Get Mystery Box with random crypto!

እነዚህ ሰዎች ቁጥር አያውቁም እንዴ ግን? የውሸታቸውን ጥግ ሲነግሩ ግን እያያችሁ ነው? ኦጋዴን | Michael Z Ethiop

እነዚህ ሰዎች ቁጥር አያውቁም እንዴ ግን? የውሸታቸውን ጥግ ሲነግሩ ግን እያያችሁ ነው? ኦጋዴን ላይ የተገኘው ቤንዚን ከምድር በታች 7 ትሪሊዬን ጫማ ጥልቀት ላይ ነው አሉን። ውሸታቸውን እስቲ እናጋልጠው።

አንድ ኪሎ ሜትር 3280 ጫማ ነው። ሳባት ትሪሊዬኑ ጫማ ምን ያህል ኪሎ ሜትር ይሆናል የሚለውን ስናሰላው 2,134,146,341.46 ጫማ ይሆናል። ሁለት ነጥብ 1 ቢሊዬን ገደማ ማለት ነው። መሬት ደግሞ ከአንደኛው ጫፍ ውስጥ ለውስጥ በስተናት በሌላኛው ጫፍ ብንወጣ ርዝመቷ 12742 እንደሆነ ሳይንስ ይነግረናል።

እነ ታከለ በነገሩን መሠረት ኦጋዴን ላይ ያገኙት ቤንዚን ርቀቱ መሬትን በስተው አልፈዋል። ማለፍ ብቻ ሳይሆን መሬትን በስተዋት ካለፉ በኋላ መሬት ካላት ዲያሜትር በ 167,489 እጥፍ አልፈው ሄደዋል። ሌላ ፕላኔት ሁሉ ሳይቆፍሩ አይቀሩም።

የኢትዮጵያን ሕዝብ በምን ያክል ውሸት እንደሚያደነዝዙት ይህ አንዱ ማሳያ ነው!