Get Mystery Box with random crypto!

የጥርስ መቦርቦር( dental caries ) የጥርስ መቦርቦር ወይም መበስበስ ፡-በዋናነት ለዚህ አ | ጤና 123 / health 123

የጥርስ መቦርቦር( dental caries )
የጥርስ መቦርቦር ወይም መበስበስ ፡-በዋናነት ለዚህ አጋላጭ ነው ተብሎ የሚታሠበው የ flouride እጥረት ሲሆን ይህ ደግሞ ጥርሳችንን ደካማ ያደርገዋል ::ይህ ሚነራል መበስበስ የጀመሩ ጥርሶችን ሁሉ ቀስ በቀስ የመሙላት ፣ባክቴሪያዎችም እንዳይባዙ የማድረግ ጥቅም ስላለው እጅግ አስፈላጊ ነው።
ብዙ ጊዜ የምንጠጣዉ ውሀ ላይ ይጨመራል፡፡ለመከላከል፦
1.በቀን ቢያንስ ሁለት ጊዜ flouride ባላቸው የጥርስ ሳሙናዎች መቦረሽ ፡ በተለይ ማታ ማታ
2.ሁልጊዜ ከምግብ በኌላ መጉመጥመጥ
3.ስኳር እና ስኳር የበዛባቸው ምግቦች እና መጠጦችን መቀነስ
4.ሲጋራ አለማጨስ...
ቀለል ያለ መቦርቦር ከሆነ በነዚህ ጥንቃቄዎች ተመልሶ ሊሞላ ይችላል ሌሎቹ ደግሞ የመዛመት ባህሪም ስላላቸው መነቀል ወይም ሙሌት አማራጮች ናቸው፡፡