Get Mystery Box with random crypto!

ብዙ ጊዜ የምንስተው በዚህ ነው:-አንድን አማኝ የምንለካው ባገኘው ነገር እንጂ በከፈለው ነገር አይ | Jesus' ministry

ብዙ ጊዜ የምንስተው በዚህ ነው:-አንድን አማኝ የምንለካው ባገኘው ነገር እንጂ በከፈለው ነገር አይደለም።ነገር ግን የአንድ አማኝ ስኬት ስለክርስትና ህይወቱ በከፈለው ዋጋ እንጂ ባገኘው ነገር አይለካም አይመዘንም።
አንድን አማኝ ሀብት እያካበት ስላየነው፣ስራው ስለሰመረለት፣በሌላም አቅጣጫ ቢሆን የሆነ ነገር ስለተጨመረለት እና ሲጨመርለት በክርስትናው አደገ ወይም ለእግዚአብሔር ቅርብ ነው እንላለን።ይህ አመለካከት ግን ፈፅሞ ከእውነተኛ መፅሀፍ ቅዱሳዊ አስተምሮ ያፈነገጠ ነው።በምድር የሚጨመርልን ነገር ሁሉ ፈፅሞ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን እውነተኛ ህብረትና መታዘዝ አያመለክትም።
እንደፈቃዱ እየኖሩ በምድራዊ አተያይ ምንም ያልተጨመራቸው የሚመስሉ በሰማይ ግን ታላቅ አክሊል የሚጠብቃቸው አማኞችና አገልጋዮች አሉ።በምድር በተሟላ ኑሮዋቸው በእግዚአብሔር የተከበሩ የሚመስሉ በእግዚአብሔር ግን የታዘነባቸው አማኞች እና አገልጋዮች በሌላ መንገድ አሉ።
በምድር ላይ የሆነ ነገር ሲጨመርልን እግዚአብሔር ይበልጥ እንደቀረበን የሚሰማን ስንሆን:የሆነ ነገር ሲጎለን ደግሞ እግዚአብሔር የራቀን የተወን ሲመስለን ስተናል።የእግዚአብሄርንም ቃል እንደማናጠና ትልቅ ምልክት ነው።
ኑሮዋቸው እየሞላላቸው ያሰቡትም እየተሳካላቸው ያሉትን ክርስቲያኖች አይተን ለክርስቶስ ምን ያክል እንደተቆረሱና እንደከፈሉ ሳናይ እንቀናባቸዋለን።በህይወታቸው ከፍለውና ተቆርሰው የሚኖሩ አማኞችና አገልጋዮችን ደግሞ ደማቅ ኑሮ እየኖሩ ስላልሆኑና፣ብዙ የሚከተላቸው ስለሌለ፣ሀብትም ስለሌላቸው አንቀናባቸውም።

አንድ አማኝ ግን በእግዚአብሔር ፊት ሲመዘን በተቆረሰበት ነገር በሰጠው ነገር በከፈለው ዋጋ ከእግዚአብሔር ጋር ባለው ህብረት ይመዘናል እንጂ በተቀበለውና በተጨመረለት ነገር አይመዘንም።

እኛም ትምህርት እንዲሆንልን እና መመለስ እንዲሆንልን ትኩረታችን ስለጌታ ነገር ዋጋ እየከፈለ ባለውና በከፈለው ላይ ይሁን።ህይወታቸው ምሳሌ ይሆንልናልና።
የህይወታችንም ዋጋ በእግዚአብሔር ፊት እየጨመረች የምትመጣው ተሳክቶላት፣ፀሎቷ ተሰምቶ ያሰበችው ሲሳካ፣ኑሮዋ ሲሻሻል ሳይሆን በየጊዜው ለጌታ ህይወቷን ስትተው፣ለእግዚአብሔር ፈቃድ ስትቆረስ፣ በህይወት ስትከፍል ነው።

https://t.me/jesusministry
https://t.me/jesusministry