Get Mystery Box with random crypto!

ሐምሌ 1/2014 ዓ.ም የጉመር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፈይሰል ሀሰን 1443ኛውን የኢድ አል | የጉመር ወረዳ መንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት

ሐምሌ 1/2014 ዓ.ም

የጉመር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፈይሰል ሀሰን 1443ኛውን የኢድ አል አድሀ አረፋ በዓል ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

ዋና አስተዳዳሪው በአለም አቀፍ ደረጃ 1443ኛ ጊዜ ለሚከበረው የኢድ አል አድሀ አረፋ በዓልን በማስመልከት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ ብለዋል።

ህብረተሰቡም የኢድ አል ፈጥር በዓል ሲያከብር ከመቼውም ጊዜ በበለጠ የተቸገሩትን በመርዳት ሊሆን እንደሚገባ ዋና አስተዳዳሪው ጠቁመዋል።

አክለውም አሁን ላይ ሀገራችን እንዳትረጋጋ የሚሹ ሀይሎች አንዴ የብሔር ገጽታ በሌላ ጊዜ ደግሞ የሀይማኖት ሽፋን በመስጠት ህብረተሰቡን እያሸበሩ ይገኛሉ ብለዋል።

ስለሆነም ህዝቡ የአካባቢውን ሰላም በማስጠበቅ እንዲሁም ለዘመናት የገነባነውን የሰላም፣ የመቻቻል፣ የአብሮነት፣ የመከባበር እና የመደጋገፍ እሴት በማጠናከር ሀገራዊ የለውጥ ጉዞውን እንዲያሳካ ጥሪ አቅርበዋል።

በመጨረሻም በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአብሮነት እና የመተሳሰብ እንዲሆን ተመኝተዋል።
ኢድ ሙባረክ

- ኢትዮጵያን እናልማ!
- የፈረሰውን እንገንባ!
- ለፈተና እንዘጋጅ!!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/profile.php?id=100068870753847
Telegram:- https://t.me/gummerw
Youtub: -https://youtube.com/channel/UCyqat__kk7lXxzpRv8r7chA