ቋቁቻ (Pityriasis _Versicolor) **** >> ቋቁቻ ማላሰዚአ (Malassezia) የሚባል ፈንገስ የሚመጣ በሽታ ነው። >> ይህ አይነት ፈንገስ በተፈጥሮ በሰው እና በእንስሳት በላይኛው የቆዳ ክፍል የሚገኝ ሲሆን በተለያየ ምክንያት በተወሰኑ ሰዎች ቋቁቻ የሚባል የቆዳ ህመም ያመጣል። የቋቁቻ መስፋፋት >> አብዛኛው ግዜ ከፍተኛ ሙቀት ባላቸው አከባቢዎች የተለመደ ሲሆን አንዳንድ ግዜ እስከ 50% ከፍተኛ ሙቀት ባለው አከባቢ የሚኖሩ ሰዎች በዚህ በሽታ ሊጠቁ ይችላሉ። >> በሰለጠኑ አገሮች ዝርጋታው በመካከለኛ ከ 2-8% ሊደርስ ይችላል። >> በስፋት ከ 15-24 አመት የእድሜ ክልል ይከሰታል። ምክያቱም ደግሞ በከፍተኛ የስራ ጫና ቅባት የሚያመነጩ እጢዎች (Sebaceous glands) ምከንያት ነው። ቋቁቻ የመከሰት ምክንያት >> አብዛኛው ግዜ በጤናማ ሰዎች ይከሰታል። ነገርግን የተለያዩ ሁኔታዎች ቋቁቻ እንዲከሰት በር ይከፍታሉ። ከነዚህ አንዳንዶቹ ፦ > ቤተሰባዊነት ወይም በዘር (Genetic predisposition) >በሞቃታማ አከባቢ መኖር > የበሽታ መቋቋም ብቃት ማነስ (Immunodeficiency) > አቅም ማነስ (በኤችአይቪ ኤድስ ፣ስኳር ፣ኮርቲኮስትሮይድ ምክንያት ወዘተ...(immunosuppression ) > የምግብ እጥረት > እርግዝና > ቅባት የበዛበት ምግብ ማዘውተር > ኩኩሺንግ የሚባል ህመም ወዘተ... የቋቁቻ ምልክቶች >የቆዳ ቀለም ነጭ መሆን ወይም ጠቆር ጠቆር ማለት * አብዛኛው ግዜ በደረት እና ጀርባ አከባቢ መፈጠር። አንድአንድ ግዜ ደግሞ በፊት ፣እጅና እግር ሊከሰት ይችላል። > በጥቂት ሰዎች ቆዳ ማሳከክ እና መቆጣት ሊኖር ይችላል። የቋቁቻ ህክምና(Treatment) >> ለቋቁቻ የሚሰጡ መድሀኒቶች በህመሙ አይነት ይወሰናል። > የሚቀቡ ፣በአፍ የሚዋጥ ክኒኖች እና የተለያየ አይነት መድሀኒት አለው። የሚወሰድበት ግዜ ከ 2 ሳምንት እስከ 1 ወር እና ከዚያ በላይ ሊወስድ ይችላል። መልካም ጤንነት!! ለወዳጅ ዘመዶ #ሼር ያድርጉ!!! ስለሚከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን። _ ተጨማሪ ወቅታዊና የተሟላ የጤና መረጃዎችን ለማግኘት፡- Join https://t.me/joinchat/AAAAAE2nAI1Hk_f9ByhTVQ 388 viewsedited 22:12