Get Mystery Box with random crypto!

#AAU የአዲስ ተማሪዎች ጥሪ ፦ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2014  የትምህርት ዘመን በመደበኛ | School information

#AAU

የአዲስ ተማሪዎች ጥሪ ፦

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2014  የትምህርት ዘመን በመደበኛ የዲግሪ ትምህርት መርሃ-ግብር በትምህርት ሚ/ር መስፈርት መሠረት አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ ሚያዚያ 24 ቀን እና ሚያዚያ 25 ቀን 2014 ዓ.ም በተመደባችሁበት የዩኒቨርስቲው ካምፓስ ሪፖርት እንድታደርጉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥሪ አቅርቧል።

ተማሪዎችም ለምዝገባ ስትመጡ የሚያስፈልጋችሁ ነገሮች ከላይ ተዘርዝረዋል አንብቧቸው።

ነዋሪነታችሁ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሆኖ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት የምታደርጉትና ስለ ዩኒቨርስቲው ገለጻ የምታገኙት ሚያዚያ 26 ቀን 2014 ዓ.ም መሆኑን ተገልጿል።

ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትመጡ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲው ውስጥ የመኝታ አገልግሎት ለማግኘት የተመደበላችሁን የመኝታ ክፍል 12ኛ ክፍል በተፈተናችሁበት ቁጥር በመጠቀም ከ https://portal.aau.edu.et ማግኘት ትችላላችሁ።

በሌሌላ በኩንል ፤ ተለያየ ምክንያት ትምህርት አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ ውጤታችሁ የሚያበቃችሁ ተማሪዎች አዲስ ከተመደቡ 1ኛ ዓመት ተማሪዎች ጋር በመቅረብ በ2014 ዓ.ም. የመጀመሪያ ሴሚስተር ለመልሶ ቅበላ ከሚያዚያ 27 እና 28 2014 ዓ.ም እንዲያመለክቱ ዩኒቨርሲቲው ጥሪ አቅርቧል።

መረጃው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ነው የደረሰን።

@minesterofeducation