Get Mystery Box with random crypto!

ማድያት (Melasma) *********** ማድያት በዋናነት በፊታችን ቆዳ ላይ በቀለም መዛባት የሚ | ስለ ጤና የቴሌግራም ቻናል 🔍💊💉

ማድያት (Melasma)
***********
ማድያት በዋናነት በፊታችን ቆዳ ላይ በቀለም መዛባት የሚፈጠር የቆዳ ችግር ዓይነት ነው፡፡ በዚህ የተናሳ የፊታችን ቆዳ ቡናማ ወይም ግራጫ ቀለም ያለው ነገር ይለጠፍበታል፡፡

ማድያት ብዙ ጊዜ ለጸሐይ በተጋለጠው የሰውነታችን ክፍል በሆኑት በአፍንጫችን ፣በግንባራችን፣ በጉንጭና በላይኛው ከንፈራችን ላይ የሚወጣ ሲሆን አንዳንዴም ክንዳአችን፣ አንገታችንና ትከሻችን ላይ ሲወጣ ይስተዋላል፡፡

እስከ አሁን ድረስ ሐኪምች የማድያት መከሰት ምክንያትን መነሾ ሙሉ በሙሉ በውል ያላወቁ ሲሆን ይሁንና በተደጋጋሚ በተደረጉ የጥናት ግኝቶች ለማድያት መከሰት አስተዋጾ አለው ተብሎ የታመነው የቆዳአችንን ቀለም የሚሰሩ ሴሎች ብዙ ቀለም በማምረታቸው ነው፡፡ በዚህ የተነሳ ጠቆር ያለ የቆዳ ቀለም ያላቸው እና ነፍሰጡር ሴቶች ብዙን ጊዜ ለማድያት የተጋለጡ እንደሆነ ታውቋል፡፡

ጠቆር ያለ የቆዳ ቀለም ያላቸው ሰዎች ሜላኖሳይትስ (Melanoceytes) የተሰኘው የቆዳችንን ቀለም የሚሰሩ ሴሎች በብዛት ስላላቸው እነዚህም ሴሎች ብዙ ቀለም በማምረታቸው የተነሳ ነጣ ያለ ቆዳ ቀለም ካለቸው ሰዎች በበለጠ ሁኔታ ለማድያት እንደሚጋለጡ ይፋ አድርገዋል፡፡
.
ለማድያት መከስት አባባሽ ምክንያት ከሆኑት መካከል፡-
#1. በእርግዝና ጊዜ የሆርሞን መለወጥ፡- የሆርሞን መለወጥ ምክንያት
#2. የወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብሎች መጠቀም
#3. ለጸሐይ መጋለጥ አንዱ የማድያት መከሰት ዋነኛ ምክንያት ሊሆን ይችላል
#4. አንዳንድ ለቆዳ እንክብካቤና ውበት መጠበቂያ ተብለው የሚሰሩ ምርቶች ቆዳችንን ሊያስቆጡ ይችላሉ፡፡
#5. በዘረመል አማካኝነት ከዚህ በፊት ከቤተሰቦቻችን ማድያት ያለበት ሰው ካለ ማድያት በእኛ ላይ የመከሰቱ ዕድል ሰፊ ነው
#6. ለተለያዩ ህመሞች ህክምና የሚሰጡ መድሃኒቶች (ለምሳሌ፡- የኤፕሌፕሲ መድሃኒት)

የማድያት ሕክምና አማራጮች፡-

ዋነኛዉ የህክምናዉ መሰረት ምከንያቱን በመለየት ማስወገድ ወይም ማስቀረት ሲሆን፤ በተጨማሪም ከታች የተዘረዘሩትን የመድሃኒት ክፍሎች እንዲጠቀሙ ሊደረግ ይችላል። ለምሳሌ፡- ከጸሃይ ራስን መከላከል (sun blocks መጠቀም)

#1. Hydroquinone ያለ ሐኪም ማዘዣ የሚሸጥ የቆዳ ሕክምና መድኃኒት ተመራጭ የሕክምና ዓይነት ነው፡፡ይህ መድኃኒት በሎሽን፣ በክሬምና በጄል መልክ የተዘጋጀ ስለሆነ የተመቾትን መርጠው ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡
#2. Corticosteroids እና Tretinoin ሁለተኛ ተመራጭ መድኃኒቶች ናቸው፡፡

#3. አልፎ አልፎ የቆዳ ሕክምና ስፔሻሊስቶች ከላይ የተጠቀሱትን የሁለቱን መድኃኒቶች ውህድ ሊያዙ ይችላሉ፡፡

#4. Azelaic acid ወይም Kojic acid ሌሎች የማድያት መድኃኒቶች ሲሆኑ ሁሉም መድኃኒቶች በቆዳችን ላይ የተለጠፉትን የጠቆሩ የማድያት ቀለሞችን በማንጣት ከቀሪው የሰውነታችን ቆዳ ቀለም ጋር በማመሳሰል ከፍተኛ ለውጥ በማምጣት በሕክምናው ዓለም የታወቁ ናቸው፡፡

#5.በህክምናዉ ጊዜ መድሃኒቶችን ዉጤታቸዉን በመጠበቅ ሳያዩ መቀያየር ህክምናዉን ዋጋ ሊያሳጣዉ ስለሚችል፣ መድሃኒት ከመቀያየር በፊት የቆዳ ስፔሺያሊስት ሃኪም ማማከሩ ተገቢ ነዉ።
መልካም ቀን !

ስለ ጤና የቴሌግራም ቻናል ! @seltena ጤናማ ኢትዮጵያ (Healthy Ethiopia !)