Get Mystery Box with random crypto!

የወሲብ ፊልሞችን(pornography) የመመልከት ጉዳት ፖርኖግራፊ ሁሉም አማኝ እንደሚረዳው በጣ | Jesus' ministry

የወሲብ ፊልሞችን(pornography) የመመልከት ጉዳት

ፖርኖግራፊ ሁሉም አማኝ እንደሚረዳው በጣም ጎጂ ነገር ነው።ግን ብዙ ወጣት አማኞች የጉዳቱን ልክ የተረዱት አይመስልም።
የወሲብ ቪዲዮ እያየን በመጣን ቁጥር ወደ ሱስ ይቀየርበታል።በሱስ የምትጠመደው ደግሞ ነፍሱ ናት።ነፍስ ህይወት ናት።የእውቀት የስሜት የፈቃድ ምንጭ ነው።ሰው በሱስ ሲጠመድ ነፍሱ በሱስ ተጠመዶአል ማለት ነው።በሱስ ከተያዘ በኃላ አለማድረግ የሚፈልገውን ነገር አለማድረግ አይችልም ማለት ነው።የሚያደርገው ልምምድ ወደ ሱስነት ስለተቀየረ ከዚያ በኃላ አለማድረግ አይችልም።ፈቃዱ ሀይል አይኖረውም በሱሱ ሀይል ስር ይወድቃል።ነፍስ ህይወት ስለሆነች ህይወቱን እያጣ ይሄዳል።

ብዙ የፖርኖግራፊ ፊዲዮዎች እና ምስሎች አጋንንታዊ ኪዳን አላቸው።እነዚህ አጋንንት ቪዲዮውን ከፍተው ወደሚያዩት ሰዎች ይገባሉ።ጥቂት የማይባሉ ሰዎችና አማኞች አጋንንትን ወደህይወታቸው የሳቡት በፖርኖግራፊ ነው።በዚህ መንገድ አጋንንት የገባባቸው ብዙ አሉ።ፖርኖግራፊ አጋንንት ሰዎችን የሚያጠቁበት አንድ መሳሪያ ነው።ጥሩ የፍቅር ህይወት እና ትዳር የነበራቸው ሰዎች ከፖርኖግራፊ በኃላ ትዳራቸው ችግር ላይ ወድቆአል ብዙ ፍቅረኛሞችም ተለያይተዋል።ነገሩ በድንገት ምኑ ጋር እንደተበላሸ ላይገባቸው ይችላል።ግን ነገራቸውን ያበላሸው መንፈስ ነው።መንፈሱንም የተዋረሱት የፖርኖግራዊ ፊልም ከፍተው ሲመለከቱ ነው።
ስለዚህ እንደዚህ አይነት ቪዲዮ ከፍተን ከማየታችን በፊት ልንጠነቀቅ ይገባል።

ሌላው ከባድ የፖርን ጉዳት አንዲት በጣም አጭር ለሰከንድ የተመለከትናት የብልግና ፊልም በፍጥነት አእምሮአችን ላይ ይቀመጣል።ከአእምሮአችንም ለረጅም ጊዜ አይጠፋም።የወሲብ ፊልም እጅም በጣም በፍጥነት ወደ አእምሮአችን ውስጥ ምስሉ የመግባት አቅም አለው።ከዚያ በኃላም በተሎ የማይረሳ ነው።
እና ይህ በአእምሮ ላይ የተቀመጠው ምስል ወደአእምሮአችን እየደጋገመ እየመጣ ይረብሸናል።አማኝ ከሆንን ሀሳባችንን በማቆሸሽ ያረክሰናል።
በግንኙነት ጊዜም ምስሉ ወደ አእምሮአችን እየመጣ ጤናማ ግንኙነት ከትዳር አጋራችን ጋር እንዳይኖረን ያደርገናል።ለተሻለ ግንኙነት ብለን የወሲብ ቪዲዮ ከፍተን ጭራሽ ጤናማ የነበረን ግንኙነታችንን እናጣለን።ጤናማ አእምሮ የነበረን ምንም ግንኙነት አድርገን የማናውቅ ልጆችም ለማወቅ ብለን የወሲብ ቪዲዮ በመመልከት የተሳሳተን እይታ፣ልምምድ እናተርፋለን ይህም ጠባሳ ይጥልብን እና ለሚኖረን የትዳር ህይወት እንቅፋት ይሆንብናል።
ጌታ ኢየሱስ ግን ከየትኛውም እስራትና ቀንበር ይፈታል።

ይቀጥላል

https://t.me/jesusministry
https://t.me/jesusministry