#ንገሪኝ_ሀገሬ ንገሪኝ ሀገሬ እስኪ ምክንያትሽን ፣ አኩሪ ልጆችሽን ለምንድን ጠላሽን ፣ መጤውን አንግሰሽ ጣልሽው መሰረትሽን ፣ አማራ ነበረ አናፄ መቅደስሽ ጠባቂ ታሪክሽን ። እንደዛሬው ሳይሆን መጤ ሳይነግስብሽ ፣ አንቺ ስትወጃቸው እነሱም ሲወዱሽ ፣ ወድ ህይወታቸውን ከፍለው ሲያስከብሩሽ ፣ እንደዚህ ነበረ የኖርሽው ተከብረሽ ፣ እሽ አሁን የት ሄደ ያ ሁሉ መውደድሽ ። አረ ተይ ሀገሬ ይሄ በጣም ግፍ ነው ፣ አርበኛን አሳዶ ምን አይነት ክብር ነው ፣ ነው ወይስ ብልፅግና ማለት ታሪክን ማጥፋት ነው ። ቆይ ግን ለምንድን ነው ሞት የታወጀብን? ፣ ክብርሽን ጠብቀን እዚ ባደረስን ። እስኪ በአማራው ሞት ምን ትጠቀሚያለሽ ፣ ንገሪኝ ሀገሬ ለምን ትፈሪያለሽ ። እድል ከሰጠሽኝ ንገረኝ ካልሽ እማ ፣ ብዙ እነግርሽአለሁ ጆሮሽ ብቻ ይስማ ። ልንገርሽ ሀገሬ ግፍ እኮ ነው እሱ ፣ ወርቅ ላበደረሽ ጠጠር መመለሱ ። ኸረ ተይ ሀገሬ እንዲህ አትርሻቸው ፣ ለክብርሽ የሞቱ ትንሽ ሳይሰስቱ ስለህይወታቸው ፣ ባለ ታሪክ ጀግኖች አማራዎች ናቸው ፣ ይወቅስሽ አይደለ ደምና አጥንታቸው ። አሸባሪ የሚል አዲስ ስም ሲሰጠን ፣ እውነት ይህ ነው ለኛ ማግኘት የሚገባን ?፣ እውነት ነው ይህ ነገር አንቺም ወስነሻል ?፣ አሸባሪነቱ ለኛ ይመጥናል ? ። ስለሚፈሩን ነው አሸባሪ ሆነን? ይህን ስም የሰጡን፣ ንገሪኝ ሀገሬ ልወቀው እውነቱን ። ቆይ ግን ምን በደልንሽ ምንስ አደረግንሽ ? ፣ ሁሉም የሚጠላን ሆነናል ልጆችሽ ። ሁሉም ምኞቱ ነው እኛ እንድንጠፋ ፣ ንገሪኝ ሀገሬ ምን ስላጠፋ ነው አማራ እሚገፋ ። ንገሪኝ ሀገሬ በየትኛው ሀገር እንዲህ ይደረጋል ፣ እንዴት መጤ ነግሶ ባለ ሀገር ይሞታል ። ባለ ሀገር በመጤ ሆኖ ማላገጫ ፣ ምን አይነት ውድቀት ነው አዘቅዝቆ ሩጫ ፣ በሰራነው ሀገር አጣን መቀመጫ ። እስኪ በምን ቋንቋ ምን ብየ ላስረዳሽ ፣ ኢትዮጵያ የአማራ ውለታ እንዳለብሽ፣ በደም በአጥንቱ ነው የኖርሽው ተከብረሽ ። በዘረኛ መንጋ ቢፈርስም ቤታችን ፣ ከቤት አፈናቅለው ጎዳና ቢጥሉን ፣ እኛ ለክብራችን ፋኖ ነው ህልማችን ፣ ቤትም አንፈልግም ጫካ ነው ቤታችን ፣ ለማስመለስ ብለን ማንነት ክብራችን ፣ ትግል ጀምረናል አንስተን ነፍጣችን ፣ አራት ኪሎን አድርገን ለመዳረሻችን ። ንገሪኝ ኢትዮጵያ (ፀሀፊ የንስር አማራ ቤተሰብ የአዴቱ ) #ድል_ለአማራ_ፋኖ #ድል_ለአማራ_ህዝብ 04/09/16 ዓ.ም @NISIREamhra 8.4K views18:12