Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም የዚህ መንፈሳዊ ማዕድ ተካፋይ ወንድም እህቶቼ እንደምን ሰነበታችሁ ሰላመ እግዚአብሔር ለሁላች | ኬልቅያስ

ሰላም የዚህ መንፈሳዊ ማዕድ ተካፋይ ወንድም እህቶቼ እንደምን ሰነበታችሁ ሰላመ እግዚአብሔር ለሁላችሁ ይብዛ ሰላም ለናንተ።

በዚህ ገጽ ላይ ስንካፈለው የነበረ መንፈሳዊ ማዕድ ለውሱን ግዜያት መቋረጡ እሙን ነው። በዚህም ብዙዎቻችሁ በስልክና በጽሁፍ መልእክት በአካልም ጭምር ለምን የሚል ጠያቂዎች ነበራችሁ።

ከዚህ ገጽ ብቻ ሳይሆን ከብዙ የአገልግሎት መድረኮች ለመከልከል የጽሞና የመገታት ግዜ እንድወስድ የምወዳቸው ወንድምና እህቶቼ ምክንያት ሆነውኛል። መንገድ ስተሀል ሰው እያሰናከልክ ነው አስተምሮህ ልክ አይደለም የሚሉ ማጉረምረሞች ነበሩ። አንዳንዶች የሃይማኖት ችግርም አለብህ የሚልማጉተምተም ስለነበረ በዚህ ገጽ ያሻኝን ለመጻፍ ቢቻለኝም ራሴን ከሌሎችም የአገልግሎት መስኮች ከልክዬ መቆየት ስላሻኝ ማዕዱ ተቋርጦ ኖሯል።

ይሁንና በወሰድኩት ጊዜ ምንም አይነት የስህተቴን ማመላከቻ የችግሬን አቅጣጫ ይህ ነው ሊለኝ ሊመክረኝና ሊያቀናኝ የወደደ ከብዙ ተቺዎቼ መሀል አንድም ስላጣው ትችቱ ቀጥሎ እኔም ወደ አገልግሎቴ ለመመለስ በተለይም በዚህ ገጽ ለብዙዎች ህመም የሆነውን እውነትን የበለጠ በመናገር ሀሰቱን በመተቸት ለመቀጠል እነሆኝ ብያለሁ።

ሌሎችንም በመጋበዝ ማዕዱን ለመካፈል ትጉ። እውነቱን ከሀሰት ለዩ። "ከፍሬአቸው ታውቋቸዋላችሁ"" እንደተባለ በወንጌል ሚዛን ሁሉን መዝኑ። እግሮቻችሁን ለንሰሀ አሩጡ። መንግስተ ሰማያት ቀርባለችና። ሀሰትን ተጸየፉ።