Get Mystery Box with random crypto!

የጓደኝነት ተጽኖ ይልቃል። **** አስተማርህን ከልብህ ብታደንቀውም አንኳን፥ ህይወትን የሚትኖ | Medicine Daily

የጓደኝነት ተጽኖ ይልቃል።
****
አስተማርህን ከልብህ ብታደንቀውም አንኳን፥ ህይወትን የሚትኖረው ከጓደኛህ ህይወት እየቀዳህ ነው።
አንዳንዴ መልካም ያልሆኑ የጓደኞቻችን ባህርይ እያየን ስለምንታገስ ፥ ከጊዜ በኃላ ያንን ባህርይ ተላብሰን ራሳችንን እናገኛለን።

ድብቁ የአዕምሯችን ክፍል በተደጋጋሚ የሚናያቸውንና የምንሰማቸውን ግደታ የመቀበል ባህርይ አለው ፤ ስለዝህ ከጓደኞቻችን በተደጋጋሚ ያየነው ህይወታችን ይሆናል። ምንም ያህል ጎበዝና ጠንቃቃ ሁን የተደጋገመልህ መልካምም ይሁን መጥፎ ወደ ልብህ መግባቱ አይቀርም።

ስለዝህ ጓደኛህን መምረጥ መዳረሻህን መምረጥ ነው።
ነገ የት መድረስ ትፈልጋለህ? ህልምህ ጓደኛን ይምረጥልህ!

ከሀብታም ጋር የዋለው ፍላጎቱ ካለ ሀብታም እንደምሆን ፥ ከጠቢብ ጋር የዋለው ጠቢብ እንደምሆን፥ ከስንፍና ጋር የዋለውም ከስንፍና አያመልጥም። ምርጫም የለህም።

ህይወት ተላላፊ ነው።
በኢኮኖሚ አቅማቸው እየገነኑ የመጡ ቻይናውያን የእርስበርስ መቀራረብ ተጽኖ ነው። አንድ ቻይናዊ ሌላ ሀገር ሄዶ ሲቀጠር ፥ የሚያገኘውን ደመወዝ ንግድ ለመጀመር ነው የምያውለው፤ ሌላውም ቻይናዊ ጓደኛውም! የመቀራረብ ተጽኖ!
መልካም የንግድ ምሣሌ በኢትዮጵያ ውስጥ ያላቸው የጉራጌ ልጆች በጎረቤት ወይም በጓደኛ ወይን በመቀራረብ የመጣ ነው።

በአዕምሮ አጠቃቀም የተመሠከረላቸው የምስራቅ ዓለም ሰዎች የመቀራረብ ተጽኖ ነው።

ጓደኛን፥ በተደጋጋሚ የሚቀርብህን ሰው መምረጥ ህይወትን መምረጥ ነወ።
መሪዎች ብቻቸውን የምራመዱ ሰዎች ናቸው፤ ጓደኞቻቸው መጽሐፍቶችና በአላማ የምኖሩ ሰዎች ናቸው።
Via: Ezra Ze Prince

የተወደዱ ዉዶች መልካም ቀን!
@medicinedaily

ይቀላቀሉን https://t.me/joinchat/AAAAAE2nAI1Hk_f9ByhTVQ