Get Mystery Box with random crypto!

ኢደል አድሃ(አረፋ) በአል በጉራጌ ማህበረሰብ ዘንድ በድምቀት የሚከበር ሃይማኖታዊ በአል ነዉ። | የጉመር ወረዳ መንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት

ኢደል አድሃ(አረፋ) በአል በጉራጌ ማህበረሰብ ዘንድ በድምቀት የሚከበር ሃይማኖታዊ በአል ነዉ።

ለዚህ በአል በጉራጌ ማህበረሰብ ዘንድ ሰፊ ቅድመ ዝግጅት የሚደረግለትና በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፋለ ሃገራት የሚኖሩ የማህበረሰቡ ተወላጆች ወደ ትዉልድ መንደራቸዉ በማቅናት ከወዳጅ ዘመዶቻቸዉና ከቤተሰቦቻቸው ጋር አብረዉ የሚየሳልፉበት ነዉ።

በአሉም በማህበረሰቡ ዘንድ ለቀናት የሚከበር ሲሆን የስጋ እና የጎመን ክትፎ በበአሉ የሚዘወተሩ የምግብ አይነቶች ናቸዉ።

በተጨማሪም ይህ በአል የጉራጌ ማህበረሰብ ባህል፣ አንድነት፣ እንገግዳ ተቀባይነት የሚንፀባረቅበትም ነው።

በተጨማሪም እንደጉራጌ በሀገራችን በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ የማህበረሰቡ ተወላጆች ወደ ትውልድ አካባቢያቸው በብዛት የሚከትሙበት በዓል በመሆኑ ተወላጆች ለበአል በመጡበት ተሰባስበው ስለአካባቢያቸው ልማት፣ እድገትና ሰላም ተመካክረው የጋራ መፍትሔ የሚሰጡበት በዓል ማድረግ ይገባል።

በአረፋና በመስቀል በዓላቶች ተራርቆ የቆየው ማህበረሰብ እጅጉ የሚገናኝ ቢሆንም በልማትና በሰላም ጉዳይ መመካከር ብዙም የተለመደ አይደለም። ሆኖም ከባለፈው ስህተታችን ተምረን በየአካባቢያችን በጋራ ተወያይተን የማህበረሰባችን ችግር ለይተን እልባት ለመስጠት በጋራ መስራት ይኖርብናል።

መልካም በዓል

- ኢትዮጵያን እናልማ!
- የፈረሰውን እንገንባ!
- ለፈተና እንዘጋጅ!!

https://www.facebook.com/100068870753847/posts/pfbid0tWkAn7B5vfajfxUD7Ki2XuJ1X6XLe96Y5f5ZKo1x6STjJCmPb55hh5BK5xFvs7fdl/?app=fbl