Get Mystery Box with random crypto!

ኬልቅያስ

የቴሌግራም ቻናል አርማ keleotc — ኬልቅያስ
የቴሌግራም ቻናል አርማ keleotc — ኬልቅያስ
የሰርጥ አድራሻ: @keleotc
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 360
የሰርጥ መግለጫ

ኬልቅያስ የቴሌ ግራም ቻናል ኦርቶዶክሳዊ የነፍስ ማዕዶችን የሕይወት ቃል ወንጌለ መንግሥት የምስል ( vidio ) ትምህርቶች ፣ ያሬዳዊ መዝሙራትን ፣ የቅዱሳን ዜና ሕይወት ፣ ወቅታዊ የቤተክርስቲያን መረጃዎች፣ የአብያተ ክርስቲያናት እና የገዳማት ታሪክ ፣ የአባቶች ምክር ፣ የጠቢባን የአባቶች አባባል ፣ መንፈሳዊ ጥቅሶች እና ኪነ - ጥበባዊ ልዩ ልዩ አውዶች የሚቀርብበት ነው።

Ratings & Reviews

1.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-19 15:00:57 ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ ዳን 10:13

➼የኃይላት አለቃ ነው ቅዱስ ሚካኤል
➼የሞት ደብዳቤን የሚለውጥ ነው።
➼ከእሳት የሚያወጣ መልአክ ነው።
➼የእግዚአብሔርን ቅዱሳን የሚራዳ የቅዱሳን ወዳጅ ነው።
➼ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት ሲወጡ መንገድ መሪያቸው ሚካኤል ነው።
➼ጠላትን የሚያሳፍር ትዕቢተኛን የሚጥል እርሱ የመላእክት አለቃቸው ነው ቅ/ ሚካኤል።
"
""""" እንኳን ለመልአኩ የክብር በአል አደረሳችሁ""""

ይህ ተራዳኢ መልአክ በዚህች ቀን እግዚአብሔርን በሚፈሩት ዙሪያ ሰፍሮ ያዳነበት በኃይሉም ጠላትን የጣለበት በአሉ ነውና ይህችን ቀን አክብሯት እንድትከብሩባት።

ይህም የፋርስ ንጉሥ ሰናክሬም ኢየሩሳሌምን በከበባት ጊዜ በእግዚአብሔርና በሕዝቅያስ ላይ በድፍረት ተናገረ። "" አሁን ከእጄ የሚያድናችሁ የለም"" አለ።
ንጉሡ ሕዝቅያስም እርሱንና ሕዝቡን ሊያድን በታመነ በእግዚአብሔር ፊት ማቅ ለብሶ አመድ ነስንሶ ጸለየ አለቀሰ። እግዚአብሔርም ቅ/ሚካኤልን ላከው። ሰናክሬም የተመካባቸውን 185 ሺ ሰራዊት በትዕቢቱ አጣ። ይህን ያህል ወታደር በሊቀ መላእክት እጅ ተቀጣ። ለዚህ ዛሬ የዳንኤልን ዝማሬ ሕዝቅያስ ዘመረው።
""" ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ"""

.እኔም ምልጃውን አውቀዋለው በችግሬ ቀድሞ የሚደርስልኝ ሚካኤል ረዳቴ ነው።
.ከመንገዱ እንዳልወጣ ቃሉን የመገበኝ ሚካኤል መምህሬ ነው።
.ስደክም የሚያበረታኝ መልአኩ ደጋፊዬ ነው።
.ስራብ የሚመግበኝ ሚካኤል መጋቢዬ ነው።
.ስደናቀፍ የያዘኝ ደግሞም የደገፈኝ ሚካኤል ረዳቴ ነው።
.ቅ/ሚካኤል የችግሬ ደራሽ አማላጄ ያሳደገኝ አባቴ ነው። ለእኔ ያላደረገው ምን አለ?"""" ለእኔ ያደረገው እጅግ ብዙ ነው።""
. ዛሬም በችግሬ ቀድሞ ደርሷልና እኔም እንደ አባቶቼ.....

ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ። የሚል ዝማሬ ከአንደበቴ ነው።

ምልጃው አይለየን አሜን ለዘለዓለም።
ሐምሌ 12-2014
* * ናትናኤል **
49 viewsናትናኤል ጎሳ, 12:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 13:18:36 ሰላም የዚህ መንፈሳዊ ማዕድ ተካፋይ ወንድም እህቶቼ እንደምን ሰነበታችሁ ሰላመ እግዚአብሔር ለሁላችሁ ይብዛ ሰላም ለናንተ።

በዚህ ገጽ ላይ ስንካፈለው የነበረ መንፈሳዊ ማዕድ ለውሱን ግዜያት መቋረጡ እሙን ነው። በዚህም ብዙዎቻችሁ በስልክና በጽሁፍ መልእክት በአካልም ጭምር ለምን የሚል ጠያቂዎች ነበራችሁ።

ከዚህ ገጽ ብቻ ሳይሆን ከብዙ የአገልግሎት መድረኮች ለመከልከል የጽሞና የመገታት ግዜ እንድወስድ የምወዳቸው ወንድምና እህቶቼ ምክንያት ሆነውኛል። መንገድ ስተሀል ሰው እያሰናከልክ ነው አስተምሮህ ልክ አይደለም የሚሉ ማጉረምረሞች ነበሩ። አንዳንዶች የሃይማኖት ችግርም አለብህ የሚልማጉተምተም ስለነበረ በዚህ ገጽ ያሻኝን ለመጻፍ ቢቻለኝም ራሴን ከሌሎችም የአገልግሎት መስኮች ከልክዬ መቆየት ስላሻኝ ማዕዱ ተቋርጦ ኖሯል።

ይሁንና በወሰድኩት ጊዜ ምንም አይነት የስህተቴን ማመላከቻ የችግሬን አቅጣጫ ይህ ነው ሊለኝ ሊመክረኝና ሊያቀናኝ የወደደ ከብዙ ተቺዎቼ መሀል አንድም ስላጣው ትችቱ ቀጥሎ እኔም ወደ አገልግሎቴ ለመመለስ በተለይም በዚህ ገጽ ለብዙዎች ህመም የሆነውን እውነትን የበለጠ በመናገር ሀሰቱን በመተቸት ለመቀጠል እነሆኝ ብያለሁ።

ሌሎችንም በመጋበዝ ማዕዱን ለመካፈል ትጉ። እውነቱን ከሀሰት ለዩ። "ከፍሬአቸው ታውቋቸዋላችሁ"" እንደተባለ በወንጌል ሚዛን ሁሉን መዝኑ። እግሮቻችሁን ለንሰሀ አሩጡ። መንግስተ ሰማያት ቀርባለችና። ሀሰትን ተጸየፉ።
52 viewsናትናኤል ጎሳ, edited  10:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 19:56:56 ➼➼➼➼ ከጠላት የከፋ ጠላት➼➼➼➼

ይህ ቤት የፍቅር ቤት የሰላም ደጅ ነበረ። በጥዋትና ማታ ከቤተሰቡ መዋደድ የተነሳ ጎረቤት አይኑን የጣለበት አንዳንዱም በቅናት አይኑ የሚቀላበት ልቡ የሚነድበት ጠላት ከዚህ የተነሳ በዚህ ቤት ላይ የሸመቀበት የሁሉ አይን ማረፊያ ነበረ ይህ ቤት።

ዛሬ የትናንቱ ደስታ የቤተሰባዊ ፍቅር ቀዝቅዞ ቤቱን ሀዘን ውጦታል። ታሪክ የትናንት አይደለም ብረሀኑ ደብዝዟል። ነፍሰ ገዳይ ይወደሳል ሟች ይወቀሳል። አደባባዮች የሀፍረታችን መታያ ከሆኑ ሰንብተዋል እያለች በመብሰልሰል ከትናንቱ የፍቅር ቤት ታማ የምታቃስት ሊጠይቋት የመጡ ህመሟን የሚያባብሱባት ምስኪን እናት.....

ከሁሉ በላይ በታመመችው የትናንቷ ደገኛ እናት የዛሬዋም ታማሚ እመቤት ህመሟን የበለጠ የሚያከፉት ግን አምጣ ወልዳ ያሳደገቻቸው ልጆቿ ናቸው። ዛሬ የእናታቸውን ህመም መድኃኒት ሆኖ ከማከም ይልቅ ለእናታቸው ህመም ያንሳታል ይሉ ይመስል መድኃኒቱን ከማምጣት ይልቅ ዛሬም ካሉበት ሳይወጡ እየሰማች ህመሟን እንዳትረሳ የተጉ መስለው ስለህመሟ በማውራት ዛሬም ጊዜን ለስሜት ጊዜን ለትችት ጊዜን መስሎ ለማደር ሰጥተው ህመሟን ያከሙ እየመሰላቸው ህመሟን የሚያባብሱ ልጆች ያላት ይህች እናት ምን ያክል ታሳዝን?

እያመሟት ህመሟን ለማከም የሚሮጡ ዝንጉ ልጆችን የወለደች እናት እንባዋ ምን መሪር ይሆን? ያም ከሳሎን በሚደረገው ምክክር ጓዳውን ይነቅፋል። ሌላውም እየዋሸ የማያደረገውን ቃል ይገባል። ሌባውም እየሰረቃት ልጅ ነኝ በሚል ለውርስ ይደራደራል። አንዱም ያዘነ መስሎ የእናቱ ሞት አልደርስለት ብሎ ቀን ይቆጥራል። ብቻ ሁሉም በምክክሩ ጉድለትን መርዝን መድኃኒት አድርጎ ቃሉን አሳምሮ አንደበቱን አጣፍጦ ያወራል። ቀን አልፎ ቀን ተተክቷል። ሳምንታት ወራትን ወልደዋል። ዓመታት ተቆጥረዋል።

ማለዳውን ለማብሰር ጎህ ቀዷል ፀሐይ በወፎች ውብ ዝማሬ ታጅባ ቀኑን እንካቹ ስትል ቋሚ ተሰብሳቢ የምስኪን ታማሚ እናት ልጆቿ በሰአታቸው እናት ከጓዳ ተኝታ ከሳሎን ምምክክሩ ስብሰባ ውይይቱ እውነትን ክዶ ማውራቱ እንደተለመደው ቀጥሎ ፀሐይ መስማት ታክቷት ዛሬም ጠለቀች። የዛሬው ቀን ዛሬ አበቃ። ስብሰባው ምክክሩና ውይይቱ ነገ ፀሐይ ስትወጣ ይቀጥላል...............

""ተፈጸመ ዝንቱ መጽሐፍ""
56 viewsናትናኤል ጎሳ, edited  16:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 07:59:55 ከህይወት ገጽ ፭ ... "መስጠት...መቀበል!"


"መስጠትም ከመቀበል ነው፣ መቀበልም ከመስጠት ነው!"...

ያለንን መስጠት 'አገልግሎት' ነው።

ለካ ስንነጠቅ አብሮ እሚሰጠንም ነገር አለ!።

" አንድ ሰው አስር ክፍል ቤት ሠርቶ ብቻውን ሲኖር አንድ ቀን በሩ ተንኳኳ፤ ሲከፍት ጌታ ነው። "ውይ አምላኬ ጌታዬ አንተ እኔ ቤት መጣህ?" ብሎ በደስታ 'ተቀብሎት' አንድ ክፍል ቤት ሰጥቶት መኖር ጀመሩ። በሌላ ጊዜ በሩ ተንኳኳ፣ ሲከፍት ሰይጣን ነው፤ ይዘጋና ጌታዬ ሆይ አንተ እኔ ቤት እያለህ ሰይጣን የእኔን ቤት እንዴት ያንኳኳል? አለው። ጌታም "ቤቱ የአንተ እንጂ የእኔ አይደለም" አለው። ያሰውም አስቦ ሁለት ክፍል ቤት ለጌታ ጨምሮለት እርሱ ሰባት ክፍል ይዞ መኖር ቀጠሉ። በሩ ተንኳኳ ሲከፍት ሰይጣን ነው። ተበሳጭቶ ይዘጋና "ጌታዬ ሆይ አንተ እኔ ቤት እያለህ ሰይጣን የእኔን ቤት እንዴት ያንኳኳል?" አለው። ጌታም ቤቱ የአንተ እንጂ የእኔ አይደለም አለው። ያሰውም ተሰምቶት ከጌታ ጋር እኩል ለእኩል ተካፈለ፤ ነገር ግን ቤቱ ከቀድሞ ይልቅ ተንኳኳ። አዝኖም ይዘጋና ጌታ ሆይ..?! አለው። ጌታም የቀድሞውን መልስ ሰጠው። በዚህ ጊዜ ይህሰው ለራሱ አንድ ክፍል ቤት ይዞ ዘጠኙን ክፍል ቤት ለጌታ ሰጠው፤ ነገር ግን ከቀድሞው ይልቅ እጅግ በጣም ተንኳኳ። ቢከፈት ሰይጣን ነው። በሩን ይዘጋና ወደ ጌታ ሄዶ "ጌታ ሆይ ምስጢሩ ምንድነው?" አለው። "ጌታ ግን ቤቱ የአንተ እንጂ የእኔ አይደለም"አለው። በዚህ ጊዜ አስሩንም ክፍል ለጌታ አስረከበ። ጌታም መልሶ 'ሰጠው' እና መኖር ጀመሩ። በሩም ተንኳኳ፤ ጌታም ሊከፍት ተነሳ። ሲከፍት ሰይጣን ነው። ሰይጣንም "ይቅርታ የአንተ ቤት መሆኑን አላወቅሁም!" ብሎ ሄደ። ከዚያን ቀን ጀምሮ መንኳኳት አቆመ።
"ሁሉንም የህይወታችንን ክፍል ለጌታ እግዚአብሔር ካላስረከብነው መንኳኳት አይቆምም!።" 10% ስንሰጥ ይንኳኳል። 30% ስንሰጥም ይንኳኳል። 50% ስንሰጥ ይበልጥ ይንኳኳል። 99% ስንሰጥ እጅጉን ይንኳኳል። 100% ስንሰጥ መንኳኳት ያቆማል። እኛ ከከፈትን ሰይጣን ይገዳደረናል፤ ጌታ ሲከፍት ግን "ይቅርታ ቤቱ ያንተ መሆኑን አላወቅሁም" ብሎ ይሄዳል።
እግዚአብሔር ሰማይን የደስታ አገር ያደረጋት ሙሉ በሙሉ ፈቃዱ የጸናባት በመሆኗ ነው። በእኛም ህይወት የእግዚአብሔር ሰላምና ደስታ የሚመጣው በህይወታችን ሙሉ በሙሉ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ስንፈጽም ነው። ስለዚህ:- "እግዚአብሔርን እረኛችን እናድርገው!....በፍፁም ልባችን እንከተለው!...የሚያስፈልጉንም ነገሮች እኛን ይከተሉናል!።" ሙሉ ህይወታችንን ለእግዚአብሔር እንስጥ፤ ህይወትን እንቀበላለን።

አንተን ያላንተ ቸርነት ማን መቀበል ይቻለዋል?!....

የሚጠሉትን መስጠት አይከብድም፤ የሚወዱትን መስጠት ግን ፍቅር ነው።

መስጠት መሰጠትንም ጭምር ያካትታል...ይኽም ማለት እራስን አሳልፎ መስጠት ነው።

"ስጡ ይሰጣችሁማል፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ተመልሶ ይሰፈርላችኋልና!..............።"
(ሉቃስ 6:38-45)
በተለያየ መልኩ ከተማርኩት
አንቆጳጊዮን
159 viewsናትናኤል ጎሳ, 04:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 21:39:15
58 viewsናትናኤል ጎሳ, 18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 19:50:37

564 viewsሰይፈ ሚካኤል, 16:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 05:59:52 ቤተክርስቲያንን በሁለት መንገድ ማወቅህን አረጋግጥ። እንደ አሕዛብ ጠላቷ እንዳትሆን #በትምህርት_ዕወቃት፤ እንደ ፈሪሳውያን እንዳትሆን #በኑሮ_ዕወቃት። ለሥርዓቷ ታማኝ ሁን፥ አንተ ወደ ሥርዓቷ እደግ እንጅ ሥርዓቷ ወደ አንተ ፈቃድ እንዲወርድልህ አትውደድ፤ ሰማያውይቷን ቤተክርሰቲያን ምድራዊት እንድትሆንልህ አትፍቀድ።

በቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አንድነቶች ካልተሳተፍክ ከቤተክርስቲያን አንድነት እየተለየህ እንደሆነ እወቅ። እሊህም፦ ኪዳን ማስደረስ፥ ማስቀደስና ንስሐ ገብቶ መቁረብ፥ በምህላ ጸሎቶቿ በአዋጅ አጽዋማቷ መተባበር ናቸው።

ከቤት ከሚጸለይ አሥር ጸሎት ይልቅ በቤተክርስታያን የሚደረግ አንድ ጸሎት እንደሚበልጥ አውቀህ በየቀኑ ወደ እርስዋ ገሥግሥ። በሕይወትህ ሁሉ ቤተክርስቲያናዊ ሁን!

ርዕሰ_ሊቃውንት_አባ_ገብረ_ኪዳን
91 viewsሰይፈ ሚካኤል, 02:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 21:26:27

652 viewsሰይፈ ሚካኤል, 18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 15:28:47 «ለመተኛት ወደ አልጋህ ባመራህ በቀረብህ ጊዜ አልጋዬ፡ ምን አልባት በዚህ ሌሊት ለእኔ መቃብሬ ልትኾኚ ይኾን ይኾናል፤ በጊዜአዊው ዕንቅልፍ ፈንታ በዚህ ሌሊት ያኛው እንቅልፍ (ሞት) ይመጣብኝም እንደ ኾነ አላውቀውም በላት ።ስለዚህ ነጻ እግሮች እያሉህ ከመልካም ሥራ በኋላ ሩጥ፤ ከታሠሩ መፈታት በማይችሉበት ማሰሪያ ከመታሠራቸው በፊት፡፡ የእጆችህ ጣቶችም እስካሉህ ድረስ ሞት ከመምጣቱ በፊት በጸሎት ፊትህንና መላ ሰውነትህን በተእምርተ መስቀል አማትብ፡፡ ዐይኖች እስካሉህ ድረስ በአቧራ ከመሽፈናቸው በፊት በእንብዕ(በእንባ) ምላቸው።ሰው ሆይ ከዚህ ዓለም መለየትህን አስብ፣ እንዲህም በል፡- እነሆ የታዘዘ መልአክ ከበር ቆሞአል (ደርሶአል)፣ እኔንም ይከተለኛል። ለምን ሊል ዘሊል እኾናለሁ? መመለሻ የሌለው ዘለዓለማዊ መንገድ አለ፡፡መለኮት ደግነት የተነሣ የሰውን ልብ የሚገዛውና ነፍስን ወደ ሕይወት የሚመራት የመጀመሪያው ትምህርት ተዘክሮተ ሞት ነው።.ተዘክሮተ ሞት በሰይጣን እጅግ በብዙ ይጠላል፡፡ እርሱም ከሰው ተዘክሮን ለመንቀል በሙሉ ኃይሉ መሞከርን አይተዉም፡፡ የሚቻለውስ ቢኾን በምድራዊ ሕይወት አሳብ ተብትቦ ተዘክሮተ ሞትን ከሰው ልብ (አእምሮ) ለማስወገድ ምድራዊ መንግሥታትን ለሰው በሰጠው ነበር፡፡ አታላዩ ሰይጣን ተዘክሮተ ሞት በሰው ሁልጊዜም ካለ፣ አሳቡ ለአሁኑ ሕይወት መታለሎች የተጣበቀ ኾኖ እንደማይቀር አልያም የሰይጣን ማታለሎች ሰውን ሊቀርቡት እንደማይችሉ ያውቃል፡፡"

ማር_ይስሐቅ_ሶርያዊ
82 viewsሰይፈ ሚካኤል, 12:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 09:26:36 ዝም እንድል አድርገኝ

በዚህ ኡኡታ ዓለም ምልልስ በበዛው
ይሰቀል በሚል ድምጽ ሁከት በከበበው
የአይሁድ መንደር ውስጥ ቀን ላስገኘኝ ለኔ
ዝም እንድል አድርገኝ እንዳይጨልም ቀኔ።

አውቃለሁ አምላኬ ቸሩ ንጉስ ጌታ
ከግርግርታው ማየል ካለው ከጫጫታ
የዝምታ ጩኸት እንዲበልጥ ዝምታ
ግና
ነፉስ ለምከተል ጉምን ለተደገፍኩ
ከሚጮሁት ስጮህ ቀናቶቼን ለጣልኩ
በዝምታ ጩኸት እንድጮኽ አድርገኝ
መናገርን ልጣል ዝምታን እንዳገኝ።

እውነትን ለብሰዋት ካሸበረቁቱ
ደምረኝ ከነርሱ ንጉስ ሆይ አቤቱ።
ሀሰትን ለብሰዋት አንተን ከረሱቱ
ጠብቀኝ ከነዚያ ሸንጋዮች አቤቱ።

መቃብርን ምሶ እውነትን ለመቅበር
ሰው ሆ ብሎ ወቷል ለመጣላት ከግዜር
ነጭ ይላል ጥቁሩን አይኔን ግንባር ያርገው
አይኑ ግንባር ሆኖ ጭራሽ እንዳያየው

እኔ ግን ተጥዬ ብቻዬን ምን ብቀር
እውነትን አልልቀቅ ከርሷ ጋር ልቀበር
ከሀሰት መንደር ልራቅ ከሸንጋዮች ጎራ
ዝም እንድል ከእውነት ጋር ልኑር ከርሷ ጋራ

እኔው ተናግሬ ሰሚ እኔው ከሆንኩኝ
ሌላውን አልረብሽ ዝም እንድል አድርገኝ።
387 viewsሰይፈ ሚካኤል, 06:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ