Get Mystery Box with random crypto!

የግንቦት ፲፮ ቀን ፳፻፲፬ ዓም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በተለያዩ ጉዳዮች ተወያይቶ ውሳኔ አ | ✞ የማርያም ✞ ፳፩ እና ✞ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ልጆች ፲፫ ✞

የግንቦት ፲፮ ቀን ፳፻፲፬ ዓም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በተለያዩ ጉዳዮች ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።

በዛሬው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሎ ሰፋ ያሉ ውይይቶች የተደረጉ ሲሆን በወቅታዊ ጉዳይ በእስር ላይ ቆይተው የነበሩ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አገልጋዮች በሥራ ገበታችን ላይ ሰው ተመድቦብናል በሚል ያቀረቡትን አቤቱታ የቋሚ ሲኖዶስ ተመልክቶ ውሳኔ ያስተላለፈ ቢሆንም በአፈጻጸሙ ላይ በነበረ ጥያቄ ወደ ምልዓተ ጉባኤ ተመርቶ ውይይት ተደርጎበታል።
ምልዓተ ጉባኤውም በጉዳዩ ላይ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስና ዋና ሥራ አስኪያጅ እንዲሁም የአቤቱታ አቅራቢ አገልጋዮችን ሀሳብ ያዳመጠ ሲሆን ፣
ጉዳዩን በተገቢው ሁኔታ መርምሮ ለመወሰን እንዲቻል
1. ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ
2. ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ የሰሜን ካሊፎርኒያ ኔቫዳ አሪዞና አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
3. ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
4. ሊቀ ትጉኃን ሽመልስ ቸርነት በመንበረ ፓትርያክ የሕግ መምሪያ ዋና ኃላፊ በአስቸኳይ አጣርተው በአጭር ቀናት ውስጥ ለምልዓተ ጉባኤው እንዲያቀርቡ ሠይሟል።

1. የደቡብ ወሎና የከሚሴ አህጉረ ስብከት በብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ ብቻ እንዲመራ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ በዚያው የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲመሩ
2. ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ(ዶ/ር) አሁን ባሉበት በሰሜን አሜሪካ የሜኔሶታ ሀገረ ስብከት ያሉት ጉዳዮች ተጣርቶ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ የሜኔሶታ ሀገረ ስብከትን እንደያዙ የኢሊባቡር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲሠሩ፤
3. ብፁዕ አቡነ እንጦንስ በያዙት ሀገረ ስብከት ላይ የአፋር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲመሩ
4. በሰሜን አሜሪካ የኦሀዮ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ሰላማ የምዕራብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲመሩ
5. ብፁዕ አቡነ አብርሃም ዘካናዳ የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲመሩ ወስኗል።
በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሀሳብን በደብዳቤ አዘጋጅቶ ለማቅረብ ብፁዓን አባቶችን ሠይሞ የነበረው ምልዓተ ጉባኤው፤ በቀረበው ረቂቅ ደብዳቤ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ሰጥቶበታል።
ብፁዕነታቸው ከቅዱስ ሲኖዶስ ያልተሰጡና ትክክለተኛነታቸው ያልተረጋገጠ መረጃዎችን የሚያስተላልፉ አካላት አካሄድ መታረም እንዳለበት ጠቁመው ካህናትና ምዕመናን ከቅዱስ ሲኖዶስ የሚሰጠውን መግለጫና መመሪያ ብቻ እንዲጠብቁ አሳስበዋል።