Get Mystery Box with random crypto!

School information

የቴሌግራም ቻናል አርማ minesterofeducation — School information S
የቴሌግራም ቻናል አርማ minesterofeducation — School information
የሰርጥ አድራሻ: @minesterofeducation
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.96K
የሰርጥ መግለጫ

ANY COMMENTS
@marcilas3bot

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-05-04 17:50:06 #JimmaUniversity

በ2014 ዓ.ም የዩንቨርሲቲ መግቢያ ውጤት አስመዝግባቹህ በትምህርት ሚኒስቴር ወደ ጅማ ዩኒቨርስቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ ግንቦት 04 እና 05/2014 ዓ.ም መሆኑን የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት አሳውቋል።

፨ @minesterofeducation
5.6K viewsedited  14:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 11:06:27 #መግቢያ_ቀናት

እስካሁን ባለው የመግቢያ እና ሪፖርት ማድረጊያ ቀን ያሳወቁ ተቋማት እና የአዲስ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መግቢያ/ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ፦

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሪፖርት ማድረጊያ ሚያዚያ 24 እና 25/2014 ዓ/ም ፤ በረመዷን በዓል ምክንያት መድረስ ለማይችሉ እስከ አርብ ሚያዚያ 28 /2014 ዓ/ም ድረስ

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የኦንላይን ምዝገባ ግንቦት 01 እስከ 05/2014 ዓ/ም ፤ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ እና ሪፖርት ማድረጊያ ግንቦት 8 እና 9/2014 ዓ/ም

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 08 እና 09/2014 ዓ.ም

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 27 እና 28/2014 ዓ/ም

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 1 እና 2 /2014 ዓ/ም

መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 01 እና 02/2014 ዓ/ም

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 29 እና 30 /2014 ዓ/ም

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 28 እስከ 30 /2014 ዓ/ም

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 28 እና 29/2014 ዓ/ም

ASTU / AASTU ሚያዚያ 28 እና 29 /2014 ዓ/ም በቅጣት ግንቦት 1 /2014 ዓ/ም

ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ቀን ግንቦት 8 እና 9 ፤ ምዝገባ ግንቦት 10 እና 11

መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ቀን ግንቦት 01 እና 02 /2014 ዓ/ም

ሐረማያ ዩኒቨርስቲ ግንቦት 12፣ 13 እና 14

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 1 እና 2/2014 ዓ/ም

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 1 እና 2/2014 ዓ/ም

@minesterofeducation
5.3K views08:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-30 07:29:40 የትኛውም የግል ሆነ የመንግስት ት/ት ቤቶች ግንቦት 1 ት/ት እንዲጀምሩ ይደረጋል


-ለብዙ ጊዜ ስትጠባበቁ የነበራችሁ ውድ የ12ተኛ ክፍል ተማሪዎች ትምህርታችሁን ልትጀምሩ በጣት ሚቆጠር ጊዜ ቀርቷችኋል።

-ተማሪዎች አስፈላጊውን ዝግጅት ምታደርጉበት ጊዜ አሁን ነው።ስለዚህ ይህን በመገንዘብ እራሳችሁን ከወዲሁ እንድታዘጋጁ ስንል እናሳስባለን ።

@minesterofeducation
5.3K views04:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-29 18:26:31 የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ጥሪ ፦

በ2014 ዓ/ም የመጀመሪያ ዓመት አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ሚያዚያ 29 እና 30 / 2014 ዓ/ም ሲሆን ተማሪዎች በአካል ተገኝታችሁ ምዝገባ እንድታከናውኑ ጥሪ ቀርቧል።

#ደብረብርሃን_ዩኒቨርሲቲ #Tewabe

@minesterofeducation
4.8K views15:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-29 10:09:12 #MoH

የጤና ሚኒስቴር ከተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ ለተመረቁ የጤና ባለሙያዎች ከግንቦት 01 እስከ 04/2014 ዓ.ም የብቃት ምዘና ፈተና እንደሚሰጥ አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ ፈተናውን ለመስጠት ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የገለጸ ሲሆን የተፈታኝ ባለሙያዎች የጊዜ ሰሌዳን ይፋ አድርጓል።

ፋርማሲ፣ አንስቴዥያ እና ሜዲካል ራዲዮሎጂ
ባለሙያዎች ~ ግንቦት 01/2014 ዓ.ም

ነርሲንግ ~ ግንቦት 02/2014 ዓ.ም

ሕክምና፣ ጤና መኮንን እና ዴንታል ሜድስን
ባለሙያዎች ~ ግንቦት 03/2014 ዓ.ም

ሚድዋይፍሪ እና ሜዲካል ላቦራቶሪ
ባለሙያዎች ~ ግንቦት 04/2014 ዓ.ም

@minesterofeducation
4.7K views07:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-27 16:28:57 #AAU

የአዲስ ተማሪዎች ጥሪ ፦

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2014  የትምህርት ዘመን በመደበኛ የዲግሪ ትምህርት መርሃ-ግብር በትምህርት ሚ/ር መስፈርት መሠረት አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ ሚያዚያ 24 ቀን እና ሚያዚያ 25 ቀን 2014 ዓ.ም በተመደባችሁበት የዩኒቨርስቲው ካምፓስ ሪፖርት እንድታደርጉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥሪ አቅርቧል።

ተማሪዎችም ለምዝገባ ስትመጡ የሚያስፈልጋችሁ ነገሮች ከላይ ተዘርዝረዋል አንብቧቸው።

ነዋሪነታችሁ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሆኖ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት የምታደርጉትና ስለ ዩኒቨርስቲው ገለጻ የምታገኙት ሚያዚያ 26 ቀን 2014 ዓ.ም መሆኑን ተገልጿል።

ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትመጡ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲው ውስጥ የመኝታ አገልግሎት ለማግኘት የተመደበላችሁን የመኝታ ክፍል 12ኛ ክፍል በተፈተናችሁበት ቁጥር በመጠቀም ከ https://portal.aau.edu.et ማግኘት ትችላላችሁ።

በሌሌላ በኩንል ፤ ተለያየ ምክንያት ትምህርት አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ ውጤታችሁ የሚያበቃችሁ ተማሪዎች አዲስ ከተመደቡ 1ኛ ዓመት ተማሪዎች ጋር በመቅረብ በ2014 ዓ.ም. የመጀመሪያ ሴሚስተር ለመልሶ ቅበላ ከሚያዚያ 27 እና 28 2014 ዓ.ም እንዲያመለክቱ ዩኒቨርሲቲው ጥሪ አቅርቧል።

መረጃው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ነው የደረሰን።

@minesterofeducation
4.6K views13:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-25 08:00:32 @moestudentbot
ምድባችሁን ለማየት
4.9K views05:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-25 07:50:50 የዩኒቨርስቲ ምድብ ከሰአታት በፊት ተለቋል

-ምድባችሁን ለማየት @marcilas3bot ላይ አድሚሽን ቁጥራችሁን ላኩ
@minesterofeducation
4.6K views04:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 12:31:50
ዘነቡ ገሰሰ ከዚህ አለም ከሞት ተለየች

@minesterofeducation
4.9K views09:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 08:17:51
ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በአል በሰላም አደረሳችሁ በቻናላችን ስም በአሉ የደስታ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን


@minesterofeducation
4.9K views05:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ