Get Mystery Box with random crypto!

️ ንስር አማራ🦅

የሰርጥ አድራሻ: @nisireamhra
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 31.84K
የሰርጥ መግለጫ

የተቀደሰን ነገር በእግሩ ለሚረግጥ ፥ ተመልሶም ያጎረሰውን እጅ ለሚናከስ ርኩስ መጫወቻ የማይሆን የነቃ ማህበረሰብ እስክንፈጥር ድረስ ብዕራችን አይነጥፍም።
አንድ አማራ ለሁሉም አማራ ፥ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ።
💚💛❤️
እኛን በውስጥ ለማናገር @NISIREamhraa_bot 👈 ይችን አድራሻ ይጠቀሙ🦅
ንስር አማራ🦅
#የግፉአን_ድምፅ
t.me/NISIREamhra

Ratings & Reviews

5.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

3

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-05-13 10:24:40 #ያልታወቁ_ኃይሎች

በአጠቃላይ 14 የባህርዳር ከተማ አመራሮች በአንድ መኪና እየሄዱ እያለ ባልታወቁ ኃይሎች መያዛቸው ታውቋል።

ተምሮ ከህዝብ ይወግናል በሚል ከትንሽ እስከ ትልቅ ላለው የብአዴን አመራር በተለያየ ጊዜ እድል ቢሰጥም፣ ነገር ግን መዘባነኑ የበዛ ሆኖ በመታየቱ ባልታወቁ ኃይሎች እጅ የገባ በሙሉ መጨረሻው ግልፅ ይመስላል።

ፑቲን በአንድ ወቅት እንዲህ እንዳለ ይነገራል - "ምህረት የፈጣሪ ስራ ነው፤ የእኔ ስራ እኩይ ፍጥረታትን ወደ እሱ (ወደ ፈጣሪ) መላክ ነው"።
BW

#ድል_ለአማራ_ፋኖ
#ድል_ለአማራ_ህዝብ

05/09/16 ዓ.ም

@NISIREamhra
7.9K views07:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-12 21:51:47
#አሳዛኝ_እልቂት
ሸዋሮቢት

በድሮን ጥቃት በርካታ ንፁሃን ተጨፈጨፉ!

በሸዋ ይፋት ቀጠና በቀወት ወረዳ የለን ቀበሌ ጉሎ  ትምህርት ቤት ላይ ዛሬ ግንቦት 4/2016 ዓ.ም ሁለት ጊዜ በተከታታይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት በርካታ ንፁሃን ተገድለዋል።

ከተገደሉት ውስጥ የትምህርት ቤቱ ሰራተኞች የሆኑ 4 መምህራን ይገኙበታል።

ከ27 በላይ ንፁሃን ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል። እግራቸውን እና እጃቸውን በድሮን ጥቃት ያጡት ወገኖች ህክምና ተቋም መድረስ ባለመቻላቸው ብዙ ደም ፈሷቸው ሕይወታቸው እያለፈ ነው ሲሉ ምንጮች ገልፀዋል።

ባለፉት 11 ወራት በዐማራ "ክልል" ከ90 ጊዜ በላይ የድሮን ጥቃት ተፈጽሞ 512 በላይ ንፁሃን መጨፍጨፋቸውን   ምንጮች አስተውሰዋል።

ግንቦት 4/2016 ዓ.ም


#ንፅሀንን_በመጨፍጨፍ_የሚፀና ወንበር የለም

#ድል_ለአማራ_ፋኖ
#ድል_ለአማራ_ህዝብ

04/09/16 ዓ.ም

@NISIREamhra
9.2K views18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-12 21:28:31
የአሸባሪው ቡድን መሪ አብይ አህመድ የባህርዳር ውሎ

#ድል_ለአማራ_ፋኖ
#ድል_ለአማራ_ህዝብ

04/09/16 ዓ.ም

@NISIREamhra
8.6K views18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-12 21:12:05 #ንገሪኝ_ሀገሬ

ንገሪኝ ሀገሬ እስኪ ምክንያትሽን ፣
አኩሪ ልጆችሽን ለምንድን ጠላሽን ፣
መጤውን አንግሰሽ ጣልሽው መሰረትሽን ፣
አማራ ነበረ አናፄ መቅደስሽ ጠባቂ ታሪክሽን ።
እንደዛሬው ሳይሆን መጤ ሳይነግስብሽ ፣
አንቺ ስትወጃቸው እነሱም ሲወዱሽ ፣
ወድ ህይወታቸውን ከፍለው ሲያስከብሩሽ ፣
እንደዚህ ነበረ የኖርሽው ተከብረሽ ፣
እሽ አሁን የት ሄደ ያ ሁሉ መውደድሽ ።
አረ ተይ ሀገሬ ይሄ በጣም ግፍ ነው ፣
አርበኛን አሳዶ ምን አይነት ክብር ነው ፣
ነው ወይስ ብልፅግና ማለት ታሪክን ማጥፋት ነው ።
ቆይ ግን ለምንድን ነው ሞት የታወጀብን? ፣
ክብርሽን ጠብቀን እዚ ባደረስን ።
እስኪ በአማራው ሞት ምን ትጠቀሚያለሽ ፣
ንገሪኝ ሀገሬ ለምን ትፈሪያለሽ ።
እድል ከሰጠሽኝ ንገረኝ ካልሽ እማ ፣
ብዙ እነግርሽአለሁ ጆሮሽ ብቻ ይስማ ።
ልንገርሽ ሀገሬ ግፍ እኮ ነው እሱ ፣
ወርቅ ላበደረሽ ጠጠር መመለሱ ።
ኸረ ተይ ሀገሬ እንዲህ አትርሻቸው ፣
ለክብርሽ የሞቱ ትንሽ ሳይሰስቱ ስለህይወታቸው ፣
ባለ ታሪክ ጀግኖች አማራዎች ናቸው ፣
ይወቅስሽ አይደለ ደምና አጥንታቸው ።
አሸባሪ የሚል አዲስ ስም ሲሰጠን ፣
እውነት ይህ ነው ለኛ ማግኘት የሚገባን ?፣
እውነት ነው ይህ ነገር አንቺም ወስነሻል ?፣
አሸባሪነቱ ለኛ ይመጥናል ? ።
ስለሚፈሩን ነው አሸባሪ ሆነን? ይህን ስም የሰጡን፣
ንገሪኝ ሀገሬ ልወቀው እውነቱን ።
ቆይ ግን ምን በደልንሽ ምንስ አደረግንሽ ? ፣
ሁሉም የሚጠላን ሆነናል ልጆችሽ  ።
ሁሉም ምኞቱ ነው እኛ እንድንጠፋ  ፣
ንገሪኝ ሀገሬ ምን ስላጠፋ ነው አማራ እሚገፋ  ።
ንገሪኝ ሀገሬ በየትኛው ሀገር እንዲህ ይደረጋል ፣
እንዴት መጤ ነግሶ ባለ ሀገር ይሞታል ።
ባለ ሀገር በመጤ ሆኖ ማላገጫ ፣
ምን አይነት ውድቀት ነው አዘቅዝቆ ሩጫ ፣
በሰራነው ሀገር አጣን መቀመጫ ።
እስኪ በምን ቋንቋ ምን ብየ ላስረዳሽ ፣
ኢትዮጵያ የአማራ ውለታ እንዳለብሽ፣
በደም በአጥንቱ ነው የኖርሽው ተከብረሽ ።
በዘረኛ መንጋ ቢፈርስም ቤታችን ፣
ከቤት አፈናቅለው ጎዳና ቢጥሉን ፣
እኛ ለክብራችን ፋኖ ነው ህልማችን ፣
ቤትም አንፈልግም ጫካ ነው ቤታችን ፣
ለማስመለስ ብለን ማንነት ክብራችን ፣
ትግል ጀምረናል አንስተን ነፍጣችን  ፣
አራት ኪሎን አድርገን ለመዳረሻችን ።


ንገሪኝ ኢትዮጵያ (ፀሀፊ የንስር አማራ ቤተሰብ የአዴቱ )

#ድል_ለአማራ_ፋኖ
#ድል_ለአማራ_ህዝብ

04/09/16 ዓ.ም

@NISIREamhra
8.4K views18:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-12 18:36:58 የኦነግ ብልፅግና መሪ ከባህርዳር ፈረጠጠ…

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የባሕር ዳሩን ፕሮግራም አቋርጠው ወደ መጡበት መመለሳቸው ተሰምቷል።

የአማራ ክልል መዲና በሆነችው ባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 11 ዙሪያ የተገነባው የዓባይ ድልድይ ምርቃ ሥነ ሥርዓት ላይ ከነባለቤታቸውና ከሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ጋር የታደሙት በአማራ ህዝብ ላይ ጦርነት ያወጁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ፡ ፕሮግራሙ ከሚካሄድበት አከባቢ በቅርብ ርቀት ላይ ፋኖ ተደጋጋሚ የሆነ የቦምብ ጥቃት በመፈፀሙ የምረቃ ሥነ ሥርዓቱን አቋርጠው በመጡበት ሄሊኮፍተር ወደ አዲስ አበባ መመለሳቸውን የአማራ ድምፅ ሚድያ የባሕር ዳር ከተማ ቅርንጫፍ ዘጋቢዎች ለማረጋገጥ ችለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሰሞኑ የምስራቅ ወለጋ ዋና መቀመጫ በሆነችው ነቀምቴ ከተማ ሄደው በሰላም መመለሳቸው የሚታወቅ ሲሆን ነገር ግን በዛሬው ዕለት የአማራ ክልል ርዕሰ መዲና ባሕር ዳር እንደ ምስራቅ ወለጋዋ ነቀምቴ ከተማ ሳትሆንላቸው ቀርታለች ነው የተባለው።

የዓባይ ድልድይ ምረቃ ሥነ ሥርዓት በሚካሄድበት ቀበሌ 11 ዙሪያ ፋኖ ተደጋጋሚ የሆነ የቦምብ ጥቃት የፈፀመ ሲሆን በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትሩና ባለቤታቸው ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እንዲሁም ሌሎች የፌደራልና የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት ተደናግጠው በሁለት ሄሊኮፍተር ተሳፍረው በአፋጣኝ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ መቀመጫ ወደ ሆነው መኮድ ካምፕ የሄዱ ቢሆንም፡ ነገር ግን በካምፑ ዙሪያም ተመሣሣይ የሆነ የቦምብ ጥቃት በመፈፀሙ በድጋሚ ሄሊኮፍተሮቻቸውን አስነስተው ወደ አዲስ አበባ መብረራቸውን ነው የአማራ ድምፅ ሚድያ የባሕር ዳር ከተማ ወኪሎች ያረጋገጡት።

ባለስልጣናቱ ተደናግጠው የድልድዩን ምረቃ ሥነ ሥርዓት ሳያጠናቅቁ ወደ መኮድ ካምፕ በሚበሩበት ወቅት፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከነ ባለቤታቸው ተሳፍረውበት የነበረው ሄሊኮፍተር በከፍታ ላይ የበረረ ሲሆን ነገር ግን በቅርቡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተደርገው የተሾሙት አቶ ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ ሌሎች ባለስልጣናትን የያዘችው ሁለተኛዋ ሄሊኮፍተር ዝቅ ብላ መብረሯን ዘጋቢዎቻችን ለመመልከት ችለዋል።

በከተማዋ ሆምላንድን ጨምሮ ባለስልጣናቱ ተሰባስበው ይገኙባቸዋል በተባሉ በተለያዩ ትላልቅ ሆቴሎች ላይ ከለሊት ጀምሮ  የቦምብ ጥቃት ሲፈፀም ማደሩም ነው የታወቀው።

በዚህም እስካሁን የታወቁ አንድ የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራርን ጨምሮ ከሚኒሊክ ክ/ከተማ በቁጥር ሦስት አመራሮች፣ ከፋሲሎ ክ/ከተማ ሁለት፣ ከቴዎድሮስ ክ/ከተማ አንድ አመራር ቆስለው ወደ ፈለገ ህይወት ሆስፒታል መወሰዳቸውንም ነው የአማራ ድምፅ ሚድያ የባሕር ዳር ወኪሎች ያረጋገጡት።

ከዚህ በተጨማሪ፡ የድልድዩ ምረቃ ስነ ስርዓት በተጀመረ በደቂቃዎች ውስጥ በቁጥር ከአምስት በላይ የሚሆኑ ሪፐብሊካን ጋርዶች ከነመሣሪያቸው የተሰወሩ ሲሆን፡ እነሱን ፍለጋ መነሻቸውን ከመኮድ ካምፕ ያደረጉ በርካታ ወታደሮች በከተማዋ መሰማራታቸው ታውቋል።


#ድል_ለአማራ_ፋኖ
#ድል_ለአማራ_ህዝብ

04/09/16 ዓ.ም

@NISIREamhra
8.7K viewsedited  15:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-12 16:53:46 #ሰከላ

ነበልባለለ የአማራ ፋኖ በጎጃም ሰከላ ብር አዳማ መሽጎ የሚገኜው የብርሃኑ ጁላ ጦር ከጠዎቱ ጀምሮ እየተለበለበ ሲሆን ነበልባሉ
#ምሽጉን በመስበር ብር አዳማን ፋኖ ተቆጣጥሯቷል

በተያያዘ መረጃ አበሰከን ላይ ብሬን እና ክላሾች ወደ ፋኖ ገቢ ሆነዎል

#ክብር_ለጀግኖቻችን
#ድል_ለአማራ_ፋኖ
#ድል_ለአማራ_ህዝብ

04/09/16 ዓ.ም

@NISIREamhra
8.9K views13:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-12 15:16:44 ዘንዶው ከሞርታር አምልጧል…

ወደ ባሕርዳር ከተማ ለዲስኩር የሄደው ዘንዶዉ ከሶስት የሞርታር ጥቃት አምልጧል። ይህንንም ተከትሎ በአዲሱ የአባይ ድልድይ ታስቦ የነበረው ዝግጅት እንዳሰቡት እምብዛም ሳይደሰኩሩ መቋረጡ ታውቋል። ለአገዛዙ ሚዲያዎችም ይህንን ለመሸፋፈን በያዙት የቪዲዮ ማስረጃዎች አማካኝነት እንዲያጫጩሁት መታዘዙ ተሰምቷል።

ዝርዝሩ በአማራ ፋኖ በጎጃም ቃል አቀባይ ፋኖ ማርሸት ፀሀዩ በኩል ይገለፃል!


04/09/16 ዓ.ም

@NISIREamhra
9.4K viewsedited  12:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-12 10:53:53 #ሰበር_ዜና - ባህርዳር

በባህርዳር አዲሱ ድልድይ እና ሆምላድ ሆቴል አካባቢዎች የአሳማው መንጋ በተሰበሰበበት በድንች* እንዲሞቁ ተደርጓል። በተጨማሪም የ6ኛ ፖሊስ ጣቢያ የፖሊስ ፓትሮል መኪና ጋይቷል።

Bw
#ክብር_ለጀግኖቻችን
#ድል_ለአማራ_ፋኖ
#ድል_ለአማራ_ህዝብ

04/09/16 ዓ.ም

@NISIREamhra
10.3K views07:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-11 18:42:51
#ራምቦን_አወቃችሁት…

የሸዋው ተወላጅ። ከሸዋ ተነስቶ የሀይቅና የአምባሰል ዙሪያ ጀግኖችን በማሰባሰብ በጠላት ኃይል ላይ የቅጣት ዶፍ ሲያዘንብ የነበረው ኩሩ  ጀግና!

በመጨረሻም ከአምስት ወራት በፊት ስለ አማራ ህዝብ ነፃነት፡ ስለ አማራ ህዝብ ህልውና መረጋገጥ ሲል በክብር የተሰዋው የጦሩ ገበሬ!

በሱ ስም የተሰየመችው በወሎ ዕዝ ልጅ እያሱ ክ/ጦር አንደኛ ወይንም ራምቦ ሻለቃ እና ሁለተኛ ሻለቃ ዛሬ ግንቦት 03/2016 ዓ/ም ከንጋት ጀምሮ እስከ አመሻሹ በሀይቅ ከተማ ዙሪያ የጠላት አብይ አህመድን ወታደር ውሃ ውሃ ሲያስብሉት ውለዋል።

በዛሬው ውጊያ ማዕረጉ ያልታወቀ የአብይ አህመድ ምንጣፍ ጎታች የሆነ አንድ ከፍተኛ አዋጊን ጨምሮ በርካታ ወታደሮች የፋኖ አፈሙዝ ሲሳይ ሆነው ቀርተዋል።

@ የአማራ ድምፅ

#ክብር_ለጀግኖቻችን
#ክብር_ለሰማዕታቱ
#ድል_ለአማራ_ፋኖ
#ድል_ለአማራ_ህዝብ

03/09/16 ዓ.ም

@NISIREamhra
11.1K views15:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-11 15:44:33 #አንተ_ማን_ነህ

እኔ ወሎዬ ነኝ አልልም አንሼ
እኔ ጎጃሜ ነኝ አልልም አንሼ
እኔ ጎንደሬ ነኝ አልልም አንሼ
እኔ ሸዋዬ ነኝ አልልም አንሼ
#አማራ ነው ቤቴ ትልቁ አዳራሼ

#ወጥር_አማራ
#አንድነት_ሀይል_ነው
#ድል_ለአማራ_ፋኖ
#ድል_ለአማራ_ህዝብ

03/09/16 ዓ.ም

@NISIREamhra
10.8K views12:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ