Get Mystery Box with random crypto!

ሰኔ 28/2014 ዓ.ም 6.5 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል ታቅዶ እየተሰራ ነው- ግብርና ጽ/ቤት የጉ | የጉመር ወረዳ መንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት

ሰኔ 28/2014 ዓ.ም

6.5 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል ታቅዶ እየተሰራ ነው- ግብርና ጽ/ቤት

የጉመር ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት 6.5 ሚሊዮን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ለመትከል አቅዶ እየሰራ እንደሚገኝ ገለጸ።

ጽህፈት ቤቱ ይህንን ያሳወቀው የመኽር ንቅናቄ መድረክ ባካሄደበት ወቅት ነው።

የግብርና ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊና የተፈጥሮ ሀብት ዘርፍ አስተባባሪ አቶ መሀመድ ናስር እንደገለፁት በወረዳው ሁለት የመደበኛ÷ ሰባት የማህበረሰብ÷ አንድ የፕሮጀክት÷ ሶስት የተቋማት በጥቅልሉ 13 የችግኝ ጣቢያዎች ይገኛሉ ብለዋል።

በወረዳው 6.5 ሚሊየን ችግኞች ለመትከል ታቅዶ እስካሁን ድረስ 6.76 ሚሊየን ችግኞች ከእነዚህ የችግኝ ጣቢያዎች ለተከላ ተዘጋጅተዋል ሲሉም አቶ መሀመድ አክለዋል።

ለእነዚህ ችግኞች የሚሆን 22 የተከላ ቦታዎች የተለዩ ሲሆን እሰካሁን ድረስ 5.5 ሚሊየን የተከላ ጉድጓዶች መዘጋጀታቸውም አሳውቀዋል።

ችግኞቹም ዘርፈ ብዙ አይነት ያላቸው መሆናቸው ያሳውቁት አቶ መሐመድ በአግሮፎረሰተሪ 2.98 ሚሊየን÷ የፍራፍሬ 0.008 ሚሊየን÷ የመኖ 3.759 ሚሊየን÷ የቀርከሃ 0.013 ሚሊዮን በጠቅላላ 6.76 ሚሊየን ችግኞች መሆናቸውን ተገልጿል ሲል የዘገበው የጉመር ወረዳ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።

- ኢትዮጵያን እናልማ!
- የፈረሰውን እንገንባ!
- ለፈተና እንዘጋጅ!!


https://www.facebook.com/100068870753847/posts/pfbid02jMDdCVyp7zxxBpDEsnQLg9kNgeYDBzRfPD2eWEQTjETabeZaSrCsXaYCuBJr5FCrl/?app=fbl