Get Mystery Box with random crypto!

Jesus' ministry

የቴሌግራም ቻናል አርማ jesusministry — Jesus' ministry J
የቴሌግራም ቻናል አርማ jesusministry — Jesus' ministry
የሰርጥ አድራሻ: @jesusministry
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 781
የሰርጥ መግለጫ

This is Jesus' ministry official channel served by Abrham Yilma(@Abrhameee). Daily bible teachings and revelations will be updated on this channel.

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-03-08 17:58:54 በመገኘትህ
ቦኒ አብርሃም

[New Ethiopian Gospel Song]
Boni Abraham


@jesusministry
514 views𝑁𝑎𝑟𝑑𝑖, 14:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-11 12:41:53 °አንዳንድ ፀሎቶች በከፍተኛ ውጊያ ብቻ ይለቀቃሉ°

የፀሎት መልሶቻችን የሚዘገይበት ምክንያት ብዙዎቹን እግዚአብሔር አዘግይቶአቸው ሳይሆን(ለትክክለኛ ጊዜ የሚያዘገያቸው እንዳሉ ሆኖ) በጠላት በጨለማው ሀይላት ስለሚዘገዩ ነው።

በትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ 10 እንደምናነበው የዳንኤልን የፀሎት መልስ ይዞ የመጣው መልአክ በአየር ላይ የፋርስና ሜዶን አለቃ መንፈስ ስለተቋቋመው ለ21 ቀን አዘገየው።ዳንኤል መልሱ የተመለሰለት ገና በመጀመሪያው ቀን ቢሆንም መልሱ ግን ለ 21 ቀን ዘገየበት።ዳንኤል መፀለዩን ስላላቌረጠ ሚካኤል በውጊያ ላይ የነበረውን መልአክ ለመርዳት ወረደ።

ልብ ልንል የሚገባው ነገር መንፈሳዊዊ አለም ከምናስበው በላይ ሰፊ፣ሀይል ያለውና በውጊያ የተሞላ ነው።ገብቶንም ይሁን ሳይገባን በእግዚአብሔር ቃል ሙላት፣በኢየሱስ ደም፣በኢየሱስ ስም ሀይልና ስልጣን፣በእሳት በየቀኑ እንዋጋለን።ዘወትር በፀለይንም ቁጥር መላእክት ስለእኛ ይዋጋሉ።በመንፈሳዊው አለም እየተሸነፈ ያለ አማኝ በዚህ በሚታየው አለም የተሸነፈና የታሰረ ህይወት ይኖረዋል።በመንፈሳዊው አለም እያሸነፈ ያለ አማኝ በሚታየው በዚህ ኑሮው አሸናፊ ነው።የሚታየው በማይታየው ይመራል።በማይታየው የታሰረ ሁሉ በሚታየው የታሰረ ነው።አሁን ያለን ኑሮአችንና አካሄዳችን በማይታየው መንፈሳዊ አለም ያለንን ቦታ ያንፀባርቃል።ዛሬ በኑሮአችን የዘገየ የታሰረ ነገር ቢኖር ለዚህ እስራት ተጠያቂ አካል በመንፈሳዊዊ አለም ነገራችንን ያዘገየ አካል አለ።ውጊያችንም ከዚህ አካል ጋር ነው።ዳንኤል መልስ እስኪመጣለት መፀለዩን አላቁዋረጠም።አለማቋረጡም ሚካኤል ለውጊያ እንዲነሳ ሀይል(ምክንያት) ሆኖታል።

ምንጊዜም መፀለያችንን ስናቋርጥ በውጊያ እያስነጠቅናቸው የነበርነውን አንዳንድን ነገሮች መልሰን በጠላት እናስይዛለን።እንዳንዋጋ እንዳንገስፅ ተስፋን እንድንቆርጥ የተስፋ መቁረጥ መንገስና የአዚም እና የድንዛዜ መንፈስ ከጨለማው አለም ይረጭብናል።ስለዚህም መፅሀፍ ቅዱስ በብዙ ቦታ ፀልዩ ብሎ አይተወንም ይልቁኑም ትጉና ፀልዩ ይለናል።

በመንፈስና በትጋት የሆኑ ፀሎቶች የፀሎት መልስን ያመጣሉ።2ኛ ቆሮንቶስ 10:4 ላይ 'ደግሞም የምንዋጋበት የጦር መሳሪያ የዚህ አለም መሳሪያ አይደለም:ይሁን እንጂ ምሽግን ለመደምሰስ የሚችል መለኮታዊ ኅይል ያለው ነው።'ይላል።አዎ!ምሽግን መደምሰስ የሚችል ሀይል በእጃችን አለ።የጠላት የአጋንንት ምሽግ ሳይደመሰስ ነገራችንን መናጠቅ አንችልም።አንዳንድ ፀሎቶች በመፀለይ ብቻ ሳይሆን በከፍተኛ የውጊያና የልመና ፀሎት ይመለሳሉ።በቅድስና መመላለስ መፆም በኢየሱስ ስምም መገሰፅ ማፍረስ መጋፈጥና መጮህ ይጠይቃል።ያኔ ስለእኛ የሚዋጉ መላእክት በአየር ላይ ፀሎታችንን የሚይዘውን አለቃ መንፈስ ይቀጠቅጡታል።በኢየሱስ ስም ባዘዝን ቁጥር የአየር ላይ አጋንንትን እሳት ይበላል ያኔ የፀሎት መልሳችን ጥሶ በማለፍ ወደኛ ይመጣል።
'አንዳንድ ፀሎቶችን ጌታ አልመልስ ብሎ ሳይሆን ተመልሶ የማናየው በሚገባ ስላልተዋጋንበት ነው።ኤፌሶን 6:12 መጋደላችን ከስጋና ከደም ጋር አይደለም ከአለቆች ከስልጣናት በሰማይም ስፍራ ካሉ ከርኩሳን መናፍስት ጋር ነው ካለን ጦርነቱ ተራ ጦርነት ሳይሆን እስከመጋደል ነው ማለት ነው።ህይወትህ አልንቀሳቀስ ያለው አንዱ ምክንያት የማታየው ሰራዊት እየተዋጋህ ስለሆነ ነው።በጊዜውም ካለጊዜውም እረፍት እየነሳህ ስትዋጋቸው ነገርህ ይለቀቃል።'
ኢየሱስ አዳኝና ጌታ ነው!!!

@jesusministry
@jesusministry
673 viewsAbrham, 09:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ