2022-07-17 19:37:54
ስርዓተ አልበኝነትን ሕግን በማስከበር መጠፍነጉ የግድ ነው!
በሶስት አመት ቆይታ ብቻ!...
- ከሸራትን 2011 ጀምሮ አንድነት እንዳይኖር፣ እንዲፈርስ በግልፅ ሲቃወሙ እንደነበር
– ከ2011 በፊት ህዝቡን ሲያስገርፉ፣ በወሸት ምስክር ሲያሳስሩ
– ተቋማዊ ግንባታ እንዳይሳካ
– ከ10 ያላነሱ የሽምግልና ጥረቶችን ሲያሰናክሉ
– ከሐይማኖት ይልቅ የለቲካዊ እንቅስቃሴ ላይ ያተኮሩ
– ጥቂት ግለሰቦች በተከበረው ሱፊያ ስም እየነገዱ
– ህጋዊ ሂደት ተከትለው የተወሰኑ ውሳኔዎችን ለመተግበር ፈቃደኛ ካለመሆንም አልፈው ስልጣን ከምንለቅ ደም ይፈሳል በማለት
– የሙስሊሙን ሐብት እና ገንዘብ በመዝረፍ
– መንግስትንም ሆነ ህዝበ ሙስሊሙን ለማሳሳት
– የሀገሪቷ ግማሽ አካል የሆነውን ህዝበ ሙስሊም ለልማት እና አገራዊ ግንባታ አስተዋፅኦ እንዳያደርግ ከውስጥ እና ከውጭ አካላት ጋር በመተባበር
– የአንድነት መጅሊሱ የሁሉም ክልል መጅሊሶች በተገኙበት በነገው እለት በሸራተን ሆቴል በሚደረገው የጠቅላላ ጉባኤ በታቀደለት መሰረት የሚካሄድ በመሆኑ ህዝበ ሙስሊሙ በጉጉት የሚጠብቀው መሆኑን በማወቅ ይህንን ታላቅ እድል ለማደናቀፍ በዛሬው እለት እየተሰራ መሆኑ ልብ ይሏል።
በመጅሊሱ ቅጥር ጊቢ ካለፉት ጊዜያት ጀምሮ የሚካሄዱት ውንብድና መሰል እንቅስቃሴዎች፣ ሕገ-ወጥነትን የተላበሱ አካሄዶች፣ በማን አለብኝነት የሚደረጉ ቅስቀሳዎች፣ አንድነትን የሚንዱና ሕዝብ ለሕዝብ ደም እንዲፋሰስ የሚስተጋቡ ድምጾች፣ ተቋምን የማፈራረስ ሂደቶች ፤ ከታሪካዊና ፖለቲካዊ ጠላቶቻችን ጋር በጣምራነት የመስራት ኢ-ሞራላዊ ድርጊቶች፣ ተቋምን ለግለሰቦች እርስትነት የማጽደቅ ክንውኖች፣ ትዉልድ እንዲከስም የታቀዱ እቅዶች፣ ...ወዘተረፈ እኩዮች ከዛሬው ክስተት ጋር በነጠላ ሳይሆን በጣምራነት ልንመለከተዉ የሚገባ አሳፋሪ እንዲሁም ኃይማኖትን ሽፋን በማድረግ ለሀገር ሠላምና ብልጽግና ሳንካ ከሆኑ ቡድኖች ጋር በጋራ የመስራት የሁከት፣ የብጥብጥ አጀንዳ መሆኑ ልብ ይሏል።
የቅርብ ጊዜውን በአዲስ አበባ መጅሊስ ላይ በኃይል ለመያዝ የተደረገውን የውንብድና ተግባር፤ ሎሎችም... ከዚህ ቀደም ደም ለማፋሰስ ሳይቀር የተደረጉ እኩይ እንቅስቃሴዎች በትዕግስት እንደታለፉ የሚታወቅ ሲሆን መንግስትና ሕዝባችን ሆደ ሰፊ በመሆን እንዳስተናገዱት እሙን ነው።
መንግስታችን ጥልቅ በሆን መንገድ ባሳየው ትዕግስትና ጉዳዮችን በጥንቃቄ ለመፍታት ላሳየዉ የተከበረ ተግባር በእጅጉ የምናከበር ሲሆን በተለይም በነገው እለት በሸራተን አዲስ የሚካሄደው ጉባዔ በሠላም እንዲከናወን ላደረገው ድጋፍ ከፍተኛ ምስጋና እያቀረብን ጥቂቶች ጉባዔውን በተለያየ መልኩ ለማደናቀፍ ቅስቀሳ ሲያደርጉ ተስተዉለዋል።
መንግስት ላሳየው ሆደ ሰፊነት ምስጋናችንን እያቀረብን ይህ ጥቂት ኃይል ከመማርና ወደሰላም ከመመለስ ይቅል በአፍራሽና አንድነትን በመናድ እንቅስቃሴ/ተግባር ውስጥ በመቀጠሉ መንግስት ሕግ የማስከበር ስራዉን እንዲሰራ አጥብቀን እንጠይቃለን።
ኢትዮጲያዊያን ሙስሊሞች በነገዉ እለት በጉጉት የሚጠብቁትን የሸራተን ጉባዔ ለማደናቀፍ የሚንቀሳቀስ ማንኛውም አካል ከድርጊቱ እንዲቆጠቡና ወደ መልካም ቀልቡ እንዲመለስ እንጠይቃለን።
ሙጂብ አሚኖ
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
https://t.me/fethmedia
132 viewsedited 16:37