Get Mystery Box with random crypto!

Michael Z Ethiop

የቴሌግራም ቻናል አርማ mikaelzethiop — Michael Z Ethiop M
የቴሌግራም ቻናል አርማ mikaelzethiop — Michael Z Ethiop
የሰርጥ አድራሻ: @mikaelzethiop
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.88K
የሰርጥ መግለጫ

ሃይማኖታዊ፣ አገራዊ፣ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ጉዳዮቻችን ይቀርቡበታል!

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-27 19:37:45 #Jesus Christ, the Son of the Virgin Mary, was crucified on the cross , He died and rose on the third day to conquer death, He ascended to the Heavenly Throne, and He made you live the previous life that Adam had in the Garden of Eden. It is the work of the Cross of Christ that has made you good, brought you back to your former glory, opened the door of heaven for you, destroyed hell and returned you to your former glory. Goodness is not what you get from a person or what you get through a person, it is your reward on the cross that God Jesus Christ gave you.
#Virgin Mary's Son Jesus gave us at the foot of the Cross mainly His Mother. Even a false group that organized in the name of Jesus to preach "another Jesus" and that who does not give you the Virgin Mary, the Mother of Jesus, is self-destructive.
#Don't believe if this self-destructive and false person order you not to break your baptismal seal of thread . Please, notice that your seal bears witness to the belief within you that Jesus Christ is God and that the Virgin Mary is the mother of God, the intercession of the saints. It is according to this teaching that the Orthodox church has sealed you with "the seal of thread. As long as you bear the seal of thread around your neck, it is your duty to witness this Orthodox teaching as a proclamation. But if your heart does not believe and your mouth does not proclame to this, your " Seal of thread" has no different use than the thread of hanging a tray. If what you believe in your heart and what you testify with your mouth is not connected to your seal of thread , Satan will hang you, and your destination will be hell. In such a way , the thread you made not only reminds you of Christ who saved the world, but also reminds you of the bandits' cross where the bandits were crucified .
#Now a day, the adulterous generation who hung the cross of Dakris (a thife , who was crucified with Jesus on the left side ) )around their necks is rising up against us by saying "we were orthodox; But now we have been converted . We were raped but we have now been restored".
#Today "in the name of 'another Jesus" we Orthodox are fed up with the insults against the orthodox believers, the "soldiers of 'another Jesus' who criticize the saints whom we plead as intercessors are lined up for us.
Beyond us, in the name of "another Jesus" the Virgin Mary is insulted by such adulterous generation by claiming her as the "use and throw material" that Jesus used to serve Him for nine months. Those of such "Christians" ridiculed the Virgin Mary in the name of "another Jesus".
#I believe that Jesus Christ, God of the saints, the Son of the Virgin Mary, judges those who insult the saints and persecute the saints even from the content of their teachings. Yes, of course !! This is the fact that we know from the Holy Scripture. Jesus claimes the persecution of the saints, His own persecution, and claimes the encroachment of the saints His own; That is whay He said from Hevean to Saul, While Saul was persecuting the saints, "Saul!! Saul!! Why are you persecuting me??". We believe that God of saints, our God Jesus Christ is still in the Judgment Throne in Heaven and He judges. (Acts 9:4)
#The Brave !!!
You have to wake up from a spell casting over you in " the name of another Jesus"!!! Protect yourself from the different gospel and different spirit that comes to you in the name of "another Jesus". When we Orthodox believers worship Jesus, not by leaving the intercession of the Virgin Mary, who was given the authority to call His name Jesus. It is Not by denying the heraldship of Saint Gabriel who came from Heaven bearing His name. It is Not by forgetting the apostles who preached His name around the world; It is Not by persecuting all the saints who will be given the seat of judgment at His second coming. (Matthew 19:28; Matthew 25:31)
241 views/\/\!|<@e|, 16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 19:37:45 #ጎበዝ !!!
በ"ሌላ ኢየሱስ ስም" ከሚረጭብህ አዚም መንቃት አለብህ !!! በ"ሌላ ኢየሱስ" ስም ከመጣብህ ልዩ ወንጌልና ልዩ መንፈስ እራስህን ጠብቅ ። እኛ ኦርቶዶክሳውያን አማኞች ኢየሱስን ስናመልክ ስሙን ኢየሱስ ብላ ለመጥራት ሥልጣን የተሰጣት የድንግል ማርያምን አማላጅነት በመተው አይደለም ። ስሙን ይዞ ከሰማይ የመጣውን የቅዱስ ገብርኤልን አብሣሪነት በመካድ አይደለም ። ስሙን በዓለም ዞረው የሰበኩትን ሐዋርያትን በመዘንጋት አይደለም ፤ በዳግም ምጽአት የመፈራረጃ ዙፋን የሚሰጣቸውን ቅዱሳንን ሁሉ በማሳደድ አይደለም ። (ማቴ.19:28፤ ማቴ.25:31)
አሁን ከኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን ከወጣቱም ከአረጋውያንም የሚጠበቀው "መልካም መሆን" ሳይሆን "መልካም ማድረግ" ነው ። ይኸውም የሚያጸድቅህ በቅዱሳን ስም በአማላጅነታቸው በመታመን የሚደረግ የትሩፋት ሥራ ነው ። (ማቴ.25:34-40)
#መልካምነት ስሙ ሳይሆን የመልካምነት ሥራው ያለውና የምንጸድቅበትም አስተምህሮ ያለው እኛ ኦርቶዶክሶች ጋር ነው ።
#ሻሎም !!!
ዘሪሁን ሙ. ግዛው
*+++++++++++*
"#Another_Jesus!!!" (2 Corinthians 11:4)
#The Holy Bible tells us that during the time of the apostles, Heterodox groups arose who called themselves chief "apostles" and "prophets" who preached "another Jesus" and not exact Jesus, the Son of the Virgin Mary.
The Apostle St. Paul informed the believers of Corinth, about the identification of "another Jesus" with warnning ; "If someone comes to you and calls you to 'another Jesus' whom we have not taught you...you should wait for us." And we will answer it .
St. Paul answered each of them. He taught Orthodox Doctrine that Jesus, the son of Virgin Mary, is Savior and Judge. He reprimanded and shamed the Heterodox groups who preached about the "other" Jesus. As the apostle St. Paul taught, he exposed the identity of "other Jesus" of the the false prophets. "#Another Jesus" means "Jesus" that the apostles did not preach. "Another Jesus" means Jesus who was not crucified to save mankind; (1. Cor. 1:18) "Another Jesus" means a godless, undead and unresurrected, "semi-Islamic Jesus". (1. Cor. 15:12) "Another Jesus" does not mean that he is said to have saved the World with His blood, but that he is only considered a moral teacher who teaches only goodness. (Mark 10:18) It is known that these teachings as "another Jesus" genre are recognized by Western theology doctrine .
#In the Western doctrine of Salvation , Such reflections of another Jesus' identification are the concepts that are given as the doctrine of Salvation and they are also a big tool for the transmission of heresies.
#In the name of "another Jesus" since the time of the apostles, sorcerers have been organizing in the name of Jesus. And they have been confusing the believers when their business is cold. As it is written in the Bible, in the Acts of the Apostles, there was a famous sorcerer called "Elymas", but later he saw the apostles baptizing and performing miracles in the name of Jesus, and he planned to be " a prophet" by saying, "Why don't I do such miracles and collect money?" . Then he has planted a kind of the Charity organization and he named it Bar-Jesus. Bar-Jesus means "Son of Jesus" . He came up with such name as a false prophet. Then he was distorting the teaching of the apostles that the governor Sergius Paulus is not to believe in Divinity of Jesus Christ, the Son of the Virgin Mary. Even today, what is happening in our country is the madeness and interference of such false prophets even in the functioning of the government. Then saying : "I am a child of Jesus!" You are a child of Jesus!" seems to be a modern but as a result, we have seen that anti-orthodox fake generation has arisen today. We are being invaded by the Western Salvation teaching genre by "being good!", and we are realizing that the destination means accepting "another Jesus".
Of course, "being good" sounds good, but what makes you rightious is not "being good" but "doing good".
Once you have been restored to your former glory and goodness through the work of Christ on the cross. When God created you, He created you good. What is now expected of you is to do good. (2 Cor. 5:17)
202 views/\/\!|<@e|, 16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 19:37:45 "#ሌላ_ኢየሱስ !!!" (2.ቆሮንቶስ.11:4)
#በሐዋርያት ዘመንም የድንግል ማርያም ልጅ ኢየሱስን ሳይሆን "ሌላ ኢየሱስን" የሚሰብኩ እራሳቸውን ዋና "ሐዋርያት"ና "ነቢያት" ያሉ ጸረ ኦርቶዶክስ ቡድኖች ተነሥተው እንደነበር ቅዱስ መጽሐፍ ይነግረናል ።
#ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ "#ወደ እናንተ የመጣና እኛ ወደ አላስተማርናችሁ ወደ "ሌላ ኢየሱስ' የጠራችሁ ቢኖር ...ልትጠብቁን ይገባል ።" መልስም እንሰጥበታለን ሲል ለቆሮንቶስ ምእመናን ስለ "ሌላኛው ኢየሱስ" መለያ ከማስጥንቀቅያ ጋር አስቀድሞ አሳውቋቸዋል ። (2.ቆሮንቶስ.11:4)
#ቅዱስ ጳውሎስ ለእያንዳንዳቸውም መልስ ሰጥቷቸዋል ። የድንግል ማርያም ልጅ ኢየሱስ "አዳኝ"ና "ፈራጅ" መሆኑን እየገለጸ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት አስተምሯል ። ስለ"ሌላ" "ኢየሱስ" የሚሰብኩትን ጸረ ኦርቶዶክስ ቡድኖችን በትምህርቱ ገስጿቸዋል፣ አሳፍሯቸዋልም ። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳስተማረው ፣ የሐሳውያኑን "ሌላ ኢየሱስን" ማንነት አጋልጧል። "ሌላ ኢየሱስ" ማለት ሐዋርያት ያልሰበኩት "ኢየሱስ" ማለት ነው ። "ሌላ ኢየሱስ" ማለት የሰው ልጆችን ለማዳን ያልተሰቀለ ኢየሱስ ማለት ነው ፤(1.ቆሮ .1:18) "ሌላ ኢየሱስ" ማለት አምላክነት የሌለው፣ ያልሞተ ከሙታንም ያልተነሳ ፣ "ከፊል-ኢስላማዊ ኢየሱስ" ማለት ነው ። (1.ቆሮ.15:12) "ሌላ ኢየሱስ" ማለት በደሙ ፈሳሽነት ዓለምን ማዳኑ የሚነገርለት ሳይሆን መልካምነትን ብቻ የሚያስተምር የሥነ ምግባር መምህር ተደርጎ የሚቆጠር ብቻ ማለት ነው ። (ማር.10:18) እነዚህ የ"ሌላ ኢየሱስ" ዘውግ አስተምህሮዎች በምዕራቡ ቲዎሎጅ አስተምህሮዎች ይታወቃሉ ። በምዕራባውያን የነገረ ድህነት አስተምህሮ ውስጥ የነገረ ድኅነት አስተምህሮ እየተባሉ የሚሰጡት እንደዚህ ዓይነት የ"ሌላ ኢየሱስ" ማንነት የሚንጸባረቅባቸው ጽንሰ ሐሳቦች ሲሆኑ ትልቅ የክህደት ማስተላለፊያዎችም ናቸው ።
#በዚህ "ሌላ ኢየሱስ" ስም ከጥንት ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ ጠንቋዮች ንግዳቸው ሲቀዘቅዝ በኢየሱስ ስም እየተደራጁ ምዕመናንን ሲያምታቱበት ኖረዋል ። በመጽሐፍ ቅዱስ በሐዋርያት ሥራ እንደተጻፈው "ኤልማስ" የሚባል ታዋቂ ጠንቋይ ነበር ፣ በኋላ ግን ሐዋርያት በኢየሱስ ስም ሲያጠምቁና ተአምር ሲያደርጉ አይቶ እርሱም ነቢይ መሆን አማረው ፤ ለምን እኔም እንዲህ ዓይነት ተአምር እያደረኩ ገንዘብ አልሰበስብም በማለት የግብረ ገብ ተቋም ዓይነት መሠረተ ፣ የተቋሙንም ስም " በር-ያሱስ አለው ። (ሐዋ.13:8)
"በር-ያሱስ" ማለትም "የኢየሱስ ልጅ" ማለት ነው ። በዚህም ስም ራሱን ነቢይ አደረገ ። ይህ ሐሰተኛ ነቢይም አንድ ሰርግዮስ ጳውሎስ የሚባል የሀገር መሪ በድንግል ማርያም ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነት እንዳያምን የሐዋርያትን ትምህርት እያጣመመበት ነበር ። ዛሬም በሀገራችን እየተከሰተ ያለው እንዲህ ዓይነት የሐሳውያን ነቢያት ውንብድና እና በመንግሥታዊ አሠራር ውስጥ የሚያደርጉት ጣልቃ ገብነት ነው ። "የኢየሱስ ልጅ ነኝ!" የኢየሱስ ልጅ ነህ!" እያለ የሚያምታታህ ዘመናዊ የመሰለ ነገር ግን ጸረ ኦርቶዶክስ የሆነ ሐሳዊ ትውልድ ዛሬም ተነስቶብናል ። "መጽደቅያው መልካምንት!" የሚል የምዕራባውያን የነገረ ድኅነት ትምህርት ዘውግ እየወረረን ነው ፣ መዳረሻውም "ሌላ ኢየሱስን" ተቀበሉ ማለት መሆኑን እያስተዋልን ነው ።
#በርግጥ "መልካምነት" ጥሩ ቢመስልም የሚያጸድቀው ግን "መልካምነት" ሳይሆን "መልካም ማድረግ" ነው ።
አንድ ጊዜ በክርስቶስ የመስቀል ሥራ ወደ ቀደመ ክብርህና መልካምነትህ ተመልሰሃል ። እግዚአብሔር ሲፈጥርህ መልካም አድርጎ ፈጥሮሃል ። አሁን ከአንተ የሚጠበቀው መልካም ማድረግ ነው ። (2.ቆሮ. 5:17)
#የድንግል ማርያም ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ፣ ሞቶ በሦስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ ተነሥቷል፣ ወደ ሰማያዊ ዙፋኑም ዐርጓል ፣ አንተንም አዳም በኤደን ገነት ያለውን የቀደመውን ኑሮ እንድትኖር አድርጎሃል ። መልካም ያደረገህ ፣ ወደ ቀደመ መልካምነት ክብርህን ያጎናጸፈህ ፣ የገነትን በር የከፈተልህ ፣ ሲዖልን መዝብሮ ወደ ቀደመ ክብርህ የመለሰህ ፣ የክርስቶስ የመስቀል ሥራ ነው ። መልካምነትን ከሰው ያገኘኸው ወይም በሰው የምታገኘው ሳይሆን እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠህ የመስቀል ሽልማትህ ነው ።
#የድንግል ማርያም ልጅ ኢየሱስ በመስቀሉ ስር የሰጠን በዋናነት እናቱን ነው ። የኢየሱስን እናት ድንግል ማርያምን የማይሰጥህ፣ በአንጻሩ "ሌላ ኢየሱስን" ለመስበክ "በኢየሱስ ስም" የተደራጀ ሐሳዊ ቡድን እንኳን መልካም ሊሆን እርሱ ራሱን አጥፍቶ ጠፊ ነው ።
#ይህ አጥፍቶ ጠፊና ሐሳዊ ሰው "ማኅተብህን እንዳትበጥስ !!' ቢልህ እንዳታምነው ፤ እባክህ አስተውል!!! ማኅተብህ የሚመሰክረው በውስጥህ ያለውን እምነትህን ሲሆን እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ መሆኑንና ድንግል ማርያም የአምላክ እናት መሆኗን፣ የቅዱሳንን አማላጅነትን ነው፤ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ማኅተብ ያሰረችልህ በዚህ አስተምሮዋ መሠረት ነው ፣ ማኅተብ እስካሰርክ ድረስ ይህንን የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ እንደ አዋጅ በዐደባባይ መመስከር ግዴታ አለብህ ። ነገር ግን ይህንን ልብህም የማያምን አፍህም የማይመሰክር ከሆን የአንተ "የአንገት ክር" "ከትሪ ማንጠልጠያ ክር" የተለየ አገልግሎት የለውም ። በልብህ የምታምነውና በእፍህ የምትመሰክረው ከአንገትህ ክርህ ጋር እንደ ማኅተምነቱ ካልተገናኘ ሰይጣን ያንጠለጥልሃል ፣ መዳረሻህም ሲዖል ይሆናል ። ያሰርከው ክርም ዓለምን ያዳነውን ክርስቶስን ማስታወሱ ቀርቶ ሽፍቶቹ የተሰቀሉበትን የሽፍታ መስቀልን ወደ ማስታወስ ይወስድሃል ።
#ለዚህም ነው ዛሬ ላይ ዳክርስ (ከኢየሱስ ጋር በግራ በኩል የተሰቀለው ) የተባለው ሌባ የተሰቀለበትን መስቀል በአንገታቸው አገልድመው ኦርቶዶክስ ነበርን፤ አሁን ግን ተለወጥን ። ተደፍረን ነበር፤ አሁን ግን ተከበርን የሚል አመንዝራ ትውልድ እያየን ነው ።
#ዛሬ "በሌላ ኢየሱስ ስም" ኦርቶዶክሳውያን አማኞች ስድብን ጠግበናል ፣ በአማላጅነታቸው የምንማጸናቸው ቅዱሳንን የሚነቅፉ "የሌላ ኢየሱስ ወታደሮች' ተሰልፈውብናል ። ከእኛ አልፎ "በሌላ ኢየሱስ" ስም ድንግል ማርያም ትሰደባለች ፣ ልክ እንደ "ዩዝ ኤንድ ስሮው ቁስ" እግዚአብሔር ለዘጠኝ ወር እንድታገለግለው ተጠቅሞ የተዋት ዓይነት አድርገው ስለ ድንግል ማርያም የሚናገሩ ሐሳውያን በ"ሌላ ኢየሱስ" ስም ተሳልቀውብናል ።
#ቅዱሳንን የሚሳደቡትንና ከአስተምህሮአቸውም ሳይቀር ቅዱሳንን በሚያሳድዱት ላይ የቅዱሳን አምላክ የድንግል ማርያም ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚፈርድባቸው አምናለሁ ። እውነት ነው !! ይህ በቅዱስ መጽሐፍ የምንረዳው ሐቅ ነው ፣ ኢየሱስ የቅዱሳኑን ስደት ፣ የራሱ ስደት ያደርገዋል ፣ የቅዱሳኑን መዘለፍ የራሱ መዘለፍ ያደርገዋል ፤ ለዚህም ነው ፦ "ሳውል!! ሳውል !! ለምን ታሳድደኛለህ ??" ያለው ፣ ይህ የቅዱሳን አምላክ፣ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰማይ በፍርድ ዙፋኑ አሁንም አለ፤ ይፈርዳል ። (ሐዋ.9:4)
222 views/\/\!|<@e|, 16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 18:15:21
እነዚህ ሰዎች ቁጥር አያውቁም እንዴ ግን? የውሸታቸውን ጥግ ሲነግሩ ግን እያያችሁ ነው? ኦጋዴን ላይ የተገኘው ቤንዚን ከምድር በታች 7 ትሪሊዬን ጫማ ጥልቀት ላይ ነው አሉን። ውሸታቸውን እስቲ እናጋልጠው።

አንድ ኪሎ ሜትር 3280 ጫማ ነው። ሳባት ትሪሊዬኑ ጫማ ምን ያህል ኪሎ ሜትር ይሆናል የሚለውን ስናሰላው 2,134,146,341.46 ጫማ ይሆናል። ሁለት ነጥብ 1 ቢሊዬን ገደማ ማለት ነው። መሬት ደግሞ ከአንደኛው ጫፍ ውስጥ ለውስጥ በስተናት በሌላኛው ጫፍ ብንወጣ ርዝመቷ 12742 እንደሆነ ሳይንስ ይነግረናል።

እነ ታከለ በነገሩን መሠረት ኦጋዴን ላይ ያገኙት ቤንዚን ርቀቱ መሬትን በስተው አልፈዋል። ማለፍ ብቻ ሳይሆን መሬትን በስተዋት ካለፉ በኋላ መሬት ካላት ዲያሜትር በ 167,489 እጥፍ አልፈው ሄደዋል። ሌላ ፕላኔት ሁሉ ሳይቆፍሩ አይቀሩም።

የኢትዮጵያን ሕዝብ በምን ያክል ውሸት እንደሚያደነዝዙት ይህ አንዱ ማሳያ ነው!
297 views/\/\!|<@e|, 15:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 08:02:12
ይደልዎ
478 views/\/\!|<@e|, 05:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 18:31:03
520 views/\/\!|<@e|, 15:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 18:30:17 ለመጸለይ ትጋት ላለመጸለይ ምክንያት ለሌለኝ ለእኔ ጸልዩልኝ!
━━━━━━━༺✞༻━━━━━━

ሰው "የማትጸልየው ለምንድነው?" ሲባል ቀዳሚ መልሱ "ጊዜ ስለሌለኝ" የሚለው ነው። በጎውን መንገድ የሚያሳዩት ግን ይህን ይላሉ "የማንጸልየው ጊዜ ስለሌለን ሳይሆን ጊዜው የሌለን ስለማንጸልይ ነው!"

ምስጋናው ክቡር ልመናው ሥሙር የሆነለትማ ጸሎቱ ውኩፉ ኃጢዓቱ ግዱፍ ጊዜውም ትሩፍ ነው! ከሰዎች ጋር የሚያወራበትን ጊዜ የሚያሳጥር ፡ ከአምላኩ ጋር ለመነጋገር የሚጥር ሰው እንዴት ያለው "ዕድላም" ነው እናንተ! ከንግግሩ የሚቀንስ ከኃጢዓቱ ይቀንሳልና።

☞ ወዘይጸልእ ብዙኃ ነቢበ ያሐጽጻ ለኃጢዓቱ ⇨ አብዝቶ መናገርን የሚጠላ ሰው ኃጢዓቱን ያሳንሳታል【ሲራ ፱፥፮】

የበረሐ አባቶችን ጥበብ የሚነግረን መጽሐፍ እንዲህ ስላለው ንግግር የመቀነስ ዝምታን የማብዛት ሕይወት የሚከተለውን አስተማሪ የቅዱስ አርሳንዮስ ታሪክ ያስቀምጣል።

ቅዱስ አርሳንዮስ ሁል ጊዜ ተሐራሚ ሆኖ በመዓልትና በሌሊት ይጸልይ ነበር:: ሰዎች ሲያነጋግሩት እንኳ ከአምላኩ ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን ግንኙነት ላለማቋረጥ ጸጥ ይል ነበር:: ለዚህም በኣቱን ከገዳመ አስጤክስ አስር ምዕራፍ ያህል ርቆ ያለ ሲሆን አንድ ቀን አባ መቃርዮስ "ከእኛ ርቀህ የምትኖረው ስለምድነው?" ቢለው "ለእኔስ ከሰውና ከእግዚአብሔር ጋር አንድነት መኖር ባይቻለኝ ነው:: የእግዚአብሔር ፈቃድ አንዲት ስትሆን የሰው ፍፈቃዱ ግን ልዩ ልዩ ብዙም ነው"ብሎታል:: ሌሎችም አኃው ሄደው በአርምሞ እንዲህ ጸንቶ ስለመኖሩ ቢጠይቁት "I have often regretted the words I have spoken, but I have never regretted my silence ⇨ በተናገርኳቸው ቃላቶች ብዙ ጊዜ ተጸጽቼ አውቃለሁ፣ በዝምታዬ ግን በፍጹም ተጸጽቼ አላውቅም" አላቸው:: 【+ St. Arsenios the Great 】

ሰው ከሰው ጋር ከመጨዋወት እና አብሮ ከመኖር የራቀውን ያህል ከእግዚአብሔር ጋር በጸሎት ለመነጋገርና አንድ ለመሆን የበቃ ይሆናልና::

ጌታችንን በምናወድስበት ጸሎትም በልቡናው ንጽሕና ተወዳጅነቱ የተመሰከረለትን አበ ልሣናት ባሕረ ጥበባት ቅዱስ ዮሐንስን የሚያነሳ ይህን እጅግ ጠቃሚ ተማጽኖ እናገኛለን ፦

ሰላም ለአፉከ ለዮሐንስ ዘሰዐሞ፣
ንጽሐ ሕሊናሁ ወልቡ ለዓይነ ፍትወትከ ሶበ አደሞ፣
ኢየሱስ ክርስቶስ መፍቀሬ የዋሃት እምተቀይሞ፣
ጸግወኒ ማዕፆ አፍ እንተ ይእቲ አርምሞ፣
ለትዕግሥትከ ከመ አእምር ዐቅሞ።

ጌታዬ ኢየሱስ ሆይ፤ ዮሐንስን ለሳመው መለኮታዊ አፍህ ሰላምታ ይገባል። የልቡናው ንጽሕና በፊትህ ተወዳጅነትን አግኝቷልና። ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤ ቅያሜ በአንተ ዘንድ ቦታ የለውም ቸርነት ግን የባሕርይህ ነው። ስለዚህ የትዕግሥትህን መጠን (ጥቅም) አውቅ ዘንድ። አፌም ክፉ ከመናገር ይቆጠብ ዘንድ የዝምታ ቁልፍ ስጠኝ።【መልክአ ኢየሱስ】

እንግዲህ በጎ ዘመን፡ መልካም ቀን፡ የተሻለ ጊዜ ለማየት አሁን ክፋትን እንቢኝ ተንኮልን ወዲያልኝ ብለን ብዙ እንጸልይ ብዙ ዝም እንበል፤ ባለቅኔው ሎሬት ከቆቃ የላኩትን ምክር እየሰማን እንደው ዝም ብለን እስኪ አብረን ዝም እንበል።

አብረን ዝም እንበል
·
·
·
ከሰው ኳኳታ እንነጠል
ለአንድ አፍታ እንኳ እንገለል
በእፎይታ ጥላ እንጠለል
ዝም ብለን አብረን ዝም እንበል።【ጸጋዬ ገብረመድኅን 1961 ቆቃ。】

✧ "ሕይወትን ሊወድ መልካሞችንም ቀኖች ሊያይ የሚፈልግ ሰው፥ ምላሱን ከክፉ ከንፈሮቹንም ተንኰልን ከመናገር ይከልክል፤" 【፩ጴጥ· ፫፥፲】

በመጨረሻውም መጨረሻ የምናገረው ነገር ቢኖር አለመናገርን ነው።

"አርምሞሰ ተፍፃሜተ ፍፃሜ ውእቱ" ይላል መጽሐፈ መነኮሳት፤ ይሔን ሁሉ ለመናገር ጊዜ የነበረኝ ለመጸለይ ግን ጊዜ አጠረኝ፤ ለመጸለይ ትጋት ላለመጸለይ ምክንያት ለሌለኝ ለእኔ ጸልዩልኝ! ◆




ዲ/ን ዶ/ር ቴዎድሮስ በለጠ

⟟ ከደብረ ብርሃን [ በተወለድኩበት ቀን ነሐሴ ገብርኤል ፳፻፲፬ ዓ.ም ]
473 views/\/\!|<@e|, 15:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 07:03:49
ይህ ትምህርት ቤት ቅዱስ ያሬድ ት/ቤት ደ/ማርቆስ ካምፖስ እንደሆነ ከመጽሐፈ ገጽ መረጃ አግኝቻለሁ፡፡ ልጆችን በዚህ መልኩ ዐውቀው እንዲያድጉ መሥራት እጅግ አስፈላጊ ነው። ያሳድግልን!

በሰላመ ቅዱስ ገብርኤል መልአክ፡ ኦ እግዝእትየ ማርያም ሰላም ለኪ፡ ድንግል በህሊናኪ ወድንግል በሥጋኪ፡ እመ እግዚአብሔር ጸባዖት፡ ሰላም ለኪ፡ ቡርክት አንቲ እም አንስት ወቡሩክ ፍሬ ከርሥኪ፡ ተፈሥሒ ፍሥሕት ኦ ምልእተ ጸጋ እግዚአብሔር ምስለኪ: ሰአሊ ወጸልዪ በእንቲአነ ኀበ ፍቁር ወልድኪ፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ከም ይሥረይ ለነ ኃጣውኢነ።
535 views/\/\!|<@e|, 04:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 05:43:22
454 views/\/\!|<@e|, 02:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 05:43:16 ማሳሰቢያ፤ በአርቲስት መቅደስ ፀጋዬ!

የኔ ታዋቂነትም ሆነ እንዳላችሁኝ የዕውቀት ደረጃ የአምላኬን እናት በዐደባባይ እንዳላወድሳት የሚያደርገኝ ከሆነ #ጥንቅር_ብሎ_ይቅር! ቁርጥ መልሴ ነው።

ይህ የእኔ የግል ገጼ ሲሆን የኔን የግል አመለካከቶቼን እና እምነቶቼን የማንፀባርቅበት ነው። ሃይማኖቴ ደግሞ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መሆኑ ይታወቃል። ኦርቶክሳዊነቴን እናትና አባቴ ስላወረሱኝ ብቻ ሳይሆን ዐውቄው፣ ተረድቼው ትክክለኛነቱን አምኜ አምላኬን የማመልክበት ሃይማኖቴ ነው።

ትናንት የለጠፍኩትን የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ተከትሎ የመጡልኝን አንዳንድ የሌላ እምነት ተከታዮች አስተያየቶችን ንቄ ለመተው ብሞክርም በግል ስልኬ እየደወሉ ቅድስት ድንግል ማርያምን የማወድስበት መንገድ ከኔ እንደማይጠበቅ መንገር እና ስለ አምላኬ ለኔ ለመስበክ መሞከርን ግን #ከንቀት_ቆጥሬዋለሁ። እናም ይህ ሁኔታ ስለተደጋገመብኝ ነው አቋሜን ለመግለፅ ዐደባባይ መውጣት የፈለግኩት።

የኔ ታዋቂነትም ሆነ እንዳላችሁኝ የዕውቀት ደረጃ የአምላኬን እናት በዐደባባይ እንዳላወድሳት የሚያደርገኝ ከሆነ #ጥንቅር_ብሎ_ይቅር! ቁርጥ መልሴ ነው። እናቴን ገና መቼ አመሰገንኳትና! መቼ ገና አወደስኳት!.....በእኔ በኃጢያተኛዋ እና በደካማዋ ሴት የሷ ስም ሲጠራ ክብሩ ለኔ ነው! አምላኬ በምሕረቱ ባይጎበኝኝ፣ እመ አምላክ ባታማልደኝ የአምላኬ ማደሪያ የሆነችውን የእናቴን ስም የመጥራት ዐቅሙስ ባልኖረኝ ነበር! እና እስትንፋሴ እስካለች #ቅድስት_ድንግል_ማርያምን እናቴን አወድሳታለሁ! ስለ ማርያም አማላጅነት እመስክራለሁ!

እግዚአብሔር ይመስገን በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በሙሉ የአምላክነት ክብሩ አለ። ቤተክርስቲያን በቅዳሴዋ፣ በማህሌቷ በመዝሙሯ አምልኮ የምታደርገው ለኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው። እናም የ80 ቀን ልጅ እያለሁ በጥምቀት የተቀበልኩትና የማውቀው የማመልከው አምላክ እያለኝ ጌታን ተቀበይ ብሎ ሙግት ለኔ አላዋቂነት ነው!

የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ የሆናቹ እጅግ የምወዳችሁ እና የማከብራቸው ጓደኞቼ እንዲሁም ቤተሰቦቼ አብረን በቆየንባቸው ዓመታት አንድም ቀን ስለእምነት ልዩነት ሳታነሱ አብሮነታችን ፀንቶ እንዲቆይ ስላደረጋችሁ ሳላመሰግናቹ አላልፍም። ለናንተ ያለኝ ፍቅር ብቻ ነው ተባረኩልኝ

በስተመጨረሻም ሀገር በከፋ ችግር ላይ ባለችበት በአሁኑ ወቅት እንደ ሕዝብ አንድነታችንን አጠናክረን በየእምነት ተቋማችን አምላካችን ለሀገራችን ምሕረቱን እንዲያመጣ እየከፋፈለን፣ እያጠፋን ካለው መንፈስ እንዲያላቅቀን መጸለይ እንጂ አንዱ የአንዱን ሃይማኖት በማንቋሸሽ ምዕመን ምልመላ ላይ መሯሯጥ አያዋጣንም።

ቸር እንሰንብት ወዳጆቼ!!
493 views/\/\!|<@e|, 02:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ