Get Mystery Box with random crypto!

#ጡት የምታጠባ #እናት ለራስዋ የምታገኛቸው #አስር የጤና ጥቅሞች እና ለልጇ የምትሰጣቸው #ስምንት | ጤና 123 / health 123

#ጡት የምታጠባ #እናት ለራስዋ የምታገኛቸው #አስር የጤና ጥቅሞች እና ለልጇ የምትሰጣቸው #ስምንት በረከቶች


አሁን አሁን ጡትን ማጥባት ባህላዊ ጡጦ/የጣሳ ወተት ማጥባት ደሞ ዘመናዊነት እየመሰለ መቷል

በተለይ ደሞ በከተሞች አካባቢ አንዳንድ እናቶች ልጆቻቸዉን የሚያጠቡት ከራሳቸው የተፈጥሮ የጡት ወተት ይልቅ የጣሳ ወተትን ሆኗል::

አንዳንድ እናቶች ደሞ የጡት ወተት በበቂ መጠን እያላቸው ራሱ የጣሳ ወተት(#formula #milk) ለልጃቸው ካልሰጡ ልጆቻቸው የሚጎዱ ይመስላቸዋል::

ሆኖም ግን እስካሁን በተጠኑት ጥናቶች መሰረት የእናትን ወተት መተኪያ የሌለው ንፁሃን እና ተስማሚ የህፃናት ምግብ ነው

ስለዝህም ህፃናት ያለምንም ተጨማሪ ምግብ የመጀመሪያዎቹን 6 ወራት የእናት ጡት ወተት ብቻ ማግኘት አለባቸው

የእናት ጡት ወተት ጥቅሙ ልጇ ብቻ ሳይሆን ለእናትም ለቤተሰብም ለማህበረሰብም ከፍ ሲልም ለሀገር ነው ቀጥሎም ለአለምም ነው :: እስኪ የ እናት ወተት ማጥባት ጥቅሞችን በዝርዝር እንያቸው ፦

#ጡት #ማጥባት ለእናቶች ምን ምን ጥቅም አለዉ

1. ከወሊድ በዋላ #ማህፀን ቶሎ እንዲኮማተር እና ወደ ቦታ እንዲመለስ ያረጋል:: ይሄም የደም መፍሰስ እንዳይከሰት ይከላከላል
2. ከወሊድ በዋላ #ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል:: ጡት ማጥባት ተጨማሪ ካሎሪ ስለሚፈልግ በተለይ ከ 3 ወር በዋላ ኪሎሽ ወደ በፊቱ ኪሎ ልመለስ ይችላል::
3. የጡት እና የእንቁላል ማኩረቻ ካንሰርን ይከላከላል (#breast #cancer & #ovarian #cancer)
4. በእድሜ የሚመጡ በሽታዎችን ለምሳሌ #ስኳር #ደም ግፊት #የልብ ህመም እና የመሳሰሉትን በሽታዎችን ይከላከላል
5.በእናት እና በልጅ መሃል ያለውን ፍቅር ይጨምራል
6. ከወሊድ በዋላ የሚመጣው ጭንቀት(#Postpartum #depression) ይቀንሳል
7. እናት ስታጠባ ከ አይምሮዋ የሚመነጨው #Oxytocin የሚባል ሆርሞን ደስተኛ እንድትሆን እና ተጨማሪ ወተት እንድታመርት ያደርጋል
8. በተፈጥሮ ፀጋ ስለሚገኝ ስለሆነ ወጪ ቆጣቢ ነው ::
9. ለአጭር ጊዜ ቢሆንም እርግዝናን ይከላከላል
(#አስተውሉ : በተለይ የወር አበባ ተመልሶ ካልመጣ እርግዝና የመከሰቱ ዕድል ዝቅተኛ ነው)
10. ጊዜ ቆጣቢ እና ለ እናት ቀላል ነው
ለምሳሌ : አንድ እናት ሌሊት ከ እንቅልፏ ተነስታ የጣሳ ወተት በጥብጣ ከመስጠት ይልቅ በቀላሉ ጡቷን ማጥባት ትቺላለች

ጡትን ማጥባት ዘመናዊነት ነው

#የእናት #ጡት #ወተት #ለህፃናት ያለው ጥቅምስ ምንድነው

ትክክለኛ እና በቂ የሆኑ ንጥረ ነገሮች በውስጡ ስለያዘ ህፃናት በተገቢው ሁኔታ እንዲያድጉ ይረዳል
የብሩህ አይምሮ(#Higher #IQ) ባለቤት ያረጋቸዋል የተሻለ ብቃት እንዲኖራቸው ያረጋቸዋል
የተለያዩ የህፃናት ኢንፌክሽኖችን ይከላከላል
ለምሳሌ የ ጆሮ፣የሳምባ፣ የአንጀት ፣የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን
ህፃናትን ከ ተቅማት እና ተያያዥ በሽታዎች ይከላለላል
የልጆች አለርጂን ይከላከላል
ልጆች ከመጠን ያለፈ ውፍረት እንዳይኖራቸዉ ይከላከላል(#obesity)
የመጀመርያዉ አይነት የስኳር በሽታ(#Type 1 #Diabetus #Mellitus) ይከላከላል
ድንገተኛ የሆነ የጨቅላ ህፃናትን ሞት(#sudden infant #death #syndrome) ይከላከላል

#የእናት ጡት ወተት ማጥባት ለ#ቤተሰብ እና ለ #ማህበረሰብ እና ለሀገር ያለው ጥቅም
ወጪ ቆጣቢ እና በተፈጥሮ የተሰጠ ነው
የተለያዩ የህፃናት በሽታ በመከላከል የሀገሪቱን የጤና ወጪ ይቀንሳል
በአጠቃላይ የህፃናትን በሺታዎች በመቀነስ በሀገር ደረጃ የህፃናት ሞትን(#child #mortality #rate) በእጅጉ ይቀንሳል
ልጆች ባለ ብሩህ አይምሮ ሆነው እንዲያድጉ በመርዳት በትምህርትም ዉጤታማ እንዲሆኑ ከዛም እንደ ሀገር ጥሩ አበርክቶ እንዲኖራቸዉ ቀላል የማይባል አስተዋፆ አለው::

ታድያ እነዝህን ጥቅሞች ያወቀች እና የተረዳች እናት የምትጠይቃቸው #ጥያቄዎች አሉ ለምሳሌ

1. ልጄን በቀን ዉስጥ ስንት ጊዜ ነው ማጥባት ያለብኝ
2. ልጄ ጡት ለመጥባት ሲፈልግምን አይነት ምልክቶችን ያሳያል
3.ልጄ ከተኛ ቀስቃሼ ማጥባት አለብኝ እስከ መቼ
4. ልጄ አንዴ ሲጠባ ለምን ያህል ደቂቃ መጥባት አለበት
5. የጡቴ ወተት እንደሚያጠግበው እና እንደማያጠግበው በምን አውቃለሁ
6. አልቤ ያስቀመጥኩትን የጡት ወተት ለምን ያህል ጊዜ መጠቀም ይቻላል

እነዝህን እና የመሳሰሉትን ወሳኝ ጥያቄዎች መልስ በነገው ዕለተ በቴሌግራም ቻናላችን ላይ ይዘን እንቀርባለን Join አርገው ይከታተሉን


ቴሌግራም : t.me/doctorfasil Join ያርጉን #ቤተሰብ ይሁን! በነፃ ይማሩ

FB:fb.me/drfasilpediatrician

ጠቃሚ መረጃ ነው ብለው ካሰቡ share ያድርጉት

አዘጋጅ ዶ/ር ፋሲል መንበረ
(በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊንየም ሜድካል ኮሌጅ ረዳት ፕሮፌሰር እና የህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም)

በአካል ሆስፒታል ላይ መተው ለልጅዎ ሕክምና እና ምርመራ በህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም(ዶ/ር ፋሲልን)ማግኘት ከፈለጉ በዝህ ስልክ ይደውሉ እና ቀጠሮ ያስይዙ

0984650912

ወይም ደሞ በቤትዎ ሆነው ስለ ልጅዎ ጤንነት እና እንክብካቤ ዶ/ር ፋሲልን ለማምከር ከፈለጉ "WeCare ET patient" የሚለውን መተግበርያ ከ google play ላይ አውረደው ማምከር ይቺላሉ

መተግበርያውን (Application) ወደ ስልኮ ለማውረድ ከታች ያለውን link ከፍተው ማውረድ ይቺላሉ

https://play.google.com/store/apps/details?id=com.icare.patient

ለበለጠ መረጃ 9394 በነፃ የመስመር ስልክን ደውለው ስለ application (መተግበርያው) አጠቃቀም መጠየቅ ይችላሉ::