 6 ሰዓታት የሚቆዩ ናቸው።
● ከማህጸን ውስጥ መድማት
ለጥቂት ሰዓቶች ከባድ ሊሆን ይችላል ከዚይም ቀላል የደም መፍሰስ ለጥቂት ሳምንታት ሊቀጥል ይችላል
● ትኩሳት, ማቅለሽለሽ, ማስታወክ እና ተቅማጥ

# በሕክምና መሳሪያ ይምታገዝ ውርጃ (MVA) ከተደረገ በኋላ የሕመም ምልክቶች ይኖራቸው ይሆን?
አዎ ይኖራቸዋል
● በታችኛው ሆድ ውስጥ ህመም እና ቁርጠት። ይህ ለጥቂት ሰዓታት ይቆያል
● ከማህጸን ውስጥ መድማት
ይህ አብዛኛውን ጊዜ ቀላል ሲሆን መድማቱ እስከ 2 ሳምንታት ሊቆይ ይችላል !!

14 ወይም ከዚያ በላይ ሳምንታት እርጉዝ ከሆንኩኝ ፅንስ ማስወረድ እችላለሁ?
ሴቶች በሚኖሩበት ሃገር በተወሰነው ህጋዊ ገደብ ድረስ ማስወረድ ይችላሉ። በብዙ አገሮች ህጋዊ ገደቡ ከ 20 እስከ 24 ሳምንታት ድረስ ነው። ከ14 ሳምንቶች በኋላ የሚደረግ የፅንስ ማስወረድ ረዘም ያለ ጊዜ ሊወስድ ይችላል። ይሁን እንጂ አሁንም መድሃኒት ወይም በሕክምና መሳሪያ ይምታገዝ ውርጃ (MVA) ወይም ሁለቱንም ዘዴዎች መጠቀም አስፈላጊ ሊሆን ይችላል።

#ፅንሱን ካስወረድኩኝ በኋላ ከቀጠሮዬ ውጪ ሐኪም ማማከር የሚኖርበት ሁኔታዎች አሉ?
አዎ ከስር የተዘረዘሩት የአደጋ ምልክቶች ካዪ ወዲያውኑ የህክምና እርዳታ ማግኘት አለብዎ
● ከፍተኛ መጠን ያለው ከማህጸን ደም መፍሰስ
● የህመም ማስታገሻ ክኒን ቢውስዱም የማይታገስ ከባድ ቁርጠት
● ከፍ ያለ ትኩሳት (ከ38.5ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ በላይ የሆነ ትኩሳት)
● መጥፎ ጠረን ያለው የሴት ብልት ፈሳሽ
● ህሊና መሳት ወይም መዘባረቅ
እንዚህ ምልክቶች ካዩ የህክምና እርዳታ ማግኘት አለብዎ!
አንዳንድ ጊዜ ፅንሱ ሙሉ በሙሉ ላይወጣ ይችላል። በዚህ ጊዜ የሚከተሉት ምልክቶች ሊታዩ ይችላሉ :-
● መድሃኒት ከተሰጠ በኋላ መድማት አይኖርም
● አሁንም ቢሆን የእርግዝና ምልክቶች እንደ ማቅለሽለሽ እና የጡት ህመም ይኖራሉ
● ፅንስ ካወረዱ ከሁለት ሳምንታት በኃላ የማህጸን መድማት
● ውርጃ ከፈጸሙ በኋላ በነበሩት ስድስት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ የወር አበባ አለማየት

#ፅንስ ማስወረድ አደጋ አለው?
በአጠቃላይ በሰለጠነ ባለሞያ እና በጤና ተቋም የሚደረጉ ውርጃዎች በጣም አስተማማኝ(safe )ናቸው። ነገር ግን ልክ እንደ ማንኛውም የሕክምና ሂደት ጽንስ ማስወረድ አንዳንድ አደጋዎች ሊያጋጥሙ ይችላሉ። ከስር የተዘረዘሩት ከፅንስ ማስወረድ በኋላ ሊከሰቱ የሚችሉ የጤና ችግሮች ናችው ።
1. ከማህጸን ብዙ ደም መፍሰስ
2. ኢንፌክሽን
3. የሆድ ውስጥ አካላት(የሆድቃ)መጎዳት

NB
#ፅንስ ማስወረድ በሚቀጥሉት አይነት ሁኔታዎች ከተካሄደ አደገኛ አይደለም ተብሎ ይታሰባል።
● በአግባቡ በሰለጠኑ እና ልምድ ባላቸው የጤና ባለሙያ ከተሰጠ
● ንፅህናቸው በተጠበቀ የህክምና መሳሪያዎች ከተሰራ

#በሌላ በኩል ደግሞ ፅንስ ማስወረድ አደገኛ የሚሆንበት ሁኔታ
● በጤና ባለሙያ ካልተካሄደ ወይም ጤና ባለሙያው በቂ ልምድ ከሌለው
● ለፅንሥ ማስወረጃ የማይሆኑ መድሃኒቶች እና መሳሪያዎች መጠቀም
● መሳሪያዎቹ ሆኑ አከባቢው ንጽህና ከሌላቸው
በከፍተኛ ጭንቀት ላይ ያሉ ሴቶች ጽንስ ለማስወረድ ብዙ አይነት ያልተገቡ ሙከራዎች ያደርጋሉ እናም እራሳቸው ለአደጋ ያጋልጣሉ።

አደገኛ በሆኑ ፅንስ የማስወረድ ተግባራት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሴቶች ለሞት ፣ ለኢንፌክሽን እና ለመሃንነት ይዳረጋሉ።

ፅንስ ለማስወረድ ከመወስኖ በፊት አቅራብያዎ ወደ ሚገኝ ጤና ተቋም በመሂድ ስለ ጉዳዩ የጤና ባለሞያዎችን ያማክሩ !!

=> ጥያቄ ለመጠየቅ እና በዚህ ቻናል በሚውጡ ፅሑፎች ላይ አስተያየት ለመስጠት ለምትፈልጉ https://t.me/joinchat/መትቭ hYG2fFyiVaF3nspAA ግሩፕ ላይ መስጠት ትችላላቹ !!

ስለ ጤና ቻናል @seltena
ጤናማ ኢትዮጵያ (Healthy Ethiopia !)
1.0K views11:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-22 19:43:28
1.6K views16:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-22 19:43:28 ማድያት (Melasma)
***********
ማድያት በዋናነት በፊታችን ቆዳ ላይ በቀለም መዛባት የሚፈጠር የቆዳ ችግር ዓይነት ነው፡፡ በዚህ የተናሳ የፊታችን ቆዳ ቡናማ ወይም ግራጫ ቀለም ያለው ነገር ይለጠፍበታል፡፡

ማድያት ብዙ ጊዜ ለጸሐይ በተጋለጠው የሰውነታችን ክፍል በሆኑት በአፍንጫችን ፣በግንባራችን፣ በጉንጭና በላይኛው ከንፈራችን ላይ የሚወጣ ሲሆን አንዳንዴም ክንዳአችን፣ አንገታችንና ትከሻችን ላይ ሲወጣ ይስተዋላል፡፡

እስከ አሁን ድረስ ሐኪምች የማድያት መከሰት ምክንያትን መነሾ ሙሉ በሙሉ በውል ያላወቁ ሲሆን ይሁንና በተደጋጋሚ በተደረጉ የጥናት ግኝቶች ለማድያት መከሰት አስተዋጾ አለው ተብሎ የታመነው የቆዳአችንን ቀለም የሚሰሩ ሴሎች ብዙ ቀለም በማምረታቸው ነው፡፡ በዚህ የተነሳ ጠቆር ያለ የቆዳ ቀለም ያላቸው እና ነፍሰጡር ሴቶች ብዙን ጊዜ ለማድያት የተጋለጡ እንደሆነ ታውቋል፡፡

ጠቆር ያለ የቆዳ ቀለም ያላቸው ሰዎች ሜላኖሳይትስ (Melanoceytes) የተሰኘው የቆዳችንን ቀለም የሚሰሩ ሴሎች በብዛት ስላላቸው እነዚህም ሴሎች ብዙ ቀለም በማምረታቸው የተነሳ ነጣ ያለ ቆዳ ቀለም ካለቸው ሰዎች በበለጠ ሁኔታ ለማድያት እንደሚጋለጡ ይፋ አድርገዋል፡፡
.
ለማድያት መከስት አባባሽ ምክንያት ከሆኑት መካከል፡-
#1. በእርግዝና ጊዜ የሆርሞን መለወጥ፡- የሆርሞን መለወጥ ምክንያት
#2. የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎች መጠቀም
#3. ለጸሐይ መጋለጥ አንዱ የማድያት መከሰት ዋነኛ ምክንያት ሊሆን ይችላል
#4. አንዳንድ ለቆዳ እንክብካቤና ውበት መጠበቂያ ተብለው የሚሰሩ ምርቶች ቆዳችንን ሊያስቆጡ ይችላሉ፡፡
#5. በዘረመል አማካኝነት ከዚህ በፊት ከቤተሰቦቻችን ማድያት ያለበት ሰው ካለ ማድያት በእኛ ላይ የመከሰቱ ዕድል ሰፊ ነው
#6. ለተለያዩ ህመሞች ህክምና የሚሰጡ መድሃኒቶች (ለምሳሌ፡- የኤፕሌፕሲ መድሃኒት)

የማድያት ሕክምና አማራጮች፡-

ዋነኛዉ የህክምናዉ መሰረት ምከንያቱን በመለየት ማስወገድ ወይም ማስቀረት ሲሆን፤ በተጨማሪም ከታች የተዘረዘሩትን የመድሃኒት ክፍሎች እንዲጠቀሙ ሊደረግ ይችላል። ለምሳሌ፡- ከጸሃይ ራስን መከላከል (sun blocks መጠቀም)

#1. Hydroquinone ያለ ሐኪም ማዘዣ የሚሸጥ የቆዳ ሕክምና መድኃኒት ተመራጭ የሕክምና ዓይነት ነው፡፡ይህ መድኃኒት በሎሽን፣ በክሬምና በጄል መልክ የተዘጋጀ ስለሆነ የተመቾትን መርጠው ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡
#2. Corticosteroids እና Tretinoin ሁለተኛ ተመራጭ መድኃኒቶች ናቸው፡፡

#3. አልፎ አልፎ የቆዳ ሕክምና ስፔሻሊስቶች ከላይ የተጠቀሱትን የሁለቱን መድኃኒቶች ውህድ ሊያዙ ይችላሉ፡፡

#4. Azelaic acid ወይም Kojic acid ሌሎች የማድያት መድኃኒቶች ሲሆኑ ሁሉም መድኃኒቶች በቆዳችን ላይ የተለጠፉትን የጠቆሩ የማድያት ቀለሞችን በማንጣት ከቀሪው የሰውነታችን ቆዳ ቀለም ጋር በማመሳሰል ከፍተኛ ለውጥ በማምጣት በሕክምናው ዓለም የታወቁ ናቸው፡፡

#5.በህክምናዉ ጊዜ መድሃኒቶችን ዉጤታቸዉን በመጠበቅ ሳያዩ መቀያየር ህክምናዉን ዋጋ ሊያሳጣዉ ስለሚችል፣ መድሃኒት ከመቀያየር በፊት የቆዳ ስፔሺያሊስት ሃኪም ማማከሩ ተገቢ ነዉ።
መልካም ቀን !

ስለ ጤና የቴሌግራም ቻናል ! @seltena ጤናማ ኢትዮጵያ (Healthy Ethiopia !)
1.5K views16:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-14 19:35:12 ስለ ጤና የቴሌግራም ቻናል pinned «ጭንቀትና ስነ ልቦናዊ መፍትሔው # ጭንቀት ምንድን ነው? ጭንቀት የሰውነትን ተፈጥሯዊ ሚዛን የሚያዛባ የአካል፣የአዕምሮና የስሜት ትንኮሳ(stimulus) የሚፈጥረው ምላሽ፣ ወይም የአንድ ሰው ፍላጎት (demand) ሊያንቀሳቅሰው ከሚችለው የግልና የማህበራዊ ሃብቶች አቅም በላይ ሆኖ ሲታየው የሚፈጠር ስሜት፣ ወይም ነገሮች ና ሁኔታዎች ከቁጥጥራችን እንደወጡ ስናስብ የሚፈጠር ስሜት ነው፡፡ መጠኑና ጊዜው…»
16:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-14 19:33:54 ጭንቀትና ስነ ልቦናዊ መፍትሔው

# ጭንቀት ምንድን ነው?
ጭንቀት የሰውነትን ተፈጥሯዊ ሚዛን የሚያዛባ የአካል፣የአዕምሮና የስሜት ትንኮሳ(stimulus) የሚፈጥረው ምላሽ፣ ወይም የአንድ ሰው ፍላጎት (demand) ሊያንቀሳቅሰው ከሚችለው የግልና የማህበራዊ ሃብቶች አቅም በላይ ሆኖ ሲታየው የሚፈጠር ስሜት፣ ወይም ነገሮች ና ሁኔታዎች ከቁጥጥራችን እንደወጡ ስናስብ የሚፈጠር ስሜት ነው፡፡

መጠኑና ጊዜው ይለያይ እንጂ ጭንቀት የማይነካው ሰው እንደሌላ ይታወቃል፡፡ በአንድ ወቀት በአንድ ኮሌጅ ውስጥ የሳይኮሎጂ ኮርስ ሳስተምር አንድ ተማሪ አንድ ከፍተኛ ባለስልጣንን ጠቅሶ “እንዴት እሳቸው ይጨነቃሉ?” በማለት ሰውየው ከማንኛውም ጭንቀት በየትኛውም ሁኔታና ጊዜ ነፃ ናቸው ብሎ እንደሚያምን ገልጾ እንደተሟገተ ትዝ ይለኛል፡፡

ሆኖም በየትኛውም የስልጣን እርከን ወይም የሥራ ሃላፊነት ላይ ብንሆን በጥቂቱም ቢሆን በተለያየ ጊዜና ሁኔታ ጭንቀት ወደ እኛ ሊመጣ ይችላል፡፡ የሚወጡ ሳይንሳዊ መረጃዎች ደግሞ ሃላፊነትና ውሳኔ ሰጪነት ሲጨምር ጭንቀት እንደሚጨምር ይጠቁማሉ፡፡ ለዚህም ነው ባለስልጣናት፣ ስራ አሰኪያጆች፣ ዲሬክተሮች፣ ሥራ ሃላፊዎች በጭንቀት መቆጣጠሪያ (stress management strategies) ስልቶች እንዲሰለጥኑ መደረግ ያለበት፡፡

በማንኛውም ደረጃ የሚሰራና ከስራ ውጪም የሆነ ሰው የጭንቀት መቆጣጠሪያ ስልቶችን መሰልጠኑ፤ማወቁና መተግበሩ የተረጋጋ ህይወት እንዲመራ ይረዳዋል፡፡ ጭንቀት ውሳኔን የማዛባትና ትኩረትን የመቀነስ ሃይል ስላለው የጭንቀት መቆጣጠሪያ ስልቶችን ማወቅና መሰልጠን ይገባቸዋል፡፡

#የጭንቀት ምንጮች ምንድን ናቸው?

የጭንቀት ምክኒያቶች በርካታ ናቸው፡፡ ሆኖም በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች ለይቶ ማየት ይቻላል፡- አካላዊና ስነ ልቦናዊ ምንጮች፡፡
እነዚህም የሚከተሉትን ሊያጠቃልል ይችላል፡-
• በስራ ቦታ በሚፈጠር የሥራ ጫና እና የሥራ አሰራር ግልፅነት ማጣት
• ከሚወዱት ሰው ጋር የሚፈጠር ችግር
• መሰረታዊ የኢኮኖሚ ግዴታዎችን መወጣት አለመቻል፡- ለምሳሌ የቤት ኪራይ፣ አስቤዛ፣ ወርሃዊ የመብራት ክፍያ ወዘተ…
• ለአዳዲስ ነገሮች አለመዘጋጀት፡- ለምሳሌ ልጅ መወለድ፣ አዲስን ስራ መያዝ
የትራፊክ መጨናነቅ
ከፍተኛ ድምፅ ህመም
• ከፍተኛ የአየር ሁኔታ፡- ለምሳሌ ከባድ ሙቀት ወይም ከባድ ቅዝቃዜ
• አካላዊ ህመም፣እንቅልፍ ማጣት፣ከመጠን ያለፈ አልኮል መጠጣትና ሲጋራ ማጨስ በሰውነት ላይ የሚፈጥሩት ጫና ወዘተ ናቸው
ቲምና ፔተርሰን (Timm and Peterson) የተባሉ ምሁራን በተለይ በሥራ አካባቢ የጭንቀት ምንጮች

የሚላቸውን እንደሚከተለው ይዘረዝራሉ።
ውጤታማ ያልሆነ ተግባቦት (Communications)
አግባብነት የጎደለው የመስሪያ ቤት አሰራር ከመጠን በላይ የሆነ የመረጃ ብዛት ወጥ ያልሆነ የሥራ አስኪያጆች ወይም የመሪዎች ባህሪ ከመጠን ያለፈ የስራ ብዛት ወይም ጫና አዲስ ሥራ መግባት የግል ችግሮች ጭንቀትን የሚዘሩ ግለሰቦች- በንግግራቸው ሁሉ ጭንቀት የሚፈጥር ወሬን የሚያወሩ (Stress carriers ይባላሉ)
የ ድርጅቶች ደሞዝ፣ፖሊሲ እና የስራ አካባቢ(working conditions)
የሥራ ቦታዎች ከፍተኛ ሙቀት ወይም ቅዝቃዜ፣ ከፍተኛ ብርሃን ወይም ድንግዝታ ለጭንቀት መነሻዎች እንደሆኑ በፃፉት መፅሃፍ ላይ ይገልፃሉ፡፡

#የጭንቀት ውጤቶች ምንድናቸው?
•የሰውነት ድካም
•ከፍተኛ የራስ ምታት
•ብስጭት
•የምግብ ፍላጎት መዛባት
•የማስታወስ ችሎታ መቀነስ
•ለራስ የሚሰጥ ዋጋ ወይም ክብር መቀነስ(low self-esteem)
•ከማህበራዊ ህይወት መገለል
•የ ደም ግፊት መጨመር
•ትንፋሽ ማጠር
•የወሲብ ፍላጎት መቀነስ
•የእንቅልፍ መዛባት
•የጨጓራና አንጀት ስርዓት መዛባት ወዘተ

ከእነዚህም በተጨማሪ ጭንቀት የልብ ህመምን፣ የቆዳ ችግርን(skin disorders) እና ሜታቦሊዝምን (በሰውነታችን ውስጥ የሚካሄዱ ኡደቶችን)የማዛባት አቅም አለው ተብሎ ይታመናል፡፡ በተጨማሪም ለስነልቦናዊ ቀውሶች ለምሳሌ፡- ለፍርሃትና ለድብርት ይዳርጋል፡፡ ጭንቀት ስነልቦናዊ ችግር ነው ቢባልም አካላዊ ተፅእኖን ይፈጥራል፡፡

#ጭንቀትን ለመቀነስ ምን ማድረግ አለብን ?

ከላይ የተጠቀሱት ምሁራን ለጭንቀት መላ ይሆናሉ ያሉትን መፍትሄዎች እንደሚከተለው ዘርዝረዋል፡-
ለአፍታ ዞር ይበሉ፡- ጭንቀት ከፈጠረብዎ ሁኔታ ወይም ሌላ ምንጭ ዞር ይበሉና የማሰቢያና የማሰላሰሊያ ጊዜ ይውሰዱ፡፡

ያውሩት፣ይናገሩት፡-ለቅርብና ለሚያምኑት ሰው የጭንቀትዎን ስሜት ይናገሩ፡፡ ባወሩ ቁጥር ይቀልልዎታል፡፡
ወጣ ብለው የሚወዱትን ይጫወቱ፡- የእግር ጉዞ ያድርጉ፣ ደረጃዎችን ወደ ላይና ወደ ታች ይውጡ፡፡
አንዳንዴ እጅ ይስጡ፡- ለምሳሌ እርስዎና ባለቤትዎ ወይም አለቃዎ “ይሄ ነው ትክክል ያኛው ነው ትክክል ” እያሉ ሙግት ከገቡና ጉዳዩ ብዙ ለወጥና ተፅዕኖ የማያመጣ ከሆነ ችላ ይበሉት፤ አንዳንዴ እያወቁ ይተውት፡፡

#ለሌሎች መልካም ነገር ያድርጉ፡-በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ሲገቡና ሃዘን ውስጥ ሲሆኑ ችግረኞችን በመርዳትና ልገሳ በማድረግ ይሳተፉ፤ ቀለል ይልልዎታል፡፡
በአንድ ጊዜ አንድን ነገር ይስሩ፡- ሁሉንም ነገር በአንድ ጊዜ ለመስራት መሞከር ጭንቀትን ስለሚያባብስ እንደ ስራዎቹ ጠቃሚነትና አስቸኳይነት ቅደም ተከተል በማሲያዝ በአንድ ጊዜ አንድን ነገር ይስሩ፡፡

የታላቁን ሰው ፍላጎት አድብ ግዛ ይበሉት፡-አንዳንዴ የራስዎንም ሆነ የሌሎች ሰዎችን ችግር በሙሉ ራስዎ መፍታት እንደሚችሉ ማሰብዎ “በውስጥዎ ያለው የሃሰተኛው ትልቅ ሰው urge of superman” ምክር ነውና አድብ ግዛ ይበሉት፡፡ እርስዎ የሁሉንም ሰው ችግር ፈቺ አይደሉም !!

ትችትን መቋቋም ይለማመዱ፡- አንዳንድ ሰው ትንሽ ትችት እንቅልፍ ትነሳዋለች፡፡ በተጨማሪም ሌሎችንም ከመተቸት ይቆጠቡ። ቶማስ ፍሬድማን የ “ The world is flat” ፀሃፊ በዚህ አለም አንድ መንደር በሆነችበት ግሎባላይዜሽን ዘመን ለትችት ቆዳህን አወፍር (Make your skin thick) ብሎ ይመክራል፡፡
ለሌሎች ራስህን አስገኝ፡- ሰዎች ሲፈልጉህ ተገኝላቸው፡፡
#ብቸኝነት የጭንቀት ምክኒያትም ሊሆን ስለሚችል፡፡
ራስህን ለማዝናናት ጊዜ ውሰድ፡-ዘና ማለት፣መጫወት፣ አዳዲስ ነገሮችን መጎብኘት መንፈስን ያድሳል፣ ጭንቀትንም ይቀንሳል፡፡
ቆፍጣና ሁን፡- በቀን ወስጥ የምትሰራውን፣ የምትሄድበትን ሥፍራ፣ የምታገኘውን ሰው በትክክል ለይተህ በማወቅ ዝርክርክነትን አስወግድ።

መልካም ቀን !

ዶ/ር ዮናስ ላቀው
(ስነ አእምሮ ሀኪም (ሳይካያትሪስት))

ይህን መርጃ ለወዳጆ ያጋሩ ወደ " ሰለ ጤና " የቴሌግራም ቻናል ይጋብዙ! @seltena

ጤናማ ኢትዮጵያ (Healthy Ethiopia !)
1.5K viewsedited  16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-10 18:06:14 ለመላው ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን እንኳን ለ2014 ዓመተ ምህረት ዘመን መለወጫ በዓል አደረሳችሁ::
አዲሱ ዓመት #የሰላም ÷#የፍቅር እንዲሁም #ፈጣሪን #የመፍራት #ዓመት ይሁንልን ::

የሰለ ጤና 'አድሚን' ዶክተር ዳንኤል ሞገስ ::
ጤናማ ኢትዮጵያ
1.8K viewsedited  15:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-01 20:14:09 ጥራት እና ብዛት?
ለባለትዳሮች . . .

በፍቅር የመጀመሪያ ወራትና አልፎም በእጮኝነት ወራቶች ሁለት ፍቅረኛሞች ተገናኝተው አይጠግቡም፤ ሲገናኙም ትኩረታቸውን በሙሉ በፍቅረኛቸው ላይ ያደርጋሉ፡፡ ከዚያም ሲለያዩ እንደገና የሚገናኙበትን ቀን ይናፍቃሉ፡፡ ያም ሳያንስ በአካል ከተገናኙ በኋላ ሲለያዩ በስልክ እያወሩ ይሄዳሉ፡፡ እቤት ሲገቡም ሆነ በሌላ ቦታ ሆነው አብሮነቱን በማሕበራዊ ሚዲያ “ቻት” በማድረግ ይቀጥሉታል፡፡ ይህ “ጥራት” እና “ብዛት” ያለው ግንኙነት ከትዳር በኋላ የሚዘልቅላቸው ሰዎች ግን ቁጥራቸው ብዙ እንዳልሆነ ጥናትም ሆነ የግል ልምምድ ይነግረናል፡፡

አንዳንድ ሰዎች ባልና ሚስት (እንዲሁም ከልጆች ጋር) ጥራት ያለው ጊዜ እስካሳለፉ ድረስ የሚገኛኙበትና አብረው የሚያሳልፉበት ጊዜ ብዙና ረጅም መሆን የለበትምነ ብለው ያስባሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ ባልና ሚስት ቤትም ሆነ ውጪ (ስራ፣ ንግድ …) ረጅም ጊዜ አብረው እስካሳለፉ ድረሰ ጥራት ምናምን የሚባል ነገር የለም ብለው ያስባሉ፡፡

እነዚህ ሁለት አብሮ የማሳለፍ ገጽታዎች የራሳቸው የሆነ ጥቅም ቢኖራቸውም በራሳቸው ብቻ ሙሉ እንዳልሆኑ ማሰብ ግን አስፈላጊ ነው፡፡ ባልና ሚስት ጤናማ የትዳር ግንኙነት የሚኖራቸው የቻሉትን ያህል አብረው ሲያሳልፉና ከዚያም በተጨማሪ አብረው የሚያሳልፉት ጊዜ የእርስ-በርስ ትኩረት የሚሰጣጡበት ጥራት ያለው ሲሆን ነው፡፡

በብዛት ማሳለፍ ከሚያካትታቸው ነገሮች መካከል፡- በጊዜ እቤት መግባት፣ በትርፍ ጊዜ አብሮ መውጣትና መግባት፣ አብሮ ለመመገብም ሆነ ለመዝናናት ወጣ ማለትና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡

በጥራት ማሳለፍ ከሚያካትታቸው ነገሮች መካከል፡- አብረው ሲሆኑ ከማሕበራዊ መገናኛዎች መቆጠብ፣ እቤት ሲሆኑ ቴሌቪዥን የሚከፈትባቸውን ጊዜያት ሚዛናዊ ማድረግ፣ የውጪ ሰዎች ግርግር የማይበዛበት የቤት ውሎ ጊዜ ማዘጋጀት፣ መነጋገርና ማውራት እና የመሳሰሉት ይገኝበታል፡፡

ከትዳር አጋራችሁ ጋር የምታሳልፉትን ጊዜ ከብዛትና ከጥራት አንጻር ብትመዝኑት ከ10 ስንት ትሰጡታላችሁ?
እስቲ ከትዳር አጋራችሁ ጋር ጥራት ያለውን ጊዜ ወስኑና በዚህም ጉዳይ ላይ ተወያዩበት፡፡

#ምንጭ--->#ዶክተር እዮብ ማሞ #(የስነ ልቦና ሙሁር እና የ "25 ስኬት ቁልፎች "ደራሲ. ከዶክተር እዮብ ገፅ የተወሰደ ::
2.0K viewsedited  17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-01 20:14:09
1.5K views17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ