Get Mystery Box with random crypto!

ማይግሬን የተባለ የራስ ምታት/ ህመም/ ማይግሬን ለማስታገስ ጠቃሚ ምክሮች የተረጋጋ እና ፀጥ ያ | ጤና 123 / health 123

ማይግሬን የተባለ የራስ ምታት/ ህመም/

ማይግሬን ለማስታገስ ጠቃሚ ምክሮች

የተረጋጋ እና ፀጥ ያለ ቦታ ይምረጡ

በአካባቢዎ የሚገኝ መብራት ማጥፋት እና ከተቻለ እንቅልፍ መተኛት,የሞቀ ወይንም የቀዘቀዘ ውኃን በላስቲክ በማድረግ በእራስዎ እና በአንገትዎ ላይ ማስቀመጥ, ይህ ማለት ደግሞቅዝቃዜው በማደንዘዝ ሕመም እንዳይሰማዎ ሲያደርግ ሙቀቱ ደግሞ የራስና የአንገት ጡንቻዎችን እንዲፈታቱ ያደርጋልሕመም የሚሰማዎ ቦታ ላይ በቀላሉ ማሸት አንገትዎን እና ትከሻዎን ማሸትገላዎን በሙቅ ውሀ መታጠብ

በቂ እረፍት ማድረግ

መደበኛ የእንቅልፍ ሰዓት ይኑርዎሁሌም በተመሳሳይ ሰዓት የመተኛት ልምድ ያዳብሩበቀን እንቅልፍ መተኛት ያስለመዱ ከሆነ ከ20-30 ደቂቃ ብቻ ቢሆን ይመከራል. ከዛ በላይ እንቅልፍ ከወሰዱ የለሊት እንቅልፍዎን ሊያዛባ ይችላልእንቅልፍዎ ያልመጣ ከሆነ እራስዎን አያስገድዱ መጽሐፍ በማንበብ ራስዎን ያድክሙ

አመጋገብዎን ያስተካክሉ

መደበኛ የሆነ የምግብ ሰዓት ይኑርዎቁርስዎን መመገብ አይዘንጉማይግሬን ቀስቃሽ የሆኑ ምግቦችን ያስወግዱ (እንደ ቼኮሌት, አይብ, ቡና እና የአልኮል መጠጦች)

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የማይግሬን ራስ ምታትን ይቀሰቅሳል ነገር ግን ሐኪምዎን በማማከር ቀለል ያሉ እንቅስቃሴዎችን ያድርጉ (ለምሳሌ እንደ ውሃ ዋና; የእግር ጉዞ የመሳሰሉትን ማድረግ ይችላሉ)

ጭንቀትዎን ይቆጣጠሩ

ጭንቀት የማይግሬን ራስ ምታትን ይቀሰቅሳል. በዕለት ተዕለት የኑሮ ሁኔታዎች የሚያጋጥሙንን አስጨናቂ ነገሮች መከላከል ባይቻልም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በመፈፀም መቀነስ ይችላሉ.ቀለል ያለ የኑሮ ዘይቤ ይኑርዎጊዜዎን በአግባቡ ይጠቀሙየዕረፍት ጊዜ ይኑርዎለነገሮች በጎ አመለካከት ይኑርዎራስዎን ዘና ያድርጉ

የራስ ምታትዎን በተመለከተ የግል ማኅደር ይኑርዎ

በግል ማኅደር መመዝገብ ራስምታትዎን የሚያስነሳውን ሁኔታ ለማወቅ እና ምን እንደሚያስታግስልዎም ለማጤን ይረዳል.