Get Mystery Box with random crypto!

ጤና 123 / health 123

የቴሌግራም ቻናል አርማ healthtena123 — ጤና 123 / health 123
የቴሌግራም ቻናል አርማ healthtena123 — ጤና 123 / health 123
የሰርጥ አድራሻ: @healthtena123
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 123

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-13 20:27:43
34 views17:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 20:27:00 በቆሎን የመመገብ የጤና ጥቅሞች
(በዶ/ር ሆነሊያት ኤፍሬም)

✓ ለኪንታሮት ህመም እና ለፊንጢጣ ካንሰር የመጋለጥ እድልን ይቀንሳል

በቆሎ በፋየበር የበለፀገ ስለሆን እንደ ሆድ ድርቀት እና ተያይዞ የሚመጣውን የኪንታሮት ህመም ተጋላጭነት በእጅጉ ይቀንሳል።

✓ ለሰውነታችን ጠቃሚ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ይዟል

እንደ ፎስፈረስ ለአጥንት ጥንካሬና እድገት ጠቀሜታ ያለው እና ማግኒዚየም ለልብ እንዲሁም ለአጥንት ጥንካሬ የሚጠቅሙ ንጥረነገሮች አሉት።

✓ የኮሌስቴሮል መጠንን ይቀንሳል

በቆሎ መጥፎ የምንለውን የኮሌስቴሮል አይነት እንዲቀንስ የሚያደርግ ሲሆን ይህም ከልብ ህመም እና ሌሎች ከኮሌስቴሮል መጠን መጨመር ጋር ተያያዥነት ባላቸው በሽታዎች እንዳንጠቃ ያደርጋል።

✓ የቫይታሚን ምንጭ ነው

በቆሎ በቫይታሚን ቢ የበለፀገ ስለሆነ በተለየም ታያሚን ለነርቭ ጤናማነት ወሳኝ ሚናን ይጫወታል።

✓ የበቆሎ አንቲኦክስደንት ባህርይ ስላለው ካንሰርን የመከላከል አቅም እንዳለው ጥናቶች ያሳያሉ።

ጤና ይስጥልኝ
38 views17:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 17:31:53 #ጡት የምታጠባ #እናት ለራስዋ የምታገኛቸው #አስር የጤና ጥቅሞች እና ለልጇ የምትሰጣቸው #ስምንት በረከቶች


አሁን አሁን ጡትን ማጥባት ባህላዊ ጡጦ/የጣሳ ወተት ማጥባት ደሞ ዘመናዊነት እየመሰለ መቷል

በተለይ ደሞ በከተሞች አካባቢ አንዳንድ እናቶች ልጆቻቸዉን የሚያጠቡት ከራሳቸው የተፈጥሮ የጡት ወተት ይልቅ የጣሳ ወተትን ሆኗል::

አንዳንድ እናቶች ደሞ የጡት ወተት በበቂ መጠን እያላቸው ራሱ የጣሳ ወተት(#formula #milk) ለልጃቸው ካልሰጡ ልጆቻቸው የሚጎዱ ይመስላቸዋል::

ሆኖም ግን እስካሁን በተጠኑት ጥናቶች መሰረት የእናትን ወተት መተኪያ የሌለው ንፁሃን እና ተስማሚ የህፃናት ምግብ ነው

ስለዝህም ህፃናት ያለምንም ተጨማሪ ምግብ የመጀመሪያዎቹን 6 ወራት የእናት ጡት ወተት ብቻ ማግኘት አለባቸው

የእናት ጡት ወተት ጥቅሙ ልጇ ብቻ ሳይሆን ለእናትም ለቤተሰብም ለማህበረሰብም ከፍ ሲልም ለሀገር ነው ቀጥሎም ለአለምም ነው :: እስኪ የ እናት ወተት ማጥባት ጥቅሞችን በዝርዝር እንያቸው ፦

#ጡት #ማጥባት ለእናቶች ምን ምን ጥቅም አለዉ

1. ከወሊድ በዋላ #ማህፀን ቶሎ እንዲኮማተር እና ወደ ቦታ እንዲመለስ ያረጋል:: ይሄም የደም መፍሰስ እንዳይከሰት ይከላከላል
2. ከወሊድ በዋላ #ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል:: ጡት ማጥባት ተጨማሪ ካሎሪ ስለሚፈልግ በተለይ ከ 3 ወር በዋላ ኪሎሽ ወደ በፊቱ ኪሎ ልመለስ ይችላል::
3. የጡት እና የእንቁላል ማኩረቻ ካንሰርን ይከላከላል (#breast #cancer & #ovarian #cancer)
4. በእድሜ የሚመጡ በሽታዎችን ለምሳሌ #ስኳር #ደም ግፊት #የልብ ህመም እና የመሳሰሉትን በሽታዎችን ይከላከላል
5.በእናት እና በልጅ መሃል ያለውን ፍቅር ይጨምራል
6. ከወሊድ በዋላ የሚመጣው ጭንቀት(#Postpartum #depression) ይቀንሳል
7. እናት ስታጠባ ከ አይምሮዋ የሚመነጨው #Oxytocin የሚባል ሆርሞን ደስተኛ እንድትሆን እና ተጨማሪ ወተት እንድታመርት ያደርጋል
8. በተፈጥሮ ፀጋ ስለሚገኝ ስለሆነ ወጪ ቆጣቢ ነው ::
9. ለአጭር ጊዜ ቢሆንም እርግዝናን ይከላከላል
(#አስተውሉ : በተለይ የወር አበባ ተመልሶ ካልመጣ እርግዝና የመከሰቱ ዕድል ዝቅተኛ ነው)
10. ጊዜ ቆጣቢ እና ለ እናት ቀላል ነው
ለምሳሌ : አንድ እናት ሌሊት ከ እንቅልፏ ተነስታ የጣሳ ወተት በጥብጣ ከመስጠት ይልቅ በቀላሉ ጡቷን ማጥባት ትቺላለች

ጡትን ማጥባት ዘመናዊነት ነው

#የእናት #ጡት #ወተት #ለህፃናት ያለው ጥቅምስ ምንድነው

ትክክለኛ እና በቂ የሆኑ ንጥረ ነገሮች በውስጡ ስለያዘ ህፃናት በተገቢው ሁኔታ እንዲያድጉ ይረዳል
የብሩህ አይምሮ(#Higher #IQ) ባለቤት ያረጋቸዋል የተሻለ ብቃት እንዲኖራቸው ያረጋቸዋል
የተለያዩ የህፃናት ኢንፌክሽኖችን ይከላከላል
ለምሳሌ የ ጆሮ፣የሳምባ፣ የአንጀት ፣የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን
ህፃናትን ከ ተቅማት እና ተያያዥ በሽታዎች ይከላለላል
የልጆች አለርጂን ይከላከላል
ልጆች ከመጠን ያለፈ ውፍረት እንዳይኖራቸዉ ይከላከላል(#obesity)
የመጀመርያዉ አይነት የስኳር በሽታ(#Type 1 #Diabetus #Mellitus) ይከላከላል
ድንገተኛ የሆነ የጨቅላ ህፃናትን ሞት(#sudden infant #death #syndrome) ይከላከላል

#የእናት ጡት ወተት ማጥባት ለ#ቤተሰብ እና ለ #ማህበረሰብ እና ለሀገር ያለው ጥቅም
ወጪ ቆጣቢ እና በተፈጥሮ የተሰጠ ነው
የተለያዩ የህፃናት በሽታ በመከላከል የሀገሪቱን የጤና ወጪ ይቀንሳል
በአጠቃላይ የህፃናትን በሺታዎች በመቀነስ በሀገር ደረጃ የህፃናት ሞትን(#child #mortality #rate) በእጅጉ ይቀንሳል
ልጆች ባለ ብሩህ አይምሮ ሆነው እንዲያድጉ በመርዳት በትምህርትም ዉጤታማ እንዲሆኑ ከዛም እንደ ሀገር ጥሩ አበርክቶ እንዲኖራቸዉ ቀላል የማይባል አስተዋፆ አለው::

ታድያ እነዝህን ጥቅሞች ያወቀች እና የተረዳች እናት የምትጠይቃቸው #ጥያቄዎች አሉ ለምሳሌ

1. ልጄን በቀን ዉስጥ ስንት ጊዜ ነው ማጥባት ያለብኝ
2. ልጄ ጡት ለመጥባት ሲፈልግምን አይነት ምልክቶችን ያሳያል
3.ልጄ ከተኛ ቀስቃሼ ማጥባት አለብኝ እስከ መቼ
4. ልጄ አንዴ ሲጠባ ለምን ያህል ደቂቃ መጥባት አለበት
5. የጡቴ ወተት እንደሚያጠግበው እና እንደማያጠግበው በምን አውቃለሁ
6. አልቤ ያስቀመጥኩትን የጡት ወተት ለምን ያህል ጊዜ መጠቀም ይቻላል

እነዝህን እና የመሳሰሉትን ወሳኝ ጥያቄዎች መልስ በነገው ዕለተ በቴሌግራም ቻናላችን ላይ ይዘን እንቀርባለን Join አርገው ይከታተሉን


ቴሌግራም : t.me/doctorfasil Join ያርጉን #ቤተሰብ ይሁን! በነፃ ይማሩ

FB:fb.me/drfasilpediatrician

ጠቃሚ መረጃ ነው ብለው ካሰቡ share ያድርጉት

አዘጋጅ ዶ/ር ፋሲል መንበረ
(በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊንየም ሜድካል ኮሌጅ ረዳት ፕሮፌሰር እና የህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም)

በአካል ሆስፒታል ላይ መተው ለልጅዎ ሕክምና እና ምርመራ በህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም(ዶ/ር ፋሲልን)ማግኘት ከፈለጉ በዝህ ስልክ ይደውሉ እና ቀጠሮ ያስይዙ

0984650912

ወይም ደሞ በቤትዎ ሆነው ስለ ልጅዎ ጤንነት እና እንክብካቤ ዶ/ር ፋሲልን ለማምከር ከፈለጉ "WeCare ET patient" የሚለውን መተግበርያ ከ google play ላይ አውረደው ማምከር ይቺላሉ

መተግበርያውን (Application) ወደ ስልኮ ለማውረድ ከታች ያለውን link ከፍተው ማውረድ ይቺላሉ

https://play.google.com/store/apps/details?id=com.icare.patient

ለበለጠ መረጃ 9394 በነፃ የመስመር ስልክን ደውለው ስለ application (መተግበርያው) አጠቃቀም መጠየቅ ይችላሉ::
28 views14:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 11:07:17
232 views08:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 11:06:33 የነጭ ሽንኩርት መድኃኒትነት

1. ነጭ ሽንኩርት ስራን በትክክል ለማከናወን፣ የሰውነት ሕዋሳትን ጤናማ ለማድረግ ፣ድካምን ለማስወገድ፣ዕድሜን ለመጨመር፣በአይጥና በልዩ ልዩ ተባዮች የሚመጡትን ተስቦ በሸታዎችን ለመከላከል ነጭ ሽንኩርት መብላት በጣም ጠቃሚ ነው፡፡

2. ማንኛውም ሰው መጥፎ ሽታ ባለበት አካባቢ ለፅዳት ከመሰማራቱ በፊት ነጭ ሽንኩርት ከትፎ ቢበላ ከማንኛውም በሽታ ከሚያመጡ ተዋህሲያን ለመዳን ይቻላል፡፡

3. በቂ ሕክምና በሌለበት አካባቢ በቁስል ለሚሰቃይ ሕሙማን በነጭ ሽንኩርት ጭማቂ አጥቦ በቁስሉ ዙሪያ በመደምደም በፋሻ ወይም በንፁህ ጨርቅ በማሰር ሕመምተኛውን ለመፈወስ ይችላል፡፡

4. ነጭ ሽንኩርት ቀቅሎ እንፋሎቱን የካንሰርንና የቲቢ በሽታዎችን ለመከላከልና በሳንባ አካባቢ ብርድና ጉንፋን ለማዳን ፍቱን መድኃኒቱ ነው፡፡

5. ብርድ ብርድ በሚያሰኝ ሕመምና በተለይም በጥርስ ሕመም ለሚሰቃዩት ሕሙማን ሁለት ራስ ነጭ ሽንኩርት የውስጠኛውን ሽፋናቸውን በመላጥ በሁለቱም ጉንጫቸው በተለይም በተነቃነቀው ጥርስ በኩል ነክሰው ረዘም ላሉት ሰዓት ቢጠቀሙበት መልሶ መልሶ ይጠነክራል፡፡

6. ለአስም፣ ለጉሮሮ ክርካሪ ወይም ኮርታ ለተባለው በሽታ እንዲሁም ጉሮሮ ለማፅዳት የነጭ ሽንኩርት ጭማቂ በስኳር ወይም በማር መጠጣት የተፈተነ መድኃኒት ነው፡፡

7. ነጭ ሽንኩርት የራስ ምታትና የደም ብዛት ያለባቸው ሰዎች ከ3 እስከ 5 ቀናት በማከታተል ሦስት ሦስት ፍንካች በቀን ሦስት ጊዜ ቢበሉ ከድካምና ከደም ብዛት ሊፈወሱ ይችላሉ፡፡

8. በደም መርጋት ምክንያት ለሚሰቃዩ ፣የልብ በሽታን፣ የፊንጢጣ ኪንታሮትና የእግር ደም ሥር እብጠት varicose የተባሉትን በሽታዎች ለመከላከልና ለመዳን ነጭ ሽንኩርት በመብላት መፈወስ ይችላል፡፡

9. ነጭ ሽንኩርት የቆላ ቁስል፣ችፌን፣የጨጓራ በሽታን ወረርሽኝን ኮሌራን ሳይቲካን የቁርጥማትን ሕመምን እንደሚያድን የተረጋገጠ ነው፡፡


ምንጭ ከ FB መንደር
225 viewsedited  08:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-12 15:21:30 የጥርስ መቦርቦር( dental caries )
የጥርስ መቦርቦር ወይም መበስበስ ፡-በዋናነት ለዚህ አጋላጭ ነው ተብሎ የሚታሠበው የ flouride እጥረት ሲሆን ይህ ደግሞ ጥርሳችንን ደካማ ያደርገዋል ::ይህ ሚነራል መበስበስ የጀመሩ ጥርሶችን ሁሉ ቀስ በቀስ የመሙላት ፣ባክቴሪያዎችም እንዳይባዙ የማድረግ ጥቅም ስላለው እጅግ አስፈላጊ ነው።
ብዙ ጊዜ የምንጠጣዉ ውሀ ላይ ይጨመራል፡፡ለመከላከል፦
1.በቀን ቢያንስ ሁለት ጊዜ flouride ባላቸው የጥርስ ሳሙናዎች መቦረሽ ፡ በተለይ ማታ ማታ
2.ሁልጊዜ ከምግብ በኌላ መጉመጥመጥ
3.ስኳር እና ስኳር የበዛባቸው ምግቦች እና መጠጦችን መቀነስ
4.ሲጋራ አለማጨስ...
ቀለል ያለ መቦርቦር ከሆነ በነዚህ ጥንቃቄዎች ተመልሶ ሊሞላ ይችላል ሌሎቹ ደግሞ የመዛመት ባህሪም ስላላቸው መነቀል ወይም ሙሌት አማራጮች ናቸው፡፡
438 views12:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-19 13:51:41 ማይግሬን የተባለ የራስ ምታት/ ህመም/

ማይግሬን ለማስታገስ ጠቃሚ ምክሮች

የተረጋጋ እና ፀጥ ያለ ቦታ ይምረጡ

በአካባቢዎ የሚገኝ መብራት ማጥፋት እና ከተቻለ እንቅልፍ መተኛት,የሞቀ ወይንም የቀዘቀዘ ውኃን በላስቲክ በማድረግ በእራስዎ እና በአንገትዎ ላይ ማስቀመጥ, ይህ ማለት ደግሞቅዝቃዜው በማደንዘዝ ሕመም እንዳይሰማዎ ሲያደርግ ሙቀቱ ደግሞ የራስና የአንገት ጡንቻዎችን እንዲፈታቱ ያደርጋልሕመም የሚሰማዎ ቦታ ላይ በቀላሉ ማሸት አንገትዎን እና ትከሻዎን ማሸትገላዎን በሙቅ ውሀ መታጠብ

በቂ እረፍት ማድረግ

መደበኛ የእንቅልፍ ሰዓት ይኑርዎሁሌም በተመሳሳይ ሰዓት የመተኛት ልምድ ያዳብሩበቀን እንቅልፍ መተኛት ያስለመዱ ከሆነ ከ20-30 ደቂቃ ብቻ ቢሆን ይመከራል. ከዛ በላይ እንቅልፍ ከወሰዱ የለሊት እንቅልፍዎን ሊያዛባ ይችላልእንቅልፍዎ ያልመጣ ከሆነ እራስዎን አያስገድዱ መጽሐፍ በማንበብ ራስዎን ያድክሙ

አመጋገብዎን ያስተካክሉ

መደበኛ የሆነ የምግብ ሰዓት ይኑርዎቁርስዎን መመገብ አይዘንጉማይግሬን ቀስቃሽ የሆኑ ምግቦችን ያስወግዱ (እንደ ቼኮሌት, አይብ, ቡና እና የአልኮል መጠጦች)

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የማይግሬን ራስ ምታትን ይቀሰቅሳል ነገር ግን ሐኪምዎን በማማከር ቀለል ያሉ እንቅስቃሴዎችን ያድርጉ (ለምሳሌ እንደ ውሃ ዋና; የእግር ጉዞ የመሳሰሉትን ማድረግ ይችላሉ)

ጭንቀትዎን ይቆጣጠሩ

ጭንቀት የማይግሬን ራስ ምታትን ይቀሰቅሳል. በዕለት ተዕለት የኑሮ ሁኔታዎች የሚያጋጥሙንን አስጨናቂ ነገሮች መከላከል ባይቻልም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በመፈፀም መቀነስ ይችላሉ.ቀለል ያለ የኑሮ ዘይቤ ይኑርዎጊዜዎን በአግባቡ ይጠቀሙየዕረፍት ጊዜ ይኑርዎለነገሮች በጎ አመለካከት ይኑርዎራስዎን ዘና ያድርጉ

የራስ ምታትዎን በተመለከተ የግል ማኅደር ይኑርዎ

በግል ማኅደር መመዝገብ ራስምታትዎን የሚያስነሳውን ሁኔታ ለማወቅ እና ምን እንደሚያስታግስልዎም ለማጤን ይረዳል.
427 viewsedited  10:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-05 17:10:53 6 ለኩላሊት ድክመት የሚዳርጉ አደገኛ ልማዶች

1.ጨው ማብዛት ፦ ጨው በሰውነታችን ውስጥ ውሃ እንዲቆይ በማድረግ የደም ግፊታችን እንዲጨምር ያደርጋል ። የደም ግፊት ደሞ የኩላሊት ድክመት በማምጣት 2ኛውን ደረጃ ይይዛል።ይህ ደሞ ወደ ዳያሊሲስ(የኩላሊት እጥበት ) ወይም ወደ ኩላሊት ንቅለ ተከላ ያመራል። ጨው በመቀነስ የኩላሊት ጤናን መጠበቅ ይቻላል።

2.የሰውነት ፈሳሽ(ውሃ ማነስ)፦ በሰውነት ውስጥ ያለው የፈሳሽ መጠን አነስተኛ ሲሆን ኩላሊት ላይ ጉዳት ያደርሳል። ይህም ፕሪ ሬናል አዞቴሚያ በመባል ሲታወቅ አ(acute kidney injury ) ያስከትላል። ይህንንም ለመከላከል በቀን ከ2-3 ሊትር ውሃ መጠጣት ያስፈልጋል። ነገር ግን የልብ ድካም ፣የሳንባ ችግር ካለቦት ምን ያህል ውሃ መውሰድ እዳለቦት ከሐኪሞ ጋር ይወያዩ። እነዚህ በሽታዎች ያሉበት ሰው ከጤነኛ ሰው ያነሰ ውሃ ይወስዳል።ሌላው ሻይ ፣ ቡና፣ ለስላሳ መጠጥና ቢራ ውሃን አይተኩም።

3.ማስታገሻ ማብዛት ፦ነን ስቴሮይዳል አንቲ ኢንፍላማቶሪ ድረግስ(Non steroidal anti-inflammatory drugs) የተባሉት የመስታገሻ ዝርያዎች በብዛት ከምንጠቀምባቸው መድኃኒቶች ውስጥ ናቸው። እነዚህ መድኃኒቶች ለአብዛኛው ሰው ለአጭር ጊዜ ቢወሰዱ ችግር የማይፈጥሩ ቢሆኑም አብዝቶ በተደጋጋሚ መውሰድ ግን ለኩላሊት ችግር ይዳርጋል። በተለይ የደም ግፊት ና ስኳር ባለባቸው ሰዎች ላይ እነዚህ መድኃኒቶች በብዛት ለረጅም ጊዜ መወሰድ የለባቸውም። በሀገራችን በብዛት የሚገኙት የዚህ ዝርያ መድኋኒቶች፦ ዳይክሎፌናክ፣አይቡፕሮፌ፣ሜሎክሲካም፣ ሪሊፍ የመሳሰሉት ይገኙበታል። የጀርባ ህመም ፣ሪህ፣ቁርጥማት ያለባቸው ስዎች ለነዚህ መድሀኒቶች የተጋለጡ ሲሆን እነዚህ ሰዎች ውሃ በብዛት መውሰድና ያለሐኪ ትዛዝ ተጨማሪ ማስታገሻ አለመውሰድ ይኖርባቸዋል።

4.አልኮል ማብዛት ፦አልኮል በብዛት መጠጣት ወደ ግፊት ያመራል። ግፊት ከላይ እንደጠቀስኩት ወደ ኩላሊት ድክመት ያመራል። በተጨማሪም አልኮል በብዛት መጠጣት ቶሎቶሎ ስለሚያሸና በሰውነት ውስጥ ያለው ፈሳሽ እንዲቀንስ ያደርጋል። ይህም ኩላሊት ይጎዳል።

5.ሲጋራ ማጨስ ፦ በርግጥ ሲጋራ በጣም ለበርካታ በሽታዎች አጋላጭ መሆኑ ይታወቃል። ወደ ኩላሊት የሚሄደውን የደም ፍሰት በመቀነስ በኩላሊትም ጉዳት ያደርሳል። በተጨማሪም ለኩላሊት ካንሰር ያጋልጣል። ሲጋራ ማጨስ አደገኛና ለኩላሊት ድክመት የሚያጋልጥ ልማድ ነው።

6.አደገኛ እፆች፦እንደ ኮኬይን ፣ ሄሮይንና ኤክስታሲ የቸሰኙ እፆች ኩላሊትን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለድክመት ሊዳርጉ ይችላሉ። ኮኬይን በተጨማሪም ለደም ግፊት ይዳርጋል።
337 views14:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-01 12:27:25
245 views09:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-30 15:18:20
254 views12:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ