Get Mystery Box with random crypto!

#ፅንስ ማስወረድ እና አደጋዎቹ #ፅንስ ማስወረድ ምንድን ነው? ሴቶች ሳያስቡት ወይም ሳይወጥኑት | ስለ ጤና የቴሌግራም ቻናል 🔍💊💉

#ፅንስ ማስወረድ እና አደጋዎቹ

#ፅንስ ማስወረድ ምንድን ነው?
ሴቶች ሳያስቡት ወይም ሳይወጥኑት ፅንስ ቢያስወርዳቸው የፅንስ መጨንገፍ ወይም ውርጃ ይባላል።
# ነገር ግን በፍላጎት ሆነ በእቅድ ፅንስን ለማስወገድ የሚደረግ ክንዋኔ ፅንስ ማስወረድ ይባላል።
ፅንስ ማስወረድ በተመለከተ የጤና ባለሙያዎች እና የሲቪል ማህበራት ያላቸው አስተያየት በሁለት ጎራ ይከፍላቸዋል።
የመጀመሪያው ፅንስ ማቋረጥ የሴቷ መብት ነው። በመሆኑም ይህ መብት በህግም ሆነ በአገልግሎት አለማቅረብ ሳቢያ መገደብ የለበትም የሚል ሲሆን
በሌላ በኩል ደግሞ
2ኛው ፅንሱ ህይወት ያለው ፍጡር በመሆኑ ፅንስ ማስወረድ አውቆ እና ሆን ብሎ ህይወት እንደማጥፋት ይቆጠራል የሚሉ ወገኖች አሉ።

በአገራችን ያሉ ትላልቅ ሃይማኖቶችም ቢሆኑ ፅንስ ማስወረድን ይቃወማሉ።

በፅንስ ማስወረድ ሕጋዊ መሆን አለመሆን ያለው ውዝግብ በአገራችን ብቻ ሳይሆን በሁሉም አገሮች ውስጥ የሚካሄድ ነው። የዚህ ፅሁፍ አላማ ከአንደኛው ወይም ከሌላኛው ጋር መወገን ሳይሆን በፅንስ ማስወረድ ዙሪያ ያሉትን እውነታዎችና አደጋዎች ለማያውቁ ማሳወቅ ነው።

#ሴቶች ፅንስ የሚያስወርዱት ለምንድን ነው?
ሴቶች ፅንስ የሚያስወርዱት አስገዳጅ ሁኔታዎች በሚያጋጥማቸው ጊዜ ነው። ሴቶች ፅንስ ለማቋረጥ የሚገደዱበት የተለያዩ ምክንያቶች አሉ
● በቂ ልጆች ስላሏቸው ተጨማሪ ልጅ ለማሳደግ ስልማይችሉ
● ባለማግባታቸው ምክኒያት ልጅ ብቻቸውን ማሳደግ ስለማይፈልጉ
● ከባለቤታቸው ጋር በሚፈጠሩ ችግሮች ምክኒያት
● በጽንሱ ላይ የሆነ የአፈጣጠር ችግር እንዳለ ከታወቀ
● እርግዝናው ለጤናቸውም ሆነ ለሂወታቸው አደገኛ ከሆነ
● እርግዝናው የመጣው በአስገድዶ መደፈር ከሆነ

#ፅንስ የሚቋረጠው እንዴት ነው?

ፅንስ ለማስወረድ ሁለት ዋና ዋና መንገዶች አሉ
● በመድኃኒት ፅንስ ማስወረድ
እርግዝናዎን ለማቆም ክኒን ይወስዳሉ። ይሄ እስከ 10 ሳምንታት ድረስ ላለ እርግዝና ይሆናል። የመድሃኒት ውርጃ የመረጡ ሴቶች 2 የተለያዩ መድሃኒቶች መውሰድ አለባቸው።
● በሕክምና መሳሪያ የተደገፈ (MVA) ፅንስ ማስወረድ
ሐኪም እርግዝናን ለማስቆም የቀዶ ጥገና መሣሪያዎችን ይጠቀማል። ይህ በመጀመሪያው ወይም በሁለተኛ ወር ውስጥ ላለ እርግዝና ለማስወረድ ሊከናወን ይችላል። ሂደቱ (ፕሮሲጀሩ) ከ 15 እስከ 30 ደቂቃዎች ይወስዳል ነገር ግን አብዛኛዎቹ ሴቶች ክሊኒኩ ውስጥ ለጥቂት ሰዓታት ለክትትል ይቆያሉ።

በመድሃኒት ውርጃ ከተፈጸመ በኋላ የሕመም ምልክቶች ይታዩኛል?
አዎ ሁለተኛውን መድሃኒት ከወሰዱ በኋላ
● የታችኛው የሆድ ህመም እና ቁርጠት ይኖራል። እነዚህ ህመሞች እስከ 6 ሰዓታት የሚቆዩ ናቸው።
● ከማህጸን ውስጥ መድማት
ለጥቂት ሰዓቶች ከባድ ሊሆን ይችላል ከዚይም ቀላል የደም መፍሰስ ለጥቂት ሳምንታት ሊቀጥል ይችላል
● ትኩሳት, ማቅለሽለሽ, ማስታወክ እና ተቅማጥ

# በሕክምና መሳሪያ ይምታገዝ ውርጃ (MVA) ከተደረገ በኋላ የሕመም ምልክቶች ይኖራቸው ይሆን?
አዎ ይኖራቸዋል
● በታችኛው ሆድ ውስጥ ህመም እና ቁርጠት። ይህ ለጥቂት ሰዓታት ይቆያል
● ከማህጸን ውስጥ መድማት
ይህ አብዛኛውን ጊዜ ቀላል ሲሆን መድማቱ እስከ 2 ሳምንታት ሊቆይ ይችላል !!

14 ወይም ከዚያ በላይ ሳምንታት እርጉዝ ከሆንኩኝ ፅንስ ማስወረድ እችላለሁ?
ሴቶች በሚኖሩበት ሃገር በተወሰነው ህጋዊ ገደብ ድረስ ማስወረድ ይችላሉ። በብዙ አገሮች ህጋዊ ገደቡ ከ 20 እስከ 24 ሳምንታት ድረስ ነው። ከ14 ሳምንቶች በኋላ የሚደረግ የፅንስ ማስወረድ ረዘም ያለ ጊዜ ሊወስድ ይችላል። ይሁን እንጂ አሁንም መድሃኒት ወይም በሕክምና መሳሪያ ይምታገዝ ውርጃ (MVA) ወይም ሁለቱንም ዘዴዎች መጠቀም አስፈላጊ ሊሆን ይችላል።

#ፅንሱን ካስወረድኩኝ በኋላ ከቀጠሮዬ ውጪ ሐኪም ማማከር የሚኖርበት ሁኔታዎች አሉ?
አዎ ከስር የተዘረዘሩት የአደጋ ምልክቶች ካዪ ወዲያውኑ የህክምና እርዳታ ማግኘት አለብዎ
● ከፍተኛ መጠን ያለው ከማህጸን ደም መፍሰስ
● የህመም ማስታገሻ ክኒን ቢውስዱም የማይታገስ ከባድ ቁርጠት
● ከፍ ያለ ትኩሳት (ከ38.5ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ በላይ የሆነ ትኩሳት)
● መጥፎ ጠረን ያለው የሴት ብልት ፈሳሽ
● ህሊና መሳት ወይም መዘባረቅ
እንዚህ ምልክቶች ካዩ የህክምና እርዳታ ማግኘት አለብዎ!
አንዳንድ ጊዜ ፅንሱ ሙሉ በሙሉ ላይወጣ ይችላል። በዚህ ጊዜ የሚከተሉት ምልክቶች ሊታዩ ይችላሉ :-
● መድሃኒት ከተሰጠ በኋላ መድማት አይኖርም
● አሁንም ቢሆን የእርግዝና ምልክቶች እንደ ማቅለሽለሽ እና የጡት ህመም ይኖራሉ
● ፅንስ ካወረዱ ከሁለት ሳምንታት በኃላ የማህጸን መድማት
● ውርጃ ከፈጸሙ በኋላ በነበሩት ስድስት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ የወር አበባ አለማየት

#ፅንስ ማስወረድ አደጋ አለው?
በአጠቃላይ በሰለጠነ ባለሞያ እና በጤና ተቋም የሚደረጉ ውርጃዎች በጣም አስተማማኝ(safe )ናቸው። ነገር ግን ልክ እንደ ማንኛውም የሕክምና ሂደት ጽንስ ማስወረድ አንዳንድ አደጋዎች ሊያጋጥሙ ይችላሉ። ከስር የተዘረዘሩት ከፅንስ ማስወረድ በኋላ ሊከሰቱ የሚችሉ የጤና ችግሮች ናችው ።
1. ከማህጸን ብዙ ደም መፍሰስ
2. ኢንፌክሽን
3. የሆድ ውስጥ አካላት(የሆድቃ)መጎዳት

NB
#ፅንስ ማስወረድ በሚቀጥሉት አይነት ሁኔታዎች ከተካሄደ አደገኛ አይደለም ተብሎ ይታሰባል።
● በአግባቡ በሰለጠኑ እና ልምድ ባላቸው የጤና ባለሙያ ከተሰጠ
● ንፅህናቸው በተጠበቀ የህክምና መሳሪያዎች ከተሰራ

#በሌላ በኩል ደግሞ ፅንስ ማስወረድ አደገኛ የሚሆንበት ሁኔታ
● በጤና ባለሙያ ካልተካሄደ ወይም ጤና ባለሙያው በቂ ልምድ ከሌለው
● ለፅንሥ ማስወረጃ የማይሆኑ መድሃኒቶች እና መሳሪያዎች መጠቀም
● መሳሪያዎቹ ሆኑ አከባቢው ንጽህና ከሌላቸው
በከፍተኛ ጭንቀት ላይ ያሉ ሴቶች ጽንስ ለማስወረድ ብዙ አይነት ያልተገቡ ሙከራዎች ያደርጋሉ እናም እራሳቸው ለአደጋ ያጋልጣሉ።

አደገኛ በሆኑ ፅንስ የማስወረድ ተግባራት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሴቶች ለሞት ፣ ለኢንፌክሽን እና ለመሃንነት ይዳረጋሉ።

ፅንስ ለማስወረድ ከመወስኖ በፊት አቅራብያዎ ወደ ሚገኝ ጤና ተቋም በመሂድ ስለ ጉዳዩ የጤና ባለሞያዎችን ያማክሩ !!

=> ጥያቄ ለመጠየቅ እና በዚህ ቻናል በሚውጡ ፅሑፎች ላይ አስተያየት ለመስጠት ለምትፈልጉ https://t.me/joinchat/መትቭ hYG2fFyiVaF3nspAA ግሩፕ ላይ መስጠት ትችላላቹ !!

ስለ ጤና ቻናል @seltena
ጤናማ ኢትዮጵያ (Healthy Ethiopia !)