Get Mystery Box with random crypto!

Medicine Daily

የቴሌግራም ቻናል አርማ medicinedaily — Medicine Daily M
የቴሌግራም ቻናል አርማ medicinedaily — Medicine Daily
የሰርጥ አድራሻ: @medicinedaily
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 814
የሰርጥ መግለጫ

✍️Trusted Health Information for You
✍️የጤና፣ የህክምናና የመድሃኒት መረጃዎችን የምናቀርብበት ቻናል።
✍️Guidelines
✍️Updates
✍️Books
✍️Health tips
✍️Healthcare Jobs & Scholarships

www.facebook.com/medicinedailynet

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-30 12:34:30 የጓደኝነት ተጽኖ ይልቃል።
****
አስተማርህን ከልብህ ብታደንቀውም አንኳን፥ ህይወትን የሚትኖረው ከጓደኛህ ህይወት እየቀዳህ ነው።
አንዳንዴ መልካም ያልሆኑ የጓደኞቻችን ባህርይ እያየን ስለምንታገስ ፥ ከጊዜ በኃላ ያንን ባህርይ ተላብሰን ራሳችንን እናገኛለን።

ድብቁ የአዕምሯችን ክፍል በተደጋጋሚ የሚናያቸውንና የምንሰማቸውን ግደታ የመቀበል ባህርይ አለው ፤ ስለዝህ ከጓደኞቻችን በተደጋጋሚ ያየነው ህይወታችን ይሆናል። ምንም ያህል ጎበዝና ጠንቃቃ ሁን የተደጋገመልህ መልካምም ይሁን መጥፎ ወደ ልብህ መግባቱ አይቀርም።

ስለዝህ ጓደኛህን መምረጥ መዳረሻህን መምረጥ ነው።
ነገ የት መድረስ ትፈልጋለህ? ህልምህ ጓደኛን ይምረጥልህ!

ከሀብታም ጋር የዋለው ፍላጎቱ ካለ ሀብታም እንደምሆን ፥ ከጠቢብ ጋር የዋለው ጠቢብ እንደምሆን፥ ከስንፍና ጋር የዋለውም ከስንፍና አያመልጥም። ምርጫም የለህም።

ህይወት ተላላፊ ነው።
በኢኮኖሚ አቅማቸው እየገነኑ የመጡ ቻይናውያን የእርስበርስ መቀራረብ ተጽኖ ነው። አንድ ቻይናዊ ሌላ ሀገር ሄዶ ሲቀጠር ፥ የሚያገኘውን ደመወዝ ንግድ ለመጀመር ነው የምያውለው፤ ሌላውም ቻይናዊ ጓደኛውም! የመቀራረብ ተጽኖ!
መልካም የንግድ ምሣሌ በኢትዮጵያ ውስጥ ያላቸው የጉራጌ ልጆች በጎረቤት ወይም በጓደኛ ወይን በመቀራረብ የመጣ ነው።

በአዕምሮ አጠቃቀም የተመሠከረላቸው የምስራቅ ዓለም ሰዎች የመቀራረብ ተጽኖ ነው።

ጓደኛን፥ በተደጋጋሚ የሚቀርብህን ሰው መምረጥ ህይወትን መምረጥ ነወ።
መሪዎች ብቻቸውን የምራመዱ ሰዎች ናቸው፤ ጓደኞቻቸው መጽሐፍቶችና በአላማ የምኖሩ ሰዎች ናቸው።
Via: Ezra Ze Prince

የተወደዱ ዉዶች መልካም ቀን!
@medicinedaily

ይቀላቀሉን https://t.me/joinchat/AAAAAE2nAI1Hk_f9ByhTVQ
552 viewsedited  09:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 15:03:51 "የህግና የህክምና ትምህርቶችን ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ትምህርቶች የመውጫ ፈተና ይሰጣል"
- ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር

* ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች ተማሪዎቻችሁን አዘጋጁ !

የመውጫ ፈተና በ2015 ዓ/ም መሰጠት ይጀምራል። ይህን በተመለከተ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለኢፕድ ከሰጡት ማብራሪያ ፦

" ... በሙሉ አቅማችን እየተዘጋጀን ነው። የሚቀር ነገር አይደለም ፤ 2015 ትምህርት ዘመን ማብቂያ ላይ ፤ ከዚህ በፊት እንደነበረው ዝም ብሎ ዲግሪ የሚሰጥበት ነገር ሀገሪቱን በጣም ክፉኛ ጎድቷታል የሚል እምነት አለን።

ይሄንንም ከዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንቶች ጋር፣ ከግል ኮሌጆች ፕሬዜዳንቶች እና ኃላፊዎች ባለቤቶች ጋር ፣ ከዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ተማሪዎች ጋር ሰፊ ውይይት ያደረግንበት ነው።

ይሄ አዲስ ሀሳብ አይደለም አተገባበሩ ነው አዲስ የሆነው። ከዚህ በፊት ተሞክሮ ተቃውሞ ስለንበር ነው የተተወው።

የህግና የህክምና ትምህርቶችን ብቻ እንዲሰጡት አድርጎ አሁንም እየተሰጡ ሌሎች በሙሉ ተትተው ነበር።

አሁን ግን በአጠቃላይ ከከፍተኛ ትምህርት ጥራት ችግር ጋር በተገናኘ ምንም ልንወጣው የማንችለው እና ያን ጥራት ለማስተካከል ዩኒቨርሲቲዎቹ በራሳቸው ባስተማሩበት እና እራሳቸው በሰጡት ፈተና ብቻ የሚለኩበት ሁኔታ ከጀርባው ያለ ጠንካራ የሞራል መሰረት ይጠይቃል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ እራሳቸው ድግሪ ስንሰጥ ለማህበረሰቡ ይሄ ሰው እንዲህ እንዲህ አይነት ትምህርቶችን፣ እውቀቶችና ክህሎቶች አሉት ብለን ነው እየነገርን ያለነው።

... ከዚህ በፊት አንዱ የነበረው ችግር ማሳለፍ የሚባል ነገር አለ። ዝም ብሎ ማሳለፍ ምክንያቱም ተማሪዎች ከወደቁ የትምህርት ክፍሉን ድክመት ያሳያል እየተባለ ሲሳራበት የነበረው ነገር ምን ያህል ሀገሪቱን እንደጎዳት አሁን ለውይይትም የሚቀርብ አይደለም።

እኔ በዚህ ጉዳይ ባለፉት ሰባት (7) ወራት በትምህርት ዘርፍ ከሚሰሩ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንቶች የግል ኮሌጆች ባለቤቶች እንደዚህ አይን ያወጣ የለም መሆን የለበትም የሚል ክርክር አልሰማሁም። ሁሌ የሚሰማው ለምን በኛ ጊዜ ? ለምን ባንተ ጊዜ ለምን በሌላውስ ሰው ጊዜ የሚለውን ልትመልስ አትችልም ይሄ ዝም ብሎ ደረቅ ክርክር ነው።

በአንድ በሆነ ጊዜ መጀመር አለበት ምክንያቱም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጥራት ላይ እየደረሳ ያለው ጉዳት ሀገሪቱን ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈላት ነው። ይሄንን ዝም ብለን ማለፍ አንችልም ብለን እየሄድንበት ነው።

ለተማሪዎችም ፣ ለወላጆችም፣ ለቤተሰብም አንድ (1) ዓመት የመዘጋጃ ጊዜ ሰጥተናል። ለኮሌጆችም ተማሪዎቻቸውን እንዲያዘጋጁበት ጊዜ ሰጥተናል ይሄን ጊዜ በደንብ ተጠቅመው ስራቸውን መስራት አለባቸው።

ይሄ የመውጫ ፈተና የተማሪዎች ፈተና ብቻ አይደለም። ከተማሪዎች በላይ የትምህርት ክፍሎች፣ የኮሌጆች ፣ የዩኒቨርሲቲዎች ፈተና ነው። ምን እያደረጉ ነው ዩኒቨርሲቲዎቹ የሚለውን እንደትምህርት ሚኒስቴር ከዚህ የምናገኘው ፤ እነዚህ ኮሌጆች ፣ ዩኒቨርሲቲዎች በእርግጥም ተማሪዎችን እያበቁ ነው ? ወይስ የዲግሪ ወፍጮ ቤት እንደሚሏቸው ዝም ብሎ ጊዜ እያስቆጠሩ ድግሪ የሚሰጡ ናቸው የሚለውን የምንለይበት ነው።

ስለዚህ የሚቀር አይደለም። ሁሉም እንደማይቀር አውቆ የተሰጠውን የመዘጋጃ ጊዜ በደንብ ተጠቅሞ ትምህርትን በደንብ አስተምሮ በደንብ አስጠንቶ ቢያዘጋጅ ነው የሚሻለው "

Compiled by tikvahethiopia
@medicinedaily

Join fore more

https://t.me/joinchat/AAAAAE2nAI1Hk_f9ByhTVQ
295 views12:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 01:12:27 ቋቁቻ (Pityriasis _Versicolor)
****
>> ቋቁቻ ማላሰዚአ (Malassezia) የሚባል ፈንገስ የሚመጣ በሽታ ነው።

>> ይህ አይነት ፈንገስ በተፈጥሮ በሰው እና በእንስሳት በላይኛው የቆዳ ክፍል የሚገኝ ሲሆን በተለያየ ምክንያት በተወሰኑ ሰዎች ቋቁቻ የሚባል የቆዳ ህመም ያመጣል።

የቋቁቻ መስፋፋት

>> አብዛኛው ግዜ ከፍተኛ ሙቀት ባላቸው አከባቢዎች የተለመደ ሲሆን አንዳንድ ግዜ እስከ 50% ከፍተኛ ሙቀት ባለው አከባቢ የሚኖሩ ሰዎች በዚህ በሽታ ሊጠቁ ይችላሉ።

>> በሰለጠኑ አገሮች ዝርጋታው በመካከለኛ ከ 2-8% ሊደርስ ይችላል።

>> በስፋት ከ 15-24 አመት የእድሜ ክልል ይከሰታል። ምክያቱም ደግሞ በከፍተኛ የስራ ጫና ቅባት የሚያመነጩ እጢዎች (Sebaceous glands) ምከንያት ነው።

ቋቁቻ የመከሰት ምክንያት

>> አብዛኛው ግዜ በጤናማ ሰዎች ይከሰታል። ነገርግን የተለያዩ ሁኔታዎች ቋቁቻ እንዲከሰት በር ይከፍታሉ።

ከነዚህ አንዳንዶቹ ፦
> ቤተሰባዊነት ወይም በዘር (Genetic predisposition)
>በሞቃታማ አከባቢ መኖር
> የበሽታ መቋቋም ብቃት ማነስ (Immunodeficiency)
> አቅም ማነስ (በኤችአይቪ ኤድስ ፣ስኳር ፣ኮርቲኮስትሮይድ ምክንያት ወዘተ...(immunosuppression )
> የምግብ እጥረት
> እርግዝና
> ቅባት የበዛበት ምግብ ማዘውተር
> ኩኩሺንግ የሚባል ህመም ወዘተ...

የቋቁቻ ምልክቶች

>የቆዳ ቀለም ነጭ መሆን ወይም ጠቆር ጠቆር ማለት
* አብዛኛው ግዜ በደረት እና ጀርባ አከባቢ መፈጠር። አንድአንድ ግዜ ደግሞ በፊት ፣እጅና እግር ሊከሰት ይችላል።
> በጥቂት ሰዎች ቆዳ ማሳከክ እና መቆጣት ሊኖር ይችላል።

የቋቁቻ ህክምና(Treatment)

>> ለቋቁቻ የሚሰጡ መድሀኒቶች በህመሙ አይነት ይወሰናል።
> የሚቀቡ ፣በአፍ የሚዋጥ ክኒኖች እና የተለያየ አይነት መድሀኒት አለው። የሚወሰድበት ግዜ ከ 2 ሳምንት እስከ 1 ወር እና ከዚያ በላይ ሊወስድ ይችላል።

መልካም ጤንነት!!
ለወዳጅ ዘመዶ #ሼር ያድርጉ!!!
ስለሚከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን።
_
ተጨማሪ ወቅታዊና የተሟላ የጤና መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Join https://t.me/joinchat/AAAAAE2nAI1Hk_f9ByhTVQ
388 viewsedited  22:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 21:21:11
#ነፃ_ጥቅል_ከኢትዮ_ቴሌኮም !

ኢትዮ ቴሌኮም በ2014 በጀት አመት 61.3 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

ይህም የእቅዱን 87.6 በመቶ ነው ብሏል።

ይህን በማስመልከት ለሦስት ቀናት የሚቆይ ነጻ ጥቅል ስጦታ ማቅረቡን ገልጿል።

ኢትዮ ቴሌኮም ያስመዘገበውን ስኬት አስመልክቶ ከህብረተሰቡ ጋር ለመጋራት ሲል የዳታ፣ ድምፅ እና የመልዕክት ጥቅል ስጦታዎችን ማቅረቡን ነው ዛሬ ያሳወቀው።

በዚህም፦

1.5 ጌጋባይት ዳታ በቀን 512 ሜባ፤

45 ደቂቃ በቀን 15 ደቂቃ፤

100 መልዕክት በቀን 33 መልዕክቶችን፤

የ10 ደቂቃ አለምአቀፍ ጥሪ በቀን 3 ደቂቃ ለተጠቃሚዎች በነጻ አቅርቧል።

ስጦታው ከዛሬ ሐምሌ 21 ከሌሊቱ 06:00 ሰአት - እስከ ምሽቱ 12 ሰአት ድረስ ለ3 ቀናት ይቆያል

@medicinedaily
268 views18:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 16:59:24
የፋርማሲ ተማሪ የፍቅር ደብዳቤ (ጅንጀና በፋርማሲኛ)
*****
እንደ Brand Drug ውድ ለሆንሽው የአይኔ ማረፊያ ለጤናሽ እንደምን አለሽ? እኔ ካንቺ ናፍቆትና My Memory ከመበላሸቱ በስተቀር በጣም healthy ነኝ::

ውዷ ፍቅሬ አንቺን ካየሁ ቀን ጀምሮ ትምህርቴን በ Warning እየተመዘገብኩ ተቸግሬአለሁ:: በአንፃሩ ውበትሽ ቁመናሽ ፀባይሽ ባጠቃላይ Stimulant የሆነው አንቺነትሽ በሌቤ ውስጥ የ blood pump ቦታ ሠጥቼዋለሁ::

ብዙ ጊዜ ላይብረሪ ላጠና ወይም assignment ልሰራ ገብቼ እንደ Tablet የጠሩ አይኖችሽ እንደ Paracetamol የተደረደሩ ጥርሶችሽ እንደ Capsule ቀጥቀጥ ያለ ጡቶችሽን እያየሁ አንቺን እንደ ፊሌም አይሻለሁ::

የፍቅርሽ ሰቀቀኑ ከቀን ወደ ቀን ጨምሮብኝ ስለተቸገርኩኝ ከጀሎሶቼ ጋር ተመካክሬ በ Pharmacoeconomics ፍቅሬን ደምሬና ቀንሼ ላቀርብልሽ ወስኛለሁ፡፡
ፍቅሬን በምን አይነት Drug mechanism ላስረዳሽ እንደምችል አላውቅም ችግሬን British Pharmacopoeia ላይ ብፈልግም ኮምፒውተሩ Error Question ብሎ ሀሳቤን መና አስቀርቶታሌል፡፡ አንቺ እንዲትወጂኝ ስል ያልወሰድኩት Drug የለም ትኩረትሽን ለመሳብ double ወስጄ አሣማ ብመስልም አንቺ ግን Adverse effect and Over dose እያልሽ ተቸግሬአለሁ::

ባንቺ የተነሳ የ Drug Company Clinical Trial እንስራብህ ብለውኛል:: ፊቴ በፍቅርሽ ከማበጡ የተነሳ Anti-depressant የወሰድኩ መስያለሁ:: አንቺን ሳይ ሌቤ Tachycardia እያደረገ ስላስቸገረኝ ችግሬን ተረድተሽ ከልብሽ Absorb እንድታደርጊኝ በ Pharmacotherapy ስም እጠይቃለሁ፡፡

Source: The Role Megazine, JU
1.9K viewsedited  13:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-26 14:52:04 #Vacancy
Armauer Hansen Research Inistitute (AHRI) is hiring!

Job Title: Lab Coordinator
Location: Addis Ababa
Career Level: Mid-Level (2-5 years)
Employment: Contractual
Salary: as Per AHRI scale
Job Requirement: BSc in Medical Laboratory Science with 4 years’ experience, Master’s degree in microbiology with 2 years’ experience from an accredited institution.
Click here to apply!
324 viewsedited  11:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 17:49:47 #LicensureExam
የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች
****
የጤና ሚኒስቴር በህክምና፣ ነርሲንግ፣ ሜዲካል ላብራቶሪ ሳይንስ፣ ጤና መኮንን፣ ሚድዋይፈሪ፣ ፋርማሲ፣ አንስቴዥያ፣ ዴንታል ሜድስን፣ ሜዲካል ራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂ፣ ሳይካትሪ ነርሲንግ፣ ኢመርጀንሲ & ክሪቲካል ኬር ነርሲንግ፣ ኢንቫይሮመንታል ሄልዝ እና ፔዲያትሪክ ነርሲንግ ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ለተመረቁ የጤና ባለሙያዎች በነሐሴ 2014 ዓ.ም ለሚሰጠው የብቃት ምዘና ፈተና ከሐምሌ 06/2014 ዓ.ም ጀምሮ የonline ምዝገባ እያካሄደ እንደሚገኝ ይታወቃል። ሆኖም ከተመዛኞች የትምህርት ማስረጃ ማጣራት (Authentication) ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን ጫና ግምት ውስጥ በማስገባት የonline ምዝገባው እስከ ሐምሌ 22/2014 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን እየገለጽን፣ ተመዛኞች በተጠቀሱት ቀናት ምዝገባችሁን እንድታጠናቅቁ እናሳስባለን፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0118275939/ 0118275937 መደወል ይቻላል፡፡

#MoH
@medicinedaily
741 views14:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 17:25:56
የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ ዓለም አቀፍ ድንገተኛ አደጋ ሲል ዛሬ አወጀ

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ድርጅታቸው የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ ዓለም አቀፍ ድንገተኛ አደጋ ሲል ማወጁን አሳውቀዋል።

#WHO
@medicinedaily
346 views14:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ