Get Mystery Box with random crypto!

#LicensureExam የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች **** የጤና ሚኒስቴር በህ | Medicine Daily

#LicensureExam
የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች
****
የጤና ሚኒስቴር በህክምና፣ ነርሲንግ፣ ሜዲካል ላብራቶሪ ሳይንስ፣ ጤና መኮንን፣ ሚድዋይፈሪ፣ ፋርማሲ፣ አንስቴዥያ፣ ዴንታል ሜድስን፣ ሜዲካል ራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂ፣ ሳይካትሪ ነርሲንግ፣ ኢመርጀንሲ & ክሪቲካል ኬር ነርሲንግ፣ ኢንቫይሮመንታል ሄልዝ እና ፔዲያትሪክ ነርሲንግ ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ለተመረቁ የጤና ባለሙያዎች በነሐሴ 2014 ዓ.ም ለሚሰጠው የብቃት ምዘና ፈተና ከሐምሌ 06/2014 ዓ.ም ጀምሮ የonline ምዝገባ እያካሄደ እንደሚገኝ ይታወቃል። ሆኖም ከተመዛኞች የትምህርት ማስረጃ ማጣራት (Authentication) ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን ጫና ግምት ውስጥ በማስገባት የonline ምዝገባው እስከ ሐምሌ 22/2014 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን እየገለጽን፣ ተመዛኞች በተጠቀሱት ቀናት ምዝገባችሁን እንድታጠናቅቁ እናሳስባለን፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0118275939/ 0118275937 መደወል ይቻላል፡፡

#MoH
@medicinedaily