2022-07-10 21:38:15
የኡመር ኢብኑል ኸጣብ መስጂድ (26) ጀመዐ ምን እያደረገ ነው?
ይህ ጀመዓ ታጋሽና እጅግ ሲበዛ መልካም ስራ ወዳድና የምኮራበት ጀመዐ ነው። ኸይር የተባሉ ስራዎችን ሁሉ እያጣጠመ ደስ እያለው ሳይሰለች አንድ ሆኖ ይሰራል።
ለምሳሌ፦
ኮሮና አለምን ባስጨነበቀት በርካታ ሚስኪኖች እርዳታ ባስፈለጋቸውና መንግስትም ለመልካም ድጋፍ ማህበረሰቡን ባነሳሳበት ወቅት ቁጥራቸው ከ አራት መቶ (400) በላይ ለሆኑ የአካበቢው ማህበረሰብ ሃይማኖትን ሳይለይ የአንድ ወር ለቀብ ማዳረስ ችሏል።
ይህ ወጣት በሀገራችን የአረንጓዴ አሻራን ለማሳረፍ በቀረበለት ጥሪ መሰረት በአካባቢው ከፍተኛ ተሳትፎ በማድረግ በርካታ ችግኞችን መትከል የቻለ ጀመዐ ነው። በነዚህም ስራዎች ከወረዳው መስተዳደር የምስክር ወረቀት ሊበረከትለት ችሏል።
የዚህ መስጂድ ወጣት ጀመዓ በየአመቱ ረመዳን ከመግባቱ በፊት በቋሚነት ወደ 320 ሚስኪኖች የወር አስቤዛ የሚያከፋፍል ሲሆን ልክ እንዲሁ ለአረፋ በአል ሚስኪኖች የኡዱህያ ስጋ እንዲያገኙ ተግቶ ይሰራል በዚህም በቋሚነት የተያዙትን እነዚህ 320 ቤተሰቦች ይረዳል።
ምንም እንኳን ዘንድሮ በአንዳንድ ሰዎች ይህንን የመልካም ስራ የማሰናከል ሙከራ ቢደረግም ሳይሳካላቸው ቀርቆ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መልኩ ኡዱህያው መዳረስ ችሏል። አልሀምዱሊላህ! ከታች የተያያዘውን ምስል ይመልከቱ።
የወጣቱ መልካም ስራ በዚህ የተገደበ አይደለም ፣ ይህ ጀግናና መልካም ስራ ወዳድ ወጣት በመስጂዱ የሚገኘውን የመፀዳጃ ቤቶች ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ሰርቶ ለመስጅዱ ኮሚቴ አስረክቧል።
በመስጂዱ አካባቢ ያለው አብዝሀኛው ማህበረሰብ የሚኖረው በቀበሌ ቤት ሲሆን ቤቶቻቸውም እጅግ ጠባብ ነው። ይህም ሰው ቢሞት እንኳ ጀናዛ ለማጠብ የማይመች መሆኑን ከግምት በማስገባት በመስጂዱ ጊቢ ውስጥ የተሟላ የጀናዛ ማጠቢያ ማዘጋጀት ችሏል ፤ በዚህም በአካበቢውም ሆነ ከሌላ ቦታ ለሚመጡ ጀናዛዎች የተሟላ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።
ይህ ኸይር ወዳድ ወጣት መስጂዱ ውስጥና በአካባቢው ያሉ ችግሮችን አነፍንፎ በማጥናት መስጂዱንም ሆነ በአካባቢው የሚገኘውን ማህበረሰብ (ሃይማኖትን ሳይለይ) ይጠቅበት ዘንድ 280 ሜትር ጥልቀት ያለው የከርሰ ምድር ውሃ ማስቆፈር ችሏል። ይህ ሁሉ የሆነው በተሟላ የአላህ እዘጋ ቀጥሎም በወጣቱ የበረታ ትብብርና ትዕግስት ነው።
እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት ዋናዋና ስራዎች ሲሆኑ ሌሎች ያልተጠሰቁ ስራዎችንም መስራት ችሏል።
የወጣቱ መልካም ስራ በአላህ ፍቃድ በዚህ አያበቃም አላባቀምም ገና ብዙ ተስፋ የሚጣልበት ብርቱ ወጣት ነውና አላህ ከሸረኞች ተንኮል ይጠብቀው ዘንድ እንዲሁም ወደፊት የተሻሉ ስራዎችን ለመስራት አላህ ይረዳው ዘንድ በዱዓ አስታውሱት!
ከታቸወ መፀዳጃ ቤቱ በፊትና አሁን ገፅታ ይመልከቱ።
መልካም ስራዎች ሁሌም ቢሆን መሰናክሎች አያጡትም ታግሶ መሰናክሎችን ያለፈ ግን መጨረሻው ያማረና የሰመረ ይሆናል።
ይህንን ሼር አድርጎ ባስተላለፈ ላይ ሁሉ የአላህ እዝነት ይስፈን!
አቡ ቁዳማ
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
110 views18:38