2022-09-03 09:12:05
ጤና ይስጥልኝ እንደት ቆያችሁ ውድ የጥበብ ቤተሰቦች
=> ሰላም ጤና በያላችሁበት ተመኘሁ
በቅንነት ሼር ያድርጉ
#ስንፈተ ወሲብ
#ስንፈተ ወሲብ ወይም የብልት መልፈስፈስ ችግር የሚሊየኖች ወንዶች ችግር መሆኑ ይታወቃል። ይህ ቢሆንም
ይህን ችግር በተለያየ መንገድ መቅረፍ ይቻላል።
አብዛኛዎቹ ወንዶች ችግሩን የሚያባብሱት ስለችግራቸው ለማንም ሳያማክሩ በውስጣቸው አምቀው በመያዛቸውና ይህም ለጭንቀትና ውጥረት እንድሁም ፍራቻ ምክንያት በመሆኑ ነው።
ከዚህ ችግር ለመውጣት የመጀመሪያው ቁልፍ መንገድ በግልፅ ስለችግሩ ከባለሙያ ጋር መነጋገር ነው። ይመኑ።
ይህ ችግር የርስዎ ብቻ አይደለም። የሚሊየኖች ነው። አብዛኛዎቹ ከዚህ
ችግር ወጥተዋል። ለመውጣት ያልሞከሩት ደግሞ እዛው ናቸው።
እርስዎስ ምን ያህል ግልፅ ነዎት?
እስኪ በሚከተሉት አስር ጥያቄዎች እንጀምርና እንቀጥላለን።
፩. ያጨሳሉ?
ካጨሱ ያቁሙት። ማቆም ከባድ መሆኑን ብንረዳም አጫሽ ከሆኑ ከዚህ ችግር ለመውጣት አይችሉም። በሲጋራ ውስጥ ያለው ኒኮቲን ብልት እንዲወጠር የሚያደርጉትን የደም ቱቦዎች ያጨማድዳቸዋል። ይህም ብልት
በደም ተሞልቱ መጠኑ እንዳይጨምርና እንዳይጠነክር ይዳርገዋል።
፪. አመጋገበዎት እንደት ነው?
አመጋገብ ትልቅ ተፅእኖ ያሳድራል። የኮሌስትሮል መጠንን የሚጨምር ክብደትን የሚጨምሩ ምግቦች ለስንፈተ ወሲብ አጋላጭ ናቸው። በራሱ ውፍረት ስንፈተ ወሲብን ያመጣል። ስለዚህ ጤናማ ምግቦችን ይመገቡ።
ጥራጥሬ፣ ፍራፍሬ፣ ቅጠላቅጠል፣ ማርና ሌሎችን
፫. አልኮል ያዘወትራሉ?
አልኮል ከመጠን ሲያልፍ ድብርት ያመጣል። ፆታዊ ስሜትንም ይገላል። ስለዚህ ይቀንሱ። ይተውት
፬. በየቀኑ የአካል እንቅስቃሴ ያደርጋሉ? በቀን ከ20-30 ደቂቃ ስፓርታዊ
እንቅስቃሴ ቢያደርጉ የራስ መተማመንዎን ከመጨመረዎ በላይ ወደብልት የሚሄደው የደም መጠን እንዲጨምር ያደርጉታል።
፭. በህይዎተዎ ጭንቀት፣ ውጥረትና ፍራቻ አለበዎት?
እነዚህ ችግሮች ካሉ በፆታዊ ግንኙነት ውጤታማ ስለማይሆኑ ያስወግዱ። ይቀንሱ።
፮. ሌላ የጤና ችግር እንደሌለበዎት አረጋግጠዋል?
የጤናዎትን አጠቃላይ ሁኔታ ይወቁ። የችግሩ ምንጭ ሌላ የጤና ችግር ሊሆን ስለሚችል አጠቃላይ የጤና ምርመራ ያድርጉ።
፯. ከትዳር አጋር ወይም ከጓደኛ ጋር ስለ ችግሩ ተወያይተዋል?
ይህን ችግር ደብቀው ሊቀርፉት ስለማይችሉ በግልፅ ተነጋግረው በተቃራኒ ፆታ ፆታዊ አነሳሽነት ችግሩን ለመቅረፍ መሞከር ጥሩ ነው። በኩርፊያና ንትርክ ችግሩ አይቀረፍም።
፰. የራስዎን የSex ህይዎት ከሌሎች ጋር ለማወዳደር ይሞክራሉ?
ይህ የበታችነት ስሜትን ስለሚፈጥርበዎት አያስቡት። ውጤታማም አያደርገዎትም።
፱. ባለሙያ አማክረዋል?
ካላማከሩ ሳይዘገዩ ያማክሩ።
፲. የወሲብ ግንኙነት አይሳካልኝም ብለው ያስባሉ?
እንድህ ካሰቡ ተሳስተዋል።
# እስከ አሁን ባለው መረጃ በአለም ላይ 40 ሚሊዮን ወንዶች የስንፈተ ወሲብ
ችግር አለባቸው።
ስንፈተ ወሲብ ስንል የወንድ ልጅ ብልት ለግብረስጋ ግንኙነት ብቁ ሆኖ አለመገኘት ማለት ነው። ይህ ችግር ደግሞ መፈታት አለበት። ይፈታልም። ካልተፈታ ስነ-አእምሮአዊ ጠባሳው ከባድ ስለሆነ።
#መቸ ነው የሚከሰተው?
በቂ የሆነ የደም ፍሰት ወደ ብልት ሳይሄድ ሲቀር
ብልትን የሚቆጣጠረው ነርቭ ላይ ችግር ካለ
በግንኙነት ሰአት ጭንቀት፡ ፍራቻና ውጥረት ካለበዎት
ስሜትዎ የሚዘበራረቅ ከሆነ
የደም ቱቦ መጥበብ፡
የልብ ችግር
ከፍተኛ ደም ግፊት
ከፍተኛ ስኳር መጠን
ውፍረት ካለ
# ከላይ የዘረዘርናቸው ለክስተቱ ከሌሉበት ችግሩ ስነ-አእምሮአዊ ነው ማለት ነው።
መቸና ለምን ስንፈተወሲብ እንደሚፈጠር ካወቅን በቀላሉ ማካም ይቻላል።
ፆታዊ ግንኙነት ስሜት ሲፈጠር ነርቭ ኬሚካል ወደ ብልት ይለቃል። በዚህ
ወቅት ብልት ውስጥ ያሉ የደም ቱቦዎች ይሰፋሉ። በውስጣቸውም ብዙ ደም
ያከማቻሉ። ይህን ጊዜ ብልት ይወጠራል። ይጠነክራል። ችግሩ ካለ ግን ይህ አይሆንም።
የብልት መልፈስፈስ ወይም ስንፈተ ወሲብ ከሚከተሉት የጤና ችግሮችም ሊሆን ስለሚችል አጠቃላይ የጤና ምርመራ ማድረግ እጅግ ጠቃሚ ነው። ከልብ ቾግር፣ ከስኳር በሽታ፣ ከውፍረት፣ ከከፍተኛ ደም ግፊት፣ ከነርቭ ችግር፣ ከደም ቱቦ መጥበብ፣ ከሆርሞንና ሌሎችም ችግሮች አኳያ ሊሆን ይችላል።
እንደቀላል ይህን ችግር ዝም ካሉት ለራስዎት የሚሰጡትን ክብር ይቀንሳል፡ በራስ መተማመንን ያወርዳል በትዳርና ፍቅረኛ መሀል ክፍተትን ይፈጥራል።
#ዋና ምክናየቶች
የእድሜ መጨመር ወይም እርጅና
የስኳር ታማሚ መሆን
ከፍተኛ ደም ግፊት
የልብ ችግር
የኮሌስትሮል መጠን መጨመር
ማጤስ
አልኮል ጠጭ መሆን
ወፍራም መሆን
የአካል እንቅስቃሴ አለማድረግ
የመድሀኒቶች ሱሰኛ መሆን
አድሜ መጨመር ስንል ለሁሉም ማለት አይደለም። ብዙ ወንዶች እስከ 100 አመት አካባቢ ውጤታማ ናቸው።
#በተጨማሪ
➤ በቂ ደም ወደብልት አለመሄድ
➤ ብልት በቂ ደም መያዝ አለመቻሉ
➤ የነርብ ጫፍ ብልት ላይ አለመድረሱ
➤ የብልት ደም ቱቦዎች መጎዳት
➤ የተለያዩ መድሀኒቶች የጎንዮሽ ተፅእኖ
#አስቡ ከላይ የዘረዘርናቸው ችግሮች ካልሆኑስ? አይጠራጠሩ የችግሩ ምክንያት ስነ-አእምሮአዊና የስሜት ችግር የፈጠረው ነው።
ትክክለኛ የግብረ ስጋ ግንኙነት
አእምሮ፡ ስሜትና አካላችን ተናበው በአንክሮ የሚከወን ነው። በሩጫ፣ በፍራቻና በውጥረት በውክቢያ የሚሆን አይደለም።
# ግንኙነት የሚከተሉት ካሉበት ስነ አዕምሮአዊ ችግሮችን ተላብሶአል ማለት
ነው።
ድብርት
ጭንቀት
ውጥረት
ከትዳር አጋር ወይም ፍቅረኛ ጋር ፀብ ካለ
በህይዎት ውስጥ እረፍት ከሌለ
በማህበራዊ ህይዎት ፣በባህልና እምነት የሚደርስ ተፅእኖ መኖር
ለግብረ ስጋ ግንኙነት ብቁ አይደለሁም የሚል እምነት ቀድሞ መኖር
የዚህ አይነት ችግር ከገጠማችሁ ያናግሩን
ለበለጠ መረጃ ከስር በተቀመጠው ስ.ቁ በስራ ሰዓት ይደውሉልን።
አድራሻ - ሽናሻ ቤንሻንጉል ጉምዝ
ስ. ቁ 0915854013
በኢሞ 0913255901
በዋትሳብ -0915854013
በቴሌግራም https://t.me/Mngistiu
የቴልግራም ቻናል https://t.me/mengistut
የቴሌግራም ግሩፕ https://t.me/Mengistuabebe
133 viewsመንግስቱ, 06:12