Get Mystery Box with random crypto!

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! #ተዝካረ_በዓላ_ለማርያም_በደብረ_ም | ✞ የማርያም ✞ ፳፩ እና ✞ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ልጆች ፲፫ ✞

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
#ተዝካረ_በዓላ_ለማርያም_በደብረ_ምጥማቅ (ግንቦት 21)

ከሠላሳ ሦስቱ የእመቤታችን በዓላት አንዱ ደብረ ምጥማቅ ነው፡፡ ደብረ ምጥማቅ ግብጽ ውስጥ በገምኑዲ አቅራቢ የምትገኝ ገዳም ናት፡፡ እመቤታችን ልጇን ይዛ በስደት ሳለች ጌታ ‹‹በዚህ ቦታ በስምሽ ታላቅ ቤተ ክርስቲያን ይታነጻል ስሙንም ደብረ ምጥማቅ ይሉታል›› ብሎ ትንቢት ነግሯት ነበር፡፡ ጊዜው ሲደርስም በዚሁ ቦታ በእመቤታችን ስም ቤተ ክርስቲያን ታንጾ ስሙ ደብረ ምጥማቅ ተብሏል፡፡
በዚህ ቦታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የክርስትናን ሃይማኖት ለመግለጽ ለ5 ቀናት ለክርስቲያኑም ለአረማዊውም በገሀድ ታይታለች፡፡ በዚህም ዕለት በልጇ የመለኮት ብርሃን ከፀሐይ ሰባት እጅ አሸብርቃ መላእክት፣ ሊቃነ መላእክት፣ ኪሩቤና ሱራፌል ከበዋት ነቢያት፣ ሐዋርያት፣ ሰማዕታት፣ ደናግልና መነኰሳት ሄሮድስ ያስፈጃቸው ሕፃናት ሁሉ ይመጣሉ፡፡ ሱራፌል ማዕጠንት ይዘው እያመሰገኑ ያጥኑ ነበር፡፡ ከሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ በነጭ ፈረስ ቅዱስ መርቆሬዎስ በጥቁር ፈረስ በየተራ እየመጡ ይሰግዱላታል፡፡