Get Mystery Box with random crypto!

Jesus' ministry

የቴሌግራም ቻናል አርማ jesusministry — Jesus' ministry J
የቴሌግራም ቻናል አርማ jesusministry — Jesus' ministry
የሰርጥ አድራሻ: @jesusministry
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 781
የሰርጥ መግለጫ

This is Jesus' ministry official channel served by Abrham Yilma(@Abrhameee). Daily bible teachings and revelations will be updated on this channel.

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-05-30 19:12:33 https://vm.tiktok.com/ZMN1ARPrx/?k=1
363 viewsAbrham, 16:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 19:45:16 ሰላም ቅዱሳን አብርሃም ነኝ።ከዚህ በፊት ብዙ ትምህርቶችን በፅሁፍ በዚህ ቻናል እለቅላችሁ ነበር።አሁን ደግሞ tiktok ላይ ስላለሁና አጫጭር ትምህርታዊ ቪዲዮዎችን መልቀቅ ስለጀመርኩ በዚህ ስለቃቸው የነበሩትን አይነት ትምህርቶች tiktok ላይ ታገኙታላልችሁ።tiktok ላይ @abrishyilma ብላችሁ search ስታደርጉት እና follow ስታደርጉኝ ታገኙኛላችሁ ተባረኩ።
376 viewsAbrham, 16:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-25 12:48:05 https://vm.tiktok.com/ZMLEdpnLP/?k=1
366 viewsAbrham, 09:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 10:50:27 የወሲብ ፊልሞችን(pornography) የመመልከት ጉዳት

ፖርኖግራፊ ሁሉም አማኝ እንደሚረዳው በጣም ጎጂ ነገር ነው።ግን ብዙ ወጣት አማኞች የጉዳቱን ልክ የተረዱት አይመስልም።
የወሲብ ቪዲዮ እያየን በመጣን ቁጥር ወደ ሱስ ይቀየርበታል።በሱስ የምትጠመደው ደግሞ ነፍሱ ናት።ነፍስ ህይወት ናት።የእውቀት የስሜት የፈቃድ ምንጭ ነው።ሰው በሱስ ሲጠመድ ነፍሱ በሱስ ተጠመዶአል ማለት ነው።በሱስ ከተያዘ በኃላ አለማድረግ የሚፈልገውን ነገር አለማድረግ አይችልም ማለት ነው።የሚያደርገው ልምምድ ወደ ሱስነት ስለተቀየረ ከዚያ በኃላ አለማድረግ አይችልም።ፈቃዱ ሀይል አይኖረውም በሱሱ ሀይል ስር ይወድቃል።ነፍስ ህይወት ስለሆነች ህይወቱን እያጣ ይሄዳል።

ብዙ የፖርኖግራፊ ፊዲዮዎች እና ምስሎች አጋንንታዊ ኪዳን አላቸው።እነዚህ አጋንንት ቪዲዮውን ከፍተው ወደሚያዩት ሰዎች ይገባሉ።ጥቂት የማይባሉ ሰዎችና አማኞች አጋንንትን ወደህይወታቸው የሳቡት በፖርኖግራፊ ነው።በዚህ መንገድ አጋንንት የገባባቸው ብዙ አሉ።ፖርኖግራፊ አጋንንት ሰዎችን የሚያጠቁበት አንድ መሳሪያ ነው።ጥሩ የፍቅር ህይወት እና ትዳር የነበራቸው ሰዎች ከፖርኖግራፊ በኃላ ትዳራቸው ችግር ላይ ወድቆአል ብዙ ፍቅረኛሞችም ተለያይተዋል።ነገሩ በድንገት ምኑ ጋር እንደተበላሸ ላይገባቸው ይችላል።ግን ነገራቸውን ያበላሸው መንፈስ ነው።መንፈሱንም የተዋረሱት የፖርኖግራዊ ፊልም ከፍተው ሲመለከቱ ነው።
ስለዚህ እንደዚህ አይነት ቪዲዮ ከፍተን ከማየታችን በፊት ልንጠነቀቅ ይገባል።

ሌላው ከባድ የፖርን ጉዳት አንዲት በጣም አጭር ለሰከንድ የተመለከትናት የብልግና ፊልም በፍጥነት አእምሮአችን ላይ ይቀመጣል።ከአእምሮአችንም ለረጅም ጊዜ አይጠፋም።የወሲብ ፊልም እጅም በጣም በፍጥነት ወደ አእምሮአችን ውስጥ ምስሉ የመግባት አቅም አለው።ከዚያ በኃላም በተሎ የማይረሳ ነው።
እና ይህ በአእምሮ ላይ የተቀመጠው ምስል ወደአእምሮአችን እየደጋገመ እየመጣ ይረብሸናል።አማኝ ከሆንን ሀሳባችንን በማቆሸሽ ያረክሰናል።
በግንኙነት ጊዜም ምስሉ ወደ አእምሮአችን እየመጣ ጤናማ ግንኙነት ከትዳር አጋራችን ጋር እንዳይኖረን ያደርገናል።ለተሻለ ግንኙነት ብለን የወሲብ ቪዲዮ ከፍተን ጭራሽ ጤናማ የነበረን ግንኙነታችንን እናጣለን።ጤናማ አእምሮ የነበረን ምንም ግንኙነት አድርገን የማናውቅ ልጆችም ለማወቅ ብለን የወሲብ ቪዲዮ በመመልከት የተሳሳተን እይታ፣ልምምድ እናተርፋለን ይህም ጠባሳ ይጥልብን እና ለሚኖረን የትዳር ህይወት እንቅፋት ይሆንብናል።
ጌታ ኢየሱስ ግን ከየትኛውም እስራትና ቀንበር ይፈታል።

ይቀጥላል

https://t.me/jesusministry
https://t.me/jesusministry
454 viewsAbrham, 07:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 22:01:25 አንዳንዴ ሁሉም ነገር ካሰብነው በተቃራኒ ሲሄድ ልንማረር ተስፋ ወደ መቁረጥ ስሜት ውስጥም ልንገባ እንችላለን።በእግዚአብሄር እየተተውን እንዳለንም ሊሰማን ይችላል።
ቁጭ ብለን ስናስበው እግዚአብሔር ካሰበልን ጋር የማንደርስ የምንጠብቀውም የማይሆን ሊመስለን ይችላል።ሁሉም ተቃራኒ የሚመስልበት ጊዜ አለ።

ዮሴፍ መሪ እንደሚሆን ህልምን ካለመ በኃላ ወደ እስር ቤት ወዲያው መርዷል።መጀመሪያ በህልሙ በኃላ ክብርን እንጂ እስር ቤትን አይጠብቅም ነበር።ተሎም እፈታለው ብሎ አስቦ ሊሆን ይችላል።ግን ብዙ አመታንን በእስር ቆይቶ ነበር።(አንዳንዶች እንደሚሉት ዮሴፍ በ17 አመቱ ታስሮ በ30 አመቱ ተፈቶአል።)
በእነዚህ ሁሉ የጨለማ ጊዜያትን ዮሴፍ መጠበቅ ግድ ብሎት ነበር።በመሀከልም ዮሴፍ በቃ ታስሬ ልቀር ነው በሚል ስሜት የገባ ይመስላል።ምክንያቱም ከታሳሪዎች አንዱን ስትወጣ አስበኝ ብሎታል።ግን የእግዚአብሔር ጊዜ አልነበረምና ይህ ሰው እረሳው።
ታሪክ የሰራው የመፍትሄ ሰው ዮሴፍ እስከ 30 አካባቢ እድሜው እስር ቤት ነበር።ከዚያ ወጥቶ ግን ሀገር መርቶአል።ታዲያ እኛ በወጣትነታችን ለምን ተስፋ እንቆርጣለን?እግዚአብሔር ወደ ፍፃሜያችን እንደሚያደርሰን አምነን አንከተለውም?

https://t.me/jesusministry
https://t.me/jesusministry
520 viewsAbrham, 19:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-15 23:05:46 ንፁህ አምልኮ
እውነተኛ አምልኮ
ከልብ የሚፈልቅ አምልኮ
ቅድስና ያለበት አምልኮ
ፍቅር የተሞላበት አምልኮ
ማስተዋል የተሞላበት አምልኮ

ሁኔታን ያላመከለ አምልኮ
ትዕቢት የሌለበት አምልኮ
ቅናት የሌለበት አምልኮ
ግብዝነት የሌለው አምልኮ

ይህ አምልኮ በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስ የሚያገኝ እና የእግዚአብሔር ክብር በሀይል የሚገለጥበት አምልኮ ነዉ


@jesusministry
@jesusministry
@jesusministry
526 views𝑁𝑎𝑟𝑑𝑖, 20:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-11 10:23:57 አንድ ክርስቲያን አደገ የሚባለው በመንፈስ ቅዱስ መመላለስ ሲጀምር ነው።

እግዚአብሔር ወደ ክርስትና ህይወት ሲያመጣን እኛ እንድንኖር ሳይሆን ልጁ ክርስቶስ ኢየሱስ በእኛ እንዲኖር ነው።

እግዚአብሔር አባትን ማየት የሚቻለው በልጁ በኢየሱስ ክርሰቶስ በኩል እንደሆነ ሁሉ እንደዚሁም ክርስቶስን ማየት የሚቻለው መገለጡ በሆነችው በቤተክርስቲያኑ (በቅዱሳን ሁሉ ) በኩል ነው።

በመንፈስ መኖር ማለት በመንፈስ ቅዱስ ቁጥጥር በመሆን እኛ በራሳችን ማድረግ የማንችለውን መንፈስ ቅዱስ በእኛ ማድረግ እንዲችል መታመን ወይንም ደግሞ ጌታ አንድ ነገር እንድናደርግ በጠየቀን ጊዜ እርሱ የሚፈልገውን በእኛ ሆኖ እንዲያደርግ ወደ እርሱ መመልከት እና እርሱን ተስፋ ማድረግ ማለት ነው።

መንፈሳዊ ድልን የምንቀዳጀው በየእለቱ ራሳችንን ለመለወጥ በምናደርገው ቁርጠኛ ውሳኔ ሳይሆን ራሳችንን ለመንፈስ ቅዱስ ሃሳብ ስናስገዛ ብቻ ነው።

እግዚአብሔር በእኛ ሕይወት ማየት የሚፈልገውን ፍሬ ለማፍራት መንገዱ ሃይማኖታዊ እና ሰዋዊ ጥበብን መጠቀም ሳይሆን በመንፈስ መኖር ብቻ ነው።

በእምነት የእግዚአብሔር ፀጋ እኛነታችንን እንዲወርስ እያስረከብን ስንመጣ መንፈስ ቅዱስ እኛን በኃጥያት ላይ ድል ነሺዎች እና የአምላክ(የክርስቶስ) ሕይወት መገለጫዎች ያደርገናል።

መንፈስ ቅዱስ እኛን በድል ሕይወት ለማኖር የሰብዓዊ ኃይል ጥረት እና እርዳታ አያስፈልገውም ጌታ ኢየሱስ የድሉ ባለቤት እና ምንጭ ነው።

"፤ ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው።"
(ወደ ገላትያ ሰዎች 2: 20)

@Excellent_youth
@Excellent_youth
533 viewsAbrham, 07:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-29 23:27:08
543 views𝑁𝑎𝑟𝑑𝑖, 20:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-29 23:14:15 Eccl 3 (AMP)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ He has made everything beautiful in its time. He also has planted eternity in men's hearts and minds , yet so that men cannot find out what God has done from the beginning to the end.
¹² I know that there is nothing better for them than to be glad and to get and do good as long as they live;
¹³ And also that every man should eat and drink and enjoy the good of all his labor--it is the gift of God.
465 views𝑁𝑎𝑟𝑑𝑖, 20:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-16 18:17:24 ብዙ ጊዜ የምንስተው በዚህ ነው:-አንድን አማኝ የምንለካው ባገኘው ነገር እንጂ በከፈለው ነገር አይደለም።ነገር ግን የአንድ አማኝ ስኬት ስለክርስትና ህይወቱ በከፈለው ዋጋ እንጂ ባገኘው ነገር አይለካም አይመዘንም።
አንድን አማኝ ሀብት እያካበት ስላየነው፣ስራው ስለሰመረለት፣በሌላም አቅጣጫ ቢሆን የሆነ ነገር ስለተጨመረለት እና ሲጨመርለት በክርስትናው አደገ ወይም ለእግዚአብሔር ቅርብ ነው እንላለን።ይህ አመለካከት ግን ፈፅሞ ከእውነተኛ መፅሀፍ ቅዱሳዊ አስተምሮ ያፈነገጠ ነው።በምድር የሚጨመርልን ነገር ሁሉ ፈፅሞ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን እውነተኛ ህብረትና መታዘዝ አያመለክትም።
እንደፈቃዱ እየኖሩ በምድራዊ አተያይ ምንም ያልተጨመራቸው የሚመስሉ በሰማይ ግን ታላቅ አክሊል የሚጠብቃቸው አማኞችና አገልጋዮች አሉ።በምድር በተሟላ ኑሮዋቸው በእግዚአብሔር የተከበሩ የሚመስሉ በእግዚአብሔር ግን የታዘነባቸው አማኞች እና አገልጋዮች በሌላ መንገድ አሉ።
በምድር ላይ የሆነ ነገር ሲጨመርልን እግዚአብሔር ይበልጥ እንደቀረበን የሚሰማን ስንሆን:የሆነ ነገር ሲጎለን ደግሞ እግዚአብሔር የራቀን የተወን ሲመስለን ስተናል።የእግዚአብሄርንም ቃል እንደማናጠና ትልቅ ምልክት ነው።
ኑሮዋቸው እየሞላላቸው ያሰቡትም እየተሳካላቸው ያሉትን ክርስቲያኖች አይተን ለክርስቶስ ምን ያክል እንደተቆረሱና እንደከፈሉ ሳናይ እንቀናባቸዋለን።በህይወታቸው ከፍለውና ተቆርሰው የሚኖሩ አማኞችና አገልጋዮችን ደግሞ ደማቅ ኑሮ እየኖሩ ስላልሆኑና፣ብዙ የሚከተላቸው ስለሌለ፣ሀብትም ስለሌላቸው አንቀናባቸውም።

አንድ አማኝ ግን በእግዚአብሔር ፊት ሲመዘን በተቆረሰበት ነገር በሰጠው ነገር በከፈለው ዋጋ ከእግዚአብሔር ጋር ባለው ህብረት ይመዘናል እንጂ በተቀበለውና በተጨመረለት ነገር አይመዘንም።

እኛም ትምህርት እንዲሆንልን እና መመለስ እንዲሆንልን ትኩረታችን ስለጌታ ነገር ዋጋ እየከፈለ ባለውና በከፈለው ላይ ይሁን።ህይወታቸው ምሳሌ ይሆንልናልና።
የህይወታችንም ዋጋ በእግዚአብሔር ፊት እየጨመረች የምትመጣው ተሳክቶላት፣ፀሎቷ ተሰምቶ ያሰበችው ሲሳካ፣ኑሮዋ ሲሻሻል ሳይሆን በየጊዜው ለጌታ ህይወቷን ስትተው፣ለእግዚአብሔር ፈቃድ ስትቆረስ፣ በህይወት ስትከፍል ነው።

https://t.me/jesusministry
https://t.me/jesusministry
3.0K viewsAbrham, edited  15:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ