Get Mystery Box with random crypto!

✞ የማርያም ✞ ፳፩ እና ✞ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ልጆች ፲፫ ✞

የቴሌግራም ቻናል አርማ muzemur — ✞ የማርያም ✞ ፳፩ እና ✞ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ልጆች ፲፫ ✞
የቴሌግራም ቻናል አርማ muzemur — ✞ የማርያም ✞ ፳፩ እና ✞ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ልጆች ፲፫ ✞
የሰርጥ አድራሻ: @muzemur
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 270
የሰርጥ መግለጫ

 
✝💚💛❤️@muzemur💚💛❤️✝
✝💚💛❤️@muzemur💚💛❤️✝
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
“አንተ ግን አቤቱ፥ መጠጊያዬ ነህ፥ ክብሬንና ራሴንም ከፍ ከፍ የምታደርገው አንተ ነህ።” መዝ ፫፥፫
join join join
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
 ✝💚💛❤️@muzemur💚💛❤️✝
 ✝💚💛❤️@muzemur💚💛❤️✝

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-05-28 21:41:42 በዚህም ጊዜ ከቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ ሆና በግልጽ ለሁሉ ትታይ ነበር፡፡ ከፊቷ ብርሃን የተነሣ አምስት ቀን ሌሊቱና ቀኑ አይታወቅም ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ ልብሳቸውን ወደ ላይ ሲወረውሩላት የፈቀደችውን ተቀብላ ትልክላቸዋለች፤ ለበረከት ይካፈሉታል፡፡ ከተሰበሰቡትም የሞተ ዘመድ ያላቸው አስነሺልን ሲሏት አስነሥታ በሕይወተ ሥጋ ታሳያቸው ነበር፡፡ እንዲህ እየሆኑ በፍጹም ደስታ አምስቱን ቀን ሰንብተዋል፡፡ ወደ ቤታቸውም ለመኼድ ሲሹ በፊቷ ሰግደው ይሰናበቷታል እርሷም ትባርካቸዋለች፡፡ የበዓሉ መታሰቢያ ከግንቦት 21 እስከ 25 ቀን ነው፡፡ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በረከቷ ይደርብን አሜን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ምንጭ፦ መድበለ ታሪክ ፣ መዝገበ ታሪክ ፣ ስንክሳር ዘግንቦት 21
111 viewsTheotokos, 18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-28 21:41:17
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
#ተዝካረ_በዓላ_ለማርያም_በደብረ_ምጥማቅ (ግንቦት 21)

ከሠላሳ ሦስቱ የእመቤታችን በዓላት አንዱ ደብረ ምጥማቅ ነው፡፡ ደብረ ምጥማቅ ግብጽ ውስጥ በገምኑዲ አቅራቢ የምትገኝ ገዳም ናት፡፡ እመቤታችን ልጇን ይዛ በስደት ሳለች ጌታ ‹‹በዚህ ቦታ በስምሽ ታላቅ ቤተ ክርስቲያን ይታነጻል ስሙንም ደብረ ምጥማቅ ይሉታል›› ብሎ ትንቢት ነግሯት ነበር፡፡ ጊዜው ሲደርስም በዚሁ ቦታ በእመቤታችን ስም ቤተ ክርስቲያን ታንጾ ስሙ ደብረ ምጥማቅ ተብሏል፡፡
በዚህ ቦታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የክርስትናን ሃይማኖት ለመግለጽ ለ5 ቀናት ለክርስቲያኑም ለአረማዊውም በገሀድ ታይታለች፡፡ በዚህም ዕለት በልጇ የመለኮት ብርሃን ከፀሐይ ሰባት እጅ አሸብርቃ መላእክት፣ ሊቃነ መላእክት፣ ኪሩቤና ሱራፌል ከበዋት ነቢያት፣ ሐዋርያት፣ ሰማዕታት፣ ደናግልና መነኰሳት ሄሮድስ ያስፈጃቸው ሕፃናት ሁሉ ይመጣሉ፡፡ ሱራፌል ማዕጠንት ይዘው እያመሰገኑ ያጥኑ ነበር፡፡ ከሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ በነጭ ፈረስ ቅዱስ መርቆሬዎስ በጥቁር ፈረስ በየተራ እየመጡ ይሰግዱላታል፡፡
97 viewsTheotokos, 18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-28 20:20:11
92 views# unknown, 17:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-28 20:19:55
90 views# unknown, 17:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-25 08:52:29 የግንቦት ፲፮ ቀን ፳፻፲፬ ዓም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በተለያዩ ጉዳዮች ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።

በዛሬው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሎ ሰፋ ያሉ ውይይቶች የተደረጉ ሲሆን በወቅታዊ ጉዳይ በእስር ላይ ቆይተው የነበሩ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አገልጋዮች በሥራ ገበታችን ላይ ሰው ተመድቦብናል በሚል ያቀረቡትን አቤቱታ የቋሚ ሲኖዶስ ተመልክቶ ውሳኔ ያስተላለፈ ቢሆንም በአፈጻጸሙ ላይ በነበረ ጥያቄ ወደ ምልዓተ ጉባኤ ተመርቶ ውይይት ተደርጎበታል።
ምልዓተ ጉባኤውም በጉዳዩ ላይ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስና ዋና ሥራ አስኪያጅ እንዲሁም የአቤቱታ አቅራቢ አገልጋዮችን ሀሳብ ያዳመጠ ሲሆን ፣
ጉዳዩን በተገቢው ሁኔታ መርምሮ ለመወሰን እንዲቻል
1. ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ
2. ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ የሰሜን ካሊፎርኒያ ኔቫዳ አሪዞና አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
3. ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
4. ሊቀ ትጉኃን ሽመልስ ቸርነት በመንበረ ፓትርያክ የሕግ መምሪያ ዋና ኃላፊ በአስቸኳይ አጣርተው በአጭር ቀናት ውስጥ ለምልዓተ ጉባኤው እንዲያቀርቡ ሠይሟል።

1. የደቡብ ወሎና የከሚሴ አህጉረ ስብከት በብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ ብቻ እንዲመራ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ በዚያው የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲመሩ
2. ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ(ዶ/ር) አሁን ባሉበት በሰሜን አሜሪካ የሜኔሶታ ሀገረ ስብከት ያሉት ጉዳዮች ተጣርቶ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ የሜኔሶታ ሀገረ ስብከትን እንደያዙ የኢሊባቡር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲሠሩ፤
3. ብፁዕ አቡነ እንጦንስ በያዙት ሀገረ ስብከት ላይ የአፋር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲመሩ
4. በሰሜን አሜሪካ የኦሀዮ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ሰላማ የምዕራብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲመሩ
5. ብፁዕ አቡነ አብርሃም ዘካናዳ የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲመሩ ወስኗል።
በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሀሳብን በደብዳቤ አዘጋጅቶ ለማቅረብ ብፁዓን አባቶችን ሠይሞ የነበረው ምልዓተ ጉባኤው፤ በቀረበው ረቂቅ ደብዳቤ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ሰጥቶበታል።
ብፁዕነታቸው ከቅዱስ ሲኖዶስ ያልተሰጡና ትክክለተኛነታቸው ያልተረጋገጠ መረጃዎችን የሚያስተላልፉ አካላት አካሄድ መታረም እንዳለበት ጠቁመው ካህናትና ምዕመናን ከቅዱስ ሲኖዶስ የሚሰጠውን መግለጫና መመሪያ ብቻ እንዲጠብቁ አሳስበዋል።
117 viewsTheotokos, 05:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-16 07:02:41 የህይወት ምክር

ደካማነትህን አስታውስ ያን ጊዜ በጣም ጠንቃቃ ትሆናለህ ሊጎዱህ በሚችሉ በትምክህትና በውዳሴ ከንቱም አትሸነፍም።

የተሰጠህን በፍቅር የተሞላ የእግዚአብሔርን ቸርነት አስታውስ ይህም በምስጋና የተሞላ ሕይወት እንድትመራ ያደርግሃል። በእግዚአብሔር ፍቅርና ሥራ ላይ ስትታመን ፍጹም የሆነ በልብህ እያደገ ይመጣል። ከእግዚአብሔር ጋር ያሳለፍከው ጊዜ ደግሞ በእምነት እንድትኖር ያበረታታሃል።

የሰዎችን ፍቅርና ከአንተ ጋር ያሳለፉትን መልካም ጊዜ አስታውስ የሰዎችን ቀናነት ትጠራጠር ዘንድ ወይም ያደረጉብህን ክፉ ነገር ታስብ ዘንድ ይገባሃልን? የቀደመ ፍቅራቸው ስለ እነርሱ ይማልዳል የአንተንም ቁጣ ያበርዳል። ሞት እንዳለ ስታውስ ፣እንዲሁም በዓለም ያለ ፈተናም እንደሚያልፍ። "ሁሉ ከንቱ ነው፣ ነፋስንም እንደመከተል ነው" መክ 1፥14 ማለትን ትረዳለህ።

በእግዚአብሔር ፊት መቆምህንና እርሱም እንደሚመለከትህ አስታውስ ያኔ ኃጥአት አትሰራም እግዚአብሔርን ታየዋለህና።

የእግዚአብሔርን ቃልኪዳን አስታውስ ። በዚህ ከጭንቀቶችህ ሁሉ ትጽናናለህ። ከዘነጋሃቸው ግን ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት እንዲህ ያለውን አስታውስ "ለባሪያህ ተስፋ ያስደረግኸውን ቃልህን አስብ። ቃልህ ሕያው አድርጎኛልና ይህች በመከራዬ ደስ አሰኘችኝ።" መዝ 118፥49-50

ስለ አንተ የፈሰሰውን የክርስቶስን ክቡር ደም አስታውስ። በዚህ ሕይወትህ ያለውን ዋጋ በእርግጥ ታውቃለህ፤ በዓይኖችህ ፊት የከበረ ይሆናል፣ ስለዚህ በከንቱ በመኖር አታጠፋውም፣ " በዋጋ ተገዝግታችኋልና " 1ኛ ቆሮ 6፥20 እንዲል ቅዱስ ጳውሎስ።

በወላጆችህ እምነት በተጠመቅህባት ቦታ ለእግዚአብሔር የገባኸውን ቃል አስታውስ፤ድያብሎስን ፣ ስራዎቹን ሁሉ ፣ሐሳቦቹንና ጥበቡን፣ ኃይሉንም ትክድ ዘንድ።

በዚህ ዓለም እንግዳ መሆንህንና ወደ ሰማያዊው ቤትህ እንደምትመለስ ዘወትር አስታውስ። ያን ጊዜ በዚህ ዓለምና በደስታው ተስፋ ማድረግን ትተዋለህ።

በጠባቡ በር መጓዝ ወደ መንግስተ ሰማያት እንደሚያደርስህ አስታውስ። ሰፊው ደጅ ፊት ለፊትህ ተከፍቶ ብታየው አልፈኸው ሂድ ከእሱም እራቅ፣ በእርሱ የሄዱ እንዳሉ አልቀዋልና።

ዘላለማዊውን ሕይወትህን አስታውስ ፣ሁልጊዜም ስለዚህ ትጋ።

የእግዚአብሔር ልጅ መሆንህንና እርሱን መምሰል እንዳለብህ አስታውስ።

እውነተኞች ከሆኑት ከእግዚአብሔር ልጆች ጋር አካሄድህን አስተካክል ።

የመንፈስ ቤተ መቅደስ መሆንህን አስታውስ በውስጥህም ያለውን ቅዱሱን የእግዚአብሔር መንፈስ አታሳዝን ። ዘወትርም ቅዱስ የእግዚአብሔር ማደሪያ ሁን።

ለልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ይግባው አሜን።
(ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ)
@muzemur
@muzemur

“አንተ ግን አቤቱ፥ መጠጊያዬ ነህ፥ ክብሬንና ራሴንም ከፍ ከፍ የምታደርገው አንተ ነህ።” መዝ ፫፥፫
join join join

  @muzemur
  @muzemur
129 viewsTheotokos, 04:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-09 16:46:27 ግንቦት አንድ በዚህችም ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደች::

እርሷም ለሰው ሁሉ ወገን ድኅነት የሆነባት ናት::

ከወንዶች ወገን የከበረ አባቷም ስሙ ኢያቄም ከሴቶች ወገን የከበረች ሚስቱ ሐና ይባላሉ::

ሁለቱም ልጅ በማጣት ሲያዝኑ ኖሩ በዚያ ወራት የመካኖችን መባዓ ካህናቱ አይቀበሉም ነበር::

እነርሱም ከሰው የሚደርስባቸውን ሽሙጥና ኀዘናቸውን ያርቅላቸው ዘንድ በቀንና በሌሊት ወደ እግዚአብሔር ፈጽሞ ይማልዱ ነበር::

ሰውን የሚወድ እግዚአብሔር ከዘራቸው ለዓለሙ ሁሉ መድኃኒት ይሆን ዘንድ መልካም የሆነ ኀሳባቸውን ተመለከተ::

ክቡር ኢያቄምም አርባ ቀን እስኪፈጸም በተራራ ውስጥ ቁሞ ሲጸልይ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገለጸለትና ለዓለሙ ሁሉ ድኅነት የሚደረግባት ዘር እንደሚሰጠው አበሠረው::

በፍጹም ልብ አምኖ ከተራራው ወረደ ለተመሰገነች ሚስቱ ለሐናም ከእግዚአብሔር መልአክ የሰማውን ያንን ራእይ ነገራት:: ቃሉ እውነት እንደሆነ እርሷም አመነች ልዑል እግዚአብሔርንም አመሰገኑት::

የተመሰገነች ቅድስት ሐናም ከእርሷ የሚወለደውን በዘመኑ ሁሉ ለቤተ እግዚአብሔር አገልጋይ ታደርግ ዘንድ ለእግዚአብሔር ስለትን ተሳለች::

ከዚህም በኋላ ይቺን የከበረች ሕፃን ፀንሳ ወለደች ስሟንም ማርያም ብላ ሰየመቻት ትርጓሜውም እመቤት ማለት ነው::

ደግሞም ሀብትና ሥጦታ ማለት ነው:: በእውነት የዓለሙ ሁሉ እመቤት ናት:: ሁላችን በእርሷ ሰማያዊ ሀብት ልጅነት ያገኘንባት::

እንግዲህ እዚህ ጋር ልብ ይሏል::

በዚህ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም መወለድ የኛ ልጅነት የኛ የመዳንችንን መንገድ እግዚአብሔር እንዴት እንዳከናወነልን እንረዳለን::

እግዚአብሔር ሰውን ሲያድን ማዳኑን የፈጸመው እጅግ በጣም ልዩ በሆነ ሁኔታ ነው::

ይህም ገናናነቱን ከእኛ ታናሽነት ጋር አዋሕዶ፤ ከሃሊነቱን ከእኛ ነፃነት ጋር አስማምቶ በመሆኑ ነው::

ይህ ማለት ምን ማለት ነው?

ሊያድነን ሲነሣ እንዲሁ በማንኛውም መንገድ ቢያድነን ታላቅ ቸርነትና ደግነት ሆኖ ሳለ እርሱ ግን ከዚያም በላይ በሆነ መንገድ እኛን አሳትፎ ፈቃዳችንን ተቀበሎ አስፈቅዶ አስወድዶ ያዳነን::

እርሱ ሁሉን ማድረግ ስለሚችል ብቻ ያለ እኛ ፈቃድ ሱታፌ እንዲሁ አፍአዊ በሆነ ሁኔታ እና ያለ ፈቃዳቸው አላዳነንም::

ባሕርያችንን ሲዋሐድም ያለ እኛው ፈቃድና ሱታፌ አላደረገውም:: የሚጠቅመንን የመዳናችንን ነገር ሲፈጽም እኛን አስወድዶና አሳትፎ ነው::

አካላዊ የእግዚአብሔር ቃል እኛን ለማዳን ከሰማየ ሰማያት ሲወርድ መከራ ተቀብሎ እኛን የሚያድንበትን መሣሪያ የወሰደው ከእኛው መዳኑ ከሚያስፈልገንና ከሚደረግልን ከሰዎች ነበር::

ይህ እንዲሆን ደግሞ ሰዎችን የሚወክልና እኛን ሁሉ ወክሎ የሚሳተፍ አንድ ሰው ያስፈልግ ነበር::

በዚህም ያ የሚያስፈልግ አንድ ሰው በዛሬዋ ቀን የተወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት:: በእወነት ምስጋና ይድረሳትና።

ከዚህ በኋላ ነው እንግዲ የነቢያት ትንቢታቸው ከተፈጻሚነት የደረሰው:: ታዲያ የዛሬውን በዓል ስናከብርና ተድላ ደስታ ስናደርግ ከመንፈሳዊነት ሳንወጣ ልንጠነቀቅ ይገባል::

ይህን በዓል ስናከብርም ሌሊት በቤተ ክርስቲያን በማኅሌት÷ በዝማሬ÷ ጠዋት በኪዳንና በቅዳሴ÷ ታምሯን በመስማት÷ ወንግል በመማር ነው:: ክርስቲያኖች ከዚህ የወጣ ባዓል የላቸውም::

ብዙዎች የእኛን መንፈሳዊ በዓል ይዘው የራሳቸውንና የቤታቸውን ጣጣ ይዘውና አስታከው መንፈሳዊ በዓላ ላይ ለጥፈው ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንም ከመንፈሳዊነታችን ጋርም የሚፃረር ነገር ሲፈጽሙ ይታያል ይህ አግባብ አይደለም::

የበግና የፍየል ከለር እየመረጡ÷ ቄጣና ፈንዲሻ እየረጩ÷ የቡና አተላ እየገለበጡ የሚከበር መንፈሳዊ በዓል የለም:: አስፀያፊም የተወገዘም ግብር ነው።

እስኪ አንድ በዓለም ያለ ሰው ልደቱን ሲያከብር ወይ ሲደግስ የበግ ከለር መርጦ የሚያርድ ማን አለ? ወይ ቡና እያንቃረረ ቂጣና ፈንዲሻ በየጥጋ ጥጉ የሚጥል ማን አለ? ታዲያ እንደዚህ ያለን ኮተታ ኮተት ከየት የመጣ ነው::

የኛ አይደለም እንዲህ ያለ ነገር እንዲህ የሚያደርጉ ካሉ ፈጥነው ንሰሐ ሊገቡና ከክርስቲያኖች ማኅበር ሊገቡ ይገባል::

የእመቤታችንን የልደቷን በዓል ግን የምናከብረው በዝማሬ÷ በማኅሌት÷ በኪዳን÷ በቅዳሴ ጊዜ ሥጋወ ደሙ እየተቀበልን÷ ወንጌልን እየተማርን÷ የተራበ እያበላንና የታረዘ እያለበስን እየዘመርን ነው::

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን የሥጋና የነፍስ መድኃኒት የሆነች እርሷን እናቱን ለሰጠን በረከቷም ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋር ለዘላለሙ ይኑር አሜን። 
@muzemur
@muzemur

“አንተ ግን አቤቱ፥ መጠጊያዬ ነህ፥ ክብሬንና ራሴንም ከፍ ከፍ የምታደርገው አንተ ነህ።” መዝ ፫፥፫
join join join

  @muzemur
  @muzemur
127 views# unknown, 13:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ