Get Mystery Box with random crypto!

የጉመር ወረዳ መንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት

የቴሌግራም ቻናል አርማ gummerw — የጉመር ወረዳ መንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት
የቴሌግራም ቻናል አርማ gummerw — የጉመር ወረዳ መንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት
የሰርጥ አድራሻ: @gummerw
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 733
የሰርጥ መግለጫ

መረጃዎችና ጥቆማዎች ለማድረስ
251113110443
የስልክ ቁጥራችን ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ!!!
ትክክልኛ መረጃ ለህዝቡ እናድርስ!!!
የጉመር ወረዳ መንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-08 17:20:37 ሐምሌ 1/2014 ዓ.ም

የጉመር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፈይሰል ሀሰን 1443ኛውን የኢድ አል አድሀ አረፋ በዓል ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

ዋና አስተዳዳሪው በአለም አቀፍ ደረጃ 1443ኛ ጊዜ ለሚከበረው የኢድ አል አድሀ አረፋ በዓልን በማስመልከት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ ብለዋል።

ህብረተሰቡም የኢድ አል ፈጥር በዓል ሲያከብር ከመቼውም ጊዜ በበለጠ የተቸገሩትን በመርዳት ሊሆን እንደሚገባ ዋና አስተዳዳሪው ጠቁመዋል።

አክለውም አሁን ላይ ሀገራችን እንዳትረጋጋ የሚሹ ሀይሎች አንዴ የብሔር ገጽታ በሌላ ጊዜ ደግሞ የሀይማኖት ሽፋን በመስጠት ህብረተሰቡን እያሸበሩ ይገኛሉ ብለዋል።

ስለሆነም ህዝቡ የአካባቢውን ሰላም በማስጠበቅ እንዲሁም ለዘመናት የገነባነውን የሰላም፣ የመቻቻል፣ የአብሮነት፣ የመከባበር እና የመደጋገፍ እሴት በማጠናከር ሀገራዊ የለውጥ ጉዞውን እንዲያሳካ ጥሪ አቅርበዋል።

በመጨረሻም በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአብሮነት እና የመተሳሰብ እንዲሆን ተመኝተዋል።
ኢድ ሙባረክ

- ኢትዮጵያን እናልማ!
- የፈረሰውን እንገንባ!
- ለፈተና እንዘጋጅ!!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100068870753847
Telegram:- https://t.me/gummerw
Youtub: -https://youtube.com/channel/UCyqat__kk7lXxzpRv8r7chA
196 views14:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 19:30:39 ጀፎረን የመሰሉ እንቁ ቅርሶቻችንን በመንከባከብና በመጠበቅ ለትወልድ ማስተላለፍ ይገባል ሲሉ የወልቂጤ ዩንቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፋሪስ ደሊል ተናገሩ፡፡

በጀፎረ ቅርስ ዙሪያ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ የውይይት መድረክ በወልቂጤ ዩንቨርሲቲ ተካሂዷል፡፡

በጉራጌ ብሄረሰብ ዘንድ ጀፎሮ ወይም አውራ መንገድ ልዩ ታሪክ አለው፡፡ ጀፎሮ ለመንደሮቹ ትልቅ ውበትን በማልበስ ከዘመኑ መሀንዲስ ቅየሳ የማይተናነስ ባህላዊ ቅርስ እንዲሆንም አስችሎታል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የወልቂጤ ዩንቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፋሪስ ደሊል ጀፎረን የመሰሉ እንቁ እና አኩሪ ቅርሶቻችንን ተንከባክቦና ጠብቆ ለትውልድ ማስተላለፍ ይገባል ብለዋል፡፡

ዩንቨርሲቲው ከመማር ማስተማር ተልእኮ ጎን ለጎን በጥናትና ምርምር አንዲሁም በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ የሀገር በቀል እውቀት እና ባህል ልማት አቋቁሞ በርካታ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል ሲሉም ዶ/ር ፋሪስ ገልፀዋል፡፡

የጉራጌ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አሰፋ አካሉ በበኩላቸው የጀፎረን ባህላዊ ቅርስ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ እና ቅርሱን ለመጠበቅ ህጋዊ ማዕቀፍ እንደሚስፈልግ ተናግረዋል፡፡

የወልቂጤ ዩንቨርሲቲ ሀገር በቀል እውቀት ልማት ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር ቸርነት ዘርጋው ጀፎረ የጉራጌ ባህላዊ ቅርስ በተለያዩ ምክንያቶች የተደቀነበትን አደጋ ለመከላከልና ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተግባራት በዩኒቨርሲቲው እየተከናወኑ ይገኛል ብለዋል፡፡

የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሀላፊ አቶ ተመስገን ገ/መድህን እንደገለፁት ከተለያዩ መሰረተ ልማቶች መስፋፋት ጋር ተያይዞ ባህላዊ ቅርሱ ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለማስቀረት እና ለመጠበቅ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

በመድረኩ ተሳተፉ የጉራጌ ዞን የሀገር ሽማግሌዎች መካከልዳሞ በለጠ ወልዴ እና አቶ ጸጋየ ታቦር የገኙበታል፡፡
በሰጡት አስተያየትም አባቶች ጠብቀው ያቆዩትንና በርካታ ጠቀሜታ ያለውን የጀፎረ ባህላዊ ቅርስ ተንከባክቦ ለማቆየት የጆካ ባህላዊ አስተዳር ሸንጎ በትኩረት እንደሚሰራ አስገንዝበዋል፡፡

በመድረኩ ማጠቃለያም አሻራችን ለትውልዳችን በሚል መሪ ቃል የወልቂጤ ዩንቨርሲቲ የስራ ሀላፊዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት 4ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በጉራጌ ዞን ቸሃ ወረዳ አንዛናባት ቀበሌ መካሄዱን ከወልቂጤ ሬድዮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።


https://www.facebook.com/100068870753847/posts/pfbid0ymsumbYVdZeYV2TqgzozM8FJjUgHzJqRzLGyBUw4jTmYVSz2c3mp3xssLNU9dxYcl/?app=fbl
234 viewsedited  16:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 18:53:39 ዘመነ ክረምት

በኢትዮጵያ የወቅቶች አከፋፈል መሠረት የክረምት ወቅት ከዘመነ መከር፣ በጋና በልግ ቀጥሎ የሚመጣ አራተኛ ወቅት ነው።

ክረምት ከረመ፣ ከርመ ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን የውሃ፣ የነጎድጓድ፣ የመብረቅና የዝናብ ወቅት የሚል ፍቺ እንዳለው የአማርኛ መዝገበ ቃላትና ድርሳናት ያስረዳሉ።

የክረምት ወቅት ተብሎ በዋናነት የሚነገረው ጊዜ ከሰኔ 25 እሰከ መስከረም 26 ያለው ወቅት ሲሆን አንዳንድ ጊዜ ከሚገባበት ቀን ቀድሞ ሊገባና ከሚወጣበት ቀንም ዘግይቶ ሊያበቃ ይችላል።

የክረምት ወቅት የዘርና የአረም እንዲሁም የውሃ ወቅት በመሆኑ ገበሬው እርሻውን የሚያካሂድበት ወሳኝ ጊዜ ነው።

ምድርም አረንጓዴ ለብሳ በአትክልት፣ አዝዕርትና አበቦች ተሸፍና መታየት ትጀምራለች፣ ይህም የውበትና የመልካም ተስፋ ተምሳሌት አለው።

ክረምት ምንም እንኳን የቅዝቃዜና የጭጋግ ሁኔታን ቢይዝም የሰው ልጅ መኖርያ የሆነችው ምድርን በማረስረስ ምግብ እንድታበቅልና ንጹህ አየር እንድትሰጥ የሚደርጋት እጅግ አስፈላጊ የተፈጥሮ ዑደት ነው።

ክረምት በየትኛውም ክፍለ አኅጉር ወቅቶችን እየቀያየረ ምድርን ሲያድስ የሰው ልጆችንም ሕልውና አብሮ በማደስ ሰውና ክረምት ያለውን ቁርኝት ዘላለማዊ አድርጎታል።

በክረምት የሚመጣው ትሩፋት በመከርና በበጋ የሚታይ ውጤት እንደመሆኑ እኛም ዛሬን እንደ ክረምት በመቁጠር ለበጋ የሚበቃ ጠንካራ ስራ መስራት አለብን።

ኢትዮጵያ ከምንም ጊዜ በላይ ሰፊ የክረምት ስራ እንዳለባት አውቀን ሰላሟን ለመጠበቅ፣ ድህነትን ለማሸነፍና ሉዓላዊነቷን ለማስከበር እጅ ለእጀ ተያይዘን መስራት ይኖርብናል።

የክረምት ዝናብ እንደ ጉልበት፣ የክረምት ፀሐይ እንደ ተስፋ፣ የምድርን አረንጓዴ መልበስ በጠንካራ ተግባር እንደሚመጣ ልምላሜ ቆጥረን ለመከርና በልግ የምንጠብቀውን መልካም ውጤት ዛሬ እንስራ።

ምንጭ:- ኢዜአ

- ኢትዮጵያን እናልማ!
- የፈረሰውን እንገንባ!
- ለፈተና እንዘጋጅ!!

https://www.facebook.com/100068870753847/posts/pfbid02WFZ5HDKi4XF8J2sEJ2baziWpVFqAzHkqjMuzCcMjoWqB6KqcQ3zNRjNsZ8mLiD91l/?app=fbl
196 views15:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 18:44:48
ሰኔ 29/2014 ዓ.ም

ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየው ክልላዊ የ8ኛ ክፍል ፈተና ተጠናቀቀ።

በወረዳው 2 ሺህ 507 ተማሪዎች ፈተናው ወስደዋል።

በ21 የመንግሥት እና በ2 የግል በጠቅላላ በ23 ትምህርት ቤቶች ሲሰጥ የቆየው ይህ ፈተና ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም መጠናቀቁን የጉመር ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ገልጿል።

- ኢትዮጵያን እናልማ!
- የፈረሰውን እንገንባ!
- ለፈተና እንዘጋጅ!!


https://www.facebook.com/100068870753847/posts/pfbid0z2QP7nZcwpEdCPJkYEpQ3kyu7kT9hhF7ewLgM2HQ5Ju8hZikbYz8gYuXuRXb67Zgl/?app=fbl
177 views15:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 15:22:03 የሐሞት ጠጠር በሽታ መንሥኤዎች፣ ምልክቶች፣ መከላከያ መንገዶች እና ሕክምና

የሐሞት ጠጠር በሐሞት ከረጢት ውስጥ በሚገኝ የሐሞት ፈሳሽ አልያም ሐሞትን ከጉበት ወደ አንጀት በሚወስዱት ቱቦዎች ውስጥ የሚፈጠር ባዕድ ነገር ነው፡፡

የሐሞት ፈሳሽ በጉበት ሕዋሳት የሚመረት፣ ጨዋማ ንጥረ ነገሮችን ያዘለ ሲሆን የምንመገባቸው ቅባት እና ቫይታሚኖች እንዲፈጩ ይረዳል፡፡ በሰውነታችን የሚገኙ መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ለማጥፋትም ይጠቅማል፡፡

የሐሞት ጠጠር መንሥኤዎች

80 በመቶ የሚሆነው የሐሞት ጠጠር የሚከሰተው በቅባት አልያም በኮሌስትሮል መብዛት መሆኑን የጤና ባለሙያዎች ይናገራሉ።

የሐሞት ጠጠር ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ነገሮች ደግሞ ፡-

• ቅባታማ ምግቦችን ማዘውተር
• ከልክ ያለፈ ውፍረት
• በሰውነት ያለ ቅባት ለመቀነስ የሚረዱ መድኃኒቶችን መውሰድ
• በነፍሰ ጡርነት ጊዜ ከልክ ያለፈ ውፍረት
• የወሊድ መቆጣጠሪያ ክኒን
• የዕድሜ መግፋት በተለይ (በሴቶች ላይ በሽታው ይዘወተራል)
• ስኳር ሕመምና እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

የሐሞት ጠጠር በሽታ ምልክቶች

የሐሞት ጠጠር ለረዥም ጊዜ የሕመም ስሜትን ሳያሳይ ሊቆይ ይችላል፡፡ ሐሞት የሚወጣበት ቱቦ በሐሞት ጠጠር በሚዘጋበት ጊዜ በቀኝ የሆዳችን የላይኛው ክፍል ላይ እየመጣ የሚመለስ ወይም የማያቋርጥ የሕመም ስሜትን ያስከትላል፡፡

የሐሞት ጠጠር በሽታ ወደ ጨጓራ እንዲሁም ወደ ቀኝ ትከሻ እና ጀርባ የመሠራጨት ባሕሪም አለው፡፡ የሕመም ስሜቱ የቅባት እህል ከተመገብን በኋላ መባባስ ከጨጓራ ሕመም እንደንለየው ይረዳል፡፡
ዋና ዋና ምልክቶቹ፡-

• ቅባት ነክ ምግቦችን ስንመገብ ያለመስማማት
• ከምግብ በኋላ የሚፈጠር የመጠዝጠዝ ስሜት
• የማቅለሽለሽ እና የማስመለስ ችግር
• ማስገሳት
• የምግብ ፍላጎት መቀነስ
• በሰውነት ላይ ቀያይ ነጠብጣብ መኖር
• በእንቅልፍ ሰዓት የሕመም ስሜት መታየት
• ዐይን ቢጫ መሆን
• የሰውነት ቆዳ ወደ አረንጓዴ ቢጫነት መቀየር
• የዐይን፣ የቆዳ እና የሽንት ቀለም ቢጫ መሆን
• የሰገራ ቀለም መቀየር
• በቀኝ ጎናችን በላይኛው ክፍል አካባቢ እጅግ ከባድ የሆነ ሕመም

የሐሞት ጠጠር መከላከያ መንገድ
• የተመጣጠነ ምግብ መመገብ
• የምግብ ሰዓታትን ሳይመገቡ አለማሳለፍ
• በቂ ውኃ መጠጣት
• የሰውነትን ክብደት በፍጥነት ያለመቀነስ ጥቂቶቹ ናቸው

የሐሞት ጠጠር በሽታ ሕክምና

የበሽታው የሕመም ስሜት ከፍተኛ ከሆነ የቅባት ምግቦችን መመገብ ማቆም እና የሕመም ማስታገሻ መድኃኒቶችን መውሰድ ለጊዜው ሕመሙን ያስታግሳል፡፡
በርግጥ አንድ ሰው ምልክቶቹ ስለታዩበት ብቻ መድኃኒት ከመውሰዱ በፊት የሐሞት ጠጠር እንዳለበት በምርመራ ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው።

ሕመሙ እየበረታ ከሄደ ግን የሐሞት ጠጠሩን በቀዶ ሕክምና ማውጣት እንደሚገባ የሕክምና ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡

ቀዶ ጥገና ማድረግ የማይቻል ከሆነ ደግሞ ለበሽታው ተገቢውን መድኃኒት በመጠቀም ጠጠሮቹን ማሟሟት ይቻላል፤ ይኽኛው መንገድ ግን ብዙ ዓመታትን እንደሚፈጅ የህክምና ሳይንስ መረጃዎች ያመለክታሉ።


https://www.facebook.com/100068870753847/posts/pfbid0EvoW3tYragzaYM9uoDbeWFy2YdSWhuYvUx75jmuu3HyFySv2H7ZuChAPTaDmYznkl/?app=fbl
190 views12:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 08:43:59 ኢደል አድሃ(አረፋ) በአል በጉራጌ ማህበረሰብ ዘንድ በድምቀት የሚከበር ሃይማኖታዊ በአል ነዉ።

ለዚህ በአል በጉራጌ ማህበረሰብ ዘንድ ሰፊ ቅድመ ዝግጅት የሚደረግለትና በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፋለ ሃገራት የሚኖሩ የማህበረሰቡ ተወላጆች ወደ ትዉልድ መንደራቸዉ በማቅናት ከወዳጅ ዘመዶቻቸዉና ከቤተሰቦቻቸው ጋር አብረዉ የሚየሳልፉበት ነዉ።

በአሉም በማህበረሰቡ ዘንድ ለቀናት የሚከበር ሲሆን የስጋ እና የጎመን ክትፎ በበአሉ የሚዘወተሩ የምግብ አይነቶች ናቸዉ።

በተጨማሪም ይህ በአል የጉራጌ ማህበረሰብ ባህል፣ አንድነት፣ እንገግዳ ተቀባይነት የሚንፀባረቅበትም ነው።

በተጨማሪም እንደጉራጌ በሀገራችን በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ የማህበረሰቡ ተወላጆች ወደ ትውልድ አካባቢያቸው በብዛት የሚከትሙበት በዓል በመሆኑ ተወላጆች ለበአል በመጡበት ተሰባስበው ስለአካባቢያቸው ልማት፣ እድገትና ሰላም ተመካክረው የጋራ መፍትሔ የሚሰጡበት በዓል ማድረግ ይገባል።

በአረፋና በመስቀል በዓላቶች ተራርቆ የቆየው ማህበረሰብ እጅጉ የሚገናኝ ቢሆንም በልማትና በሰላም ጉዳይ መመካከር ብዙም የተለመደ አይደለም። ሆኖም ከባለፈው ስህተታችን ተምረን በየአካባቢያችን በጋራ ተወያይተን የማህበረሰባችን ችግር ለይተን እልባት ለመስጠት በጋራ መስራት ይኖርብናል።

መልካም በዓል

- ኢትዮጵያን እናልማ!
- የፈረሰውን እንገንባ!
- ለፈተና እንዘጋጅ!!

https://www.facebook.com/100068870753847/posts/pfbid0tWkAn7B5vfajfxUD7Ki2XuJ1X6XLe96Y5f5ZKo1x6STjJCmPb55hh5BK5xFvs7fdl/?app=fbl
207 views05:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 21:53:34 “አጭበርባሪዎች ከባንክ እንደደወሉ በማስመሰል የማጭበርበር ሙከራዎችን እያደረጉ በመሆኑ ኅብረተሰቡ ይጠንቀቅ”፦ የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት

አጭበርባሪዎች ከባንክ እንደደወሉ በማስመሰል ገንዘብ ለማጭበርበር ሙከራዎችን እያደረጉ በመሆኑ ኅብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ጥሪ አቀረበ።

አጭበርባሪዎች የግለሰቦች ስልክ ላይ በመደወል እና ከባንክ እንደደወሉ በማስመሰል ሽልማት ደርሷችኋል፣ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎታችሁን አስተካክሉ እና ሌሎች መሰል መልእክቶችን በማስተላለፍ ገንዘብ ለማጭበርበር ሙከራዎችን እያደረጉ እንደሆነ ጥቆማዎች ደርሰውኛል ብሏል አገልግሎቱ።

ግለሰቦች እንደዚህ ዓይነት መልእክቶች በሚደርሳቸው ወቅት አቅራቢያቸው በሚገኝ የባንክ ቅርንጫፍ በመሄድ ከማረጋገጣቸው በፊት ምንም ዓይነት እርምጃ ከመውሰድ በመጠንቀቅ እራሳቸውን ከአጭበርባሪዎች እንዲጠብቁ አሳስቧል።

- ኢትዮጵያን እናልማ!
- የፈረሰውን እንገንባ!
- ለፈተና እንዘጋጅ!!

https://www.facebook.com/100068870753847/posts/pfbid02YYgQ3o4n4kWA4SgqPQtsHY1g8uyLHzhmF1htd1iK2pGjpfxuPd7RmwrzUvFB4CsCl/?app=fbl
221 views18:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 15:23:57 ሰኔ 28/2014 ዓ.ም

6.5 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል ታቅዶ እየተሰራ ነው- ግብርና ጽ/ቤት

የጉመር ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት 6.5 ሚሊዮን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ለመትከል አቅዶ እየሰራ እንደሚገኝ ገለጸ።

ጽህፈት ቤቱ ይህንን ያሳወቀው የመኽር ንቅናቄ መድረክ ባካሄደበት ወቅት ነው።

የግብርና ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊና የተፈጥሮ ሀብት ዘርፍ አስተባባሪ አቶ መሀመድ ናስር እንደገለፁት በወረዳው ሁለት የመደበኛ÷ ሰባት የማህበረሰብ÷ አንድ የፕሮጀክት÷ ሶስት የተቋማት በጥቅልሉ 13 የችግኝ ጣቢያዎች ይገኛሉ ብለዋል።

በወረዳው 6.5 ሚሊየን ችግኞች ለመትከል ታቅዶ እስካሁን ድረስ 6.76 ሚሊየን ችግኞች ከእነዚህ የችግኝ ጣቢያዎች ለተከላ ተዘጋጅተዋል ሲሉም አቶ መሀመድ አክለዋል።

ለእነዚህ ችግኞች የሚሆን 22 የተከላ ቦታዎች የተለዩ ሲሆን እሰካሁን ድረስ 5.5 ሚሊየን የተከላ ጉድጓዶች መዘጋጀታቸውም አሳውቀዋል።

ችግኞቹም ዘርፈ ብዙ አይነት ያላቸው መሆናቸው ያሳውቁት አቶ መሐመድ በአግሮፎረሰተሪ 2.98 ሚሊየን÷ የፍራፍሬ 0.008 ሚሊየን÷ የመኖ 3.759 ሚሊየን÷ የቀርከሃ 0.013 ሚሊዮን በጠቅላላ 6.76 ሚሊየን ችግኞች መሆናቸውን ተገልጿል ሲል የዘገበው የጉመር ወረዳ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።

- ኢትዮጵያን እናልማ!
- የፈረሰውን እንገንባ!
- ለፈተና እንዘጋጅ!!


https://www.facebook.com/100068870753847/posts/pfbid02jMDdCVyp7zxxBpDEsnQLg9kNgeYDBzRfPD2eWEQTjETabeZaSrCsXaYCuBJr5FCrl/?app=fbl
228 views12:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 12:22:08 ሰኔ 28/2014 ዓ.ም

በጉመር ወረዳ በሁሉም የመፈተኛ ጣቢያዎች የ8ኛ ክፍል አቀፍ ብሔራዊ ፈተና መሰጠት ተጀመረ።

የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና በ23 የመፈተኛ ጣቢያ 2 ሺህ 507 ተማሪዎች ክልል አቀፍ ፈተና እየወሰዱ ይገኛል።

የጉመር ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት የፈተና ዝግጅት አስተዳደር የትምህርት ምዘና ጥናት ስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ አበበ ክንፈ እንደገለፁት ፈተናው ለመውሰድ ከተመዘገቡት 2 ሺህ 515 ተማሪዎች ውስጥ 7 ተማሪዎች ከመደበኛ እንዲሁም አንድ ተማሪ ከግል በጥቅልሉ 8 ተማሪዎች ለፈተናው አልተቀመጡም ብለዋል።

23 የጣቢያ ሃላፊዎች÷19 ሱፐርሻይዘሮች÷ 102 ፈታኝ መምህራን ፈተናውን ለመፈተን መመደባቸው አቶ አበበ ገልጸዋል።

በተጨማሪም ለሁሉም ትምህርት ቤቶች ፖሊስና ሚሊሻ መመደቡንም ተናግረዋል።

በወረዳው 21 የመንግስት ትምህርት ቤቶችና 2 የግል ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ 2 ሺህ 507 የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተና እየወሰዱ እንደሆነም ነው የገለፁት።

በተለያዩ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናውን ያለምንም የጸጥታ ችግር እየወሰዱ እንደሚገኝም የፈተና ጣቢያ ኃላፊዎች ገልጸዋል ሲል የዘገበው የጉመር ወረዳ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።

- ኢትዮጵያን እናልማ!
- የፈረሰውን እንገንባ!
- ለፈተና እንዘጋጅ!!

https://www.facebook.com/100068870753847/posts/pfbid0cRet6WifwTYAaGqP8X1HmPPJ19aNx1N55ev9tTZ8XFGPFcwAtR8jEdqEyDjxs751l/?app=fbl
213 views09:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 22:10:25 ሰኔ 27/2014 ዓ.ም
=============
የዘቢዳር አትሌቲክስ ክለብ አትሌቶች የሽኝት ፕሮግራም ተደረገላቸው።

በአትሌቲክሱ ዘርፍ የሚጠበቀው ውጤት ለማምጣት ክለቡን የመደገፍ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ።

የጉራጌ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሰፋ አካሉ በአትሌቲክሱ ዘርፍ የሚጠበቀው ውጤት ለማምጣት የዞኑ አስተዳደር ለዘቢዳር አትሌቲክስ ክለብ የሚያደርገው ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

አትሌቶች በእረፍት ጊዜያቸው በስፖርታዊ ፍቅርና ስነ ምግባር ማህበረሰባቸው እንዲያገለግሉና ተተኪ አትሌቶች ማፍራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

ስፖርቱን ሲሰሩ በወኔና በቁጭት እንዲሁም የጉራጌን ማህበረሰብ ሊያስጠራ በሚችል መልኩ መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አወል ጅሟቶ በአትሌቲክሱ ዘርፍ በቀጣይ አመት ውጤት ሊያመጡ የሚችሉ ስራዎች ያለ ማቋረጥ ይሰራል ነው ያሉት።

ይህንን ደግሞ እውን የሚሆነው አትሌቶቹ የእረፍት ጊዜያቸው እንደ ጥሩ አጋጣሚ ተጠቅመውና ተጨማሪ ልምድ ይዘው ሲመጡ በመሆኑ ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል።

አትሌቶቹ ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ከወትሮ በተለየ ደሞዛቸው ሳይቆረጥ እንዲከፈላቸው ተደርጓል ነው ያሉት።

ዘቢዳር አትሌቲክስ ክለብ ዞኑን ብሎም ሀገር የሚያስጠሩ አትሌቶች መፍለቂያ ክለብ ለማድረግ ከሚመለከታቸው አካላትና ተቋማት ጋር በመሆን በቁሳቁስ፣ በበጀት፣ በአሰልጣኝና በሌሎችም ለመደገፍ ታቅዷል ብለዋል አቶ አወል።

የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ምክትል ኃላፊና የስፖርት ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አደም ሽኩር እንደ ተናገሩት በቀጣይ ክለቡ ህዝባዊ መሰረት እንዲኖረው በውስጡ የሚያስፈልጉ ጂምና ትራክ ሌሎችም ለማሟላት ይሰራል።

እነዚህ ግብዓት እስኪሟላላቸው በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲና በወለቂጤ ሁለገብ ስቴዲየም ላይ አገልግሎቱ እንዲያገኙ ይደረጋል ብለዋል።

አትሌቶች ከእረፍት መልስ ጥሪ ሲደረግላቸው ተመዝነው የሚገቡ በመሆኑ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረግ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት የሴቶች ህጻናት፣ወጣቶች ማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ጠጄ ደነቀ እንደገለጹት ከዚህ በፊት በዞኑ ስፖርቱን ሳይደገፍ እንኳን በራሳቸው ጥረት በመስራታቸው ጉራጌን የሚያስጠሩ አትሌቶች ተገኝተዋል።

ይህንን ለማስቀጠል ዘርፉን መደገፍና የተጀመሩ ስራዎችም አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

አትሌት መለሰ ገብሬ፣ ዳንኤል ወልዴና ሰላም አበበ በጋራ በሰጡት አስተያየት በተደረገላቸው የእረፍት የሽኝት ፕሮግራም መደሰታቸው ተናግረዋል።

በየ ጊዜው በሚደረግልን ድጋፍና ክትትል የበለጠ እንድንሰራ ያደርገናል ያሉት አትሌቶቹ ቀጣይም ውጤታማ እንድንሆን ክለቡ የጀመራቸው እንቅስቃሴ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

የተሰጠን የእረፍት ጊዜ በአግባቡ በመጠቀም ቀጣይ የሚጠበቅብንን ውጤት ለማምጣት ጥረት እናደርጋለን ብለዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

- ኢትዮጵያን እናልማ!
- የፈረሰውን እንገንባ!
- ለፈተና እንዘጋጅ!!


https://www.facebook.com/100068870753847/posts/pfbid02qbaTLxC2T4DuP2hygJGFmezk46BfcMVmZdiAJNHmSUQHHqggv2VJ9FGXEb4yhkz9l/?app=fbl
196 views19:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ